የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ያቀረቡላቸውን የጉብኝት ግብዣ ተቀበሉ

አባይ ሚዲያ ዜና

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለጣሊያኑ አቻቸው በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እንዲያደርጉ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ ተዘገበ።

ጣሊያንን በጠቅላይ ሚንስትርነት እያገለገሉ ያሉት ጁሴፔ ኮንቴ ሁለት ቀናት የሚቆይ የስራ ጉብኝት ለማድረግ በሚቀጥለው ሳምንት ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሏል።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ከጣሊያኑ አቻቸው ጋር ከኢንቨስተመንት በተጨማሪ በተለያዩ ጉዳዮች ውይይት እንደሚያደርጉ የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ካሰፈሩት መልክት ለመረዳት ተችሏል።

የሁለቱ አገራት ጠቅላይ ሚንስትሮች በሚቀጥለው ሐሙስ በአዲስ አበባ የሚያደርጉት ውይይት ኢትዮጵያ ከአውሮፓ አገራት ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያጠናክረዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በጥቅምት ወር ( October 31, 2018) ወደ አውሮፓ በማቅናት ከጀርመን መርሃመንግስት አንጌላ መርክል ጋር እንዲሁም አውሮፓ ከሚገኙ ኢትዮጵያኖች ጋራ በፍራንክፈርት ከተማ ውይይት ለማደረግ ፕሮግራም እንደያዙ መገለጹ ይታወሳል።