ዶ/ር አብይ አህመድ እና አቶ ደመቀ መኮንን በአብላጫ ድምጽ አሸነፉ

አባይ ሚዲያ ዜና 

በሃዋሳ ጠቅላላ ስብሰባውን እያደረገ የሚገኘው የኢህአዴግ ድርጅት ለሊቀመንበርነት ከቀረቡት እጩዎች ውስጥ ዶክተር አብይ አህመድን ከፍተኛ የድጋፍ ድምጽ በመስጠት መርጧቸዋል ። 

ለምርጫው ከተሰበሰብው 177 ድምጽ ዶክተር አብይ አህመድ 176 የድጋፍ ድምጽ በማግኘት የድርጅቱ ሊቀመንበር በመሆን እንዲቀጥሉ ተወስኗል። ከዶክተር አብይ ጋር ለምርጫ የተቀረቡት አቶ ደመቀ መኮንን ሲሆኑ አንድ የድጋፍ ድምጽ እንዳገኙ ተገልጿል። 

ለድርጅቱ  ምክትል ሊቀመንበርነት የተወዳደሩት አቶ ደመቀ መኮንን እና ዶክተር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ሲሆኑ፤ አቶ ደመቀ መኮንን 149 ድምጽ በማገኘት የድርጅቱ ምክተል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። ዶክተር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ከጠቅላላው የድምጽ አሰጣጥ 15 ድጋፍ እንዳገኙ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ የጀመሩት የለውጥ ጎዞ በቀጣይነት ስኬታማ እንዲሆን የዛሬው የኢህአዴግ ሊቀመንበርነት ምርጫ ውጤት ከፍተኛ አስተዋጾ እንደሚያደርግ ተንታኞች ገለጸዋል።