ኢት-ኢኮኖሚ      /ET- ECONOMY

የጦር አበጋዞች በስመ ሶሻሊዝም የብሄር ብሄረሰብን ጥያቄ በማራገብ፣ ማርክሲዝም ሌኒኒዝም፣ ማኦይዝም ደቀ መዝሙር የነበሩ የጀሌውን ወጣቶች ህሊና አጠቡት፡፡ የጦር አበጋዞቹ እልፍ አእላፍ ገበሬዎችን በወታደርነት በመመልመልና አንዱን ዘር በሌላው ዘር ላይ ጥላቻ በመቀስቀስ፣ የራሳቸውን ታማኝ ጦር ማደራጀት ቻሉ፡፡ የጦር አበጋዞቹ  የማንነት ጥያቄ ኢንተርፕሬነር ፈላስፎች ሆኑ፡፡ በኢትዩጵያ ውስጥ በዘመነ-ጦር አበጋዞች ‹‹የማንነት ጥያቄ›› ዘውጌ ብሄረተኛነት  በጉጠኛነት፣ በዘውገኛነትና በዘር ላይ የተመሠረቱ ድርጅቶች መኃል፤ ህዝባዊ ግምባር ሓርነት ኤርትራ (ህግሓኤ)፣ ኤርትራ አርነት ግንባር (ኤአግ)፣ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፣ ግምባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ (ግገሓት)፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦሮሞ እስላማዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦእነግ)፣ ምዕራብ ሶማልያ ነፃ አውጭ ግንባር (ምሶነግ)፣ በሱማሌ (ኦኤንሌኤፍ)፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ)፣ በጋንቤላ ነፃ አውጪ ግንባር (ጋነግ)፣ የሲዳማ አርነት (ሲአን)፣ ቤኒ-ሻንጉል ነፃአውጪ ግንባር፣ አፋር ነፃ አውጭ ግንባር (አነግ) ወዘተ ማዕከላዊውን መንግስት በማዳከም የፖለቲካ ስልጣን የሚቆጣጠሩበት ስርዓት ሆነ፡፡ በዘመነ-ጦር አበጋዞች በነፃ አውጭ ስም፣ በአንድ ዘር ላይ የተመሠረተ የግላቸው ሎሌ ጦር ሰራዊት ለራሳቸው ጥቅምና ስልጣን በማደራጀትና በመመልመል በብሔራቸው ስም ስልጣን ለመያዥ ይታገላሉ ጀመር፡፡ የጦር አበጋዞቹ በግለሰቦችና በተለያዩ ቡድኖች ላይ ጥላቻን በመፍጠር የራሳቸውን የጦር ሰራዊት በማቆቆም ጥቅማቸውን ያስጠብቃሉ፡፡ የኢህአዴግ ህወሓት (የትግራይ)፣ ኦህዴድ (የኦሮሞ)፣ ብአዴን (አማራ)፣ ደቡብ ወዘተ በዘርና ቌንቌ  ላይ የተመሠረተ  የማንነት መታወቂያ የሚሠጡ የንግድ ድርጅት ጋር ይወዳደራሉ፣ በዛም የዘርህ ግንድ ተጣርቶ መታወቂያ ይሰጥህና በጀት ተደልድሎልህ፣ ሥራና ደሞዝ ይቆረጥልሃል ማለት ነው፡፡ ‹‹የማንነት መታወቂያ የሚሠጥ የንግድ ድርጅት አመሰራረቱ፣ በግለሰብና በቡድን የተደራጁ ግለሰቦች የግል ፍልጎታቸውንና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የቡድን የማንነት ጥያቄን በማራገብ  ዘውጌ ብሄርተኛነትን በህዝብ ላይ በኃይል የሚጭኑበት ስርአት ነው፡፡ የጦር አበጋዞቹ በተለይ ተለዋዋጭ ሁኔታዎቹን ሁሉ በመጠቀምና ያለውን ክፍተት፣ ልዩነትና ጥላቻን በማራገብና እንዲሁም አዲስ ልዩነቶችን በመፍጠር በኃይል በመጠቀም ዘውጌ ብሄርተኛነትን ይፈበርካሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከሰማንያ በላይ የዘርና ቌንቌ ያለት ሃገር በመሆኖ ወደ ሰማንያ መንግሥታት ምሥረታ መሸጋገራችን አይቀሬ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም በጂኦግራፊያዊ አከላለል ላይ እንደቀድሞው ቢከፋፈል ግጭት ይጠፋል፡፡ ክልሎችን በዘር እና በቌንቌ በድንበር እየለያዩ መለየት የትግራይ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የጉራጌ፣ የሃዲያ፣ ወዘተ ‹‹ክልላዊ ብሄራዊ መንግሥት›› በማለት ድንበርና ወሰን ማካለል ወደማያባራ ግጭትና ጦርነት ህዝብን ይከተዋል፡፡ ዛሬ የምናየው በየቦታው የተከሰተው የህዝብ መፈናቀል የህወሓት/ኢህአዴግ የፈለሰፈው በዘር እና በቋንቋ ላይ የተመሠረተ የፊዴራል መንግሥት ሥርዓት አወቃቀር ነው እንላለን፡፡  

ደውሉ የሚደወለው ለማን ነውFor Whom The Bell Tolls?

asferi

የትናንቱ ውጊያ ከኮረብታው ላይ፣ ሲያውድ የባሩድ ሽታ፣

በዛ ቅዝቃዜ! ሆድ ሲንቦጫቦጭ፣ ሙቀት በብርድ ሲረታ፣ 

የጠመንጃ ጩኸት፣ የተኩስ እሩምታ ሰማየ ሰማያቱን ሲነድለው

በዛ ውጊያ የጦር ጀነራሎቹ ትክክል ነበሩ …ማን አለና?

ለባድማ መሬት ብሎ ሰው ይሞታል፣ ግን ለምን? እነሱም አያውቁማ!!!

ያመረቀዘ ቁስላችን፣ ለእነሱ ክብርና ኩራት ሆናቸው!!!

በባድማ! ያ ሁሉ የደሃ ልጅ ረግፎ፣ የአምስቱ የጦር መኮንኖቹ  ሲሳይ፣

በሹመት ላይ ሹመት፣ በሜዳልያ ላይ ሜዳልያ፣ በበላይ ላይ በላይ፣

የእብደትና ህመም ደዌችንን፣ በእርግጥ ያውቃሉ ያሳለፉነውን ስቃይ፣  

ታዲያ! ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?

ጊዜው እንደ ወንዝ እየገዘፈ፣ እንደ አውሎ ንፋስ እየከነፈ፣ ነፍስ ነፍስን ካጠፋ፣

የባህር ማዶ ቄጤማ፣ ሲወድቅ ሲነሳ በተስፋ

ታዲያ ደውሉ የሚያቃጭለው ለማን ነው? ኩኩሉ ሳይል አውራ ዶሮው፣

የደሃ ልጅ የሆናችሁ፣የእናንተን ዕጣ ፈንታ ልንገራችሁ፣

ከመሞታችሁ በፊት፣ ቀኑን ተሠናበቱ፣ ሰማየ ሰማያቱን እያያችሁ፣

በመጨረሻ እስትንፋሳችሁ፣ ትሁን ንዛዜችሁ ለእናታችሁ!!!

ነፍሳችሁ ስታርግ፣ ትሰወራለች ቀስ ብላ ጥላችሁ፣

በድቅድቁ ጨለማ፣ በነጎድጎዳማ መብረቅ ሲርድ ሰማይ፣

ለተቀጨ ዓላማችሁ ብካይ፣ አጎሩ ለረገፈ መንፈሳችሁ ታላቅ ራዕይ፣

ነፍስ ረቂቅ ሚስጢር፣ እንግዳ ነገር ሆነች ዐይናችሁ ላይ፣

ፀጥታው ባርቆ ይሰማል፣ በዝምታ አድምጥ የልብህ ትርታ ካንተ ስትለይ፣

የብርሃን ጨረር ፈንጥቃ ለስንብት፣ በዚህ ዓለም ከተስፋ ሌላ አረ ምን ሊታይ?

ሞታችሁን ባናይ እንኮን፣ ያዩት ይመሰክሩ የሌት ጨረቃ የቀን ፀሃይ

የዓይነ ስውር ዓይን ሲበራ፣ ሞት በህይወት ልትረታ ትንሳኤ ላይ፣

ታዲያ እማማ፣ ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?

ጊዜው እንደ ወንዝ እየገዘፈ፣ እንደ አውሎ ንፋስ እየከነፈ፣ ነፍስ ነፍስን ከገፋ፣

የባህር ማዶ ቄጤማ፣ ሲወድቅ ሲነሳ በተስፋ

ድህነትና ርሃብ፣ በሽታና ሰደት ሳናጠፋ

በቌንቌ ተካለን፣ ማኛ ጤፍ ዘር ስንነፋ      

ጦርነት አርግዘን ስናናፋ፣ ድንቁርናችን ምነው ከፋ

ዛሬም ወገን በወገን ላይ፣ በዘር ጦር ሰብቀን ስንነሳ፣

የባደማ ፆረና ሞት አልፈን፣ በወልቃይት፣ራያና አፋር ጦር ሜዳ ደንገላሳ፣

ታዲያ እማዬ ደውሉ የሚደወለው ለእኛ ሞቾች ነው?  ትንቢተ ትንሣዔ ራቀ ምነው?

ጦርነት ‹መቼም የትም አይደገም!!!› ሳንል! መፈናቀላችን ስለምን ነው! ሰደቱንስ መች ለመነው?

የሰው ልጅን ከኃጢያቱ እንፈውሰው፣ ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?

ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው? ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?

(እኔና አንተ ለምናውቀው፣ በባድማ ጦርነት ለቀበርከው ማሙሽና፣ ለኩኩሻ መታወሻ ትሁን)

ለኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የጦርነት ሠማዕታት ትሁን!!! ጦርነት መቼም የትም አይደገም!!!

For Whom The Bell Tolls?

WRITTEN BY HETFIELD/ULRICH/BURTON

Make his flght on the hill in the early day

Constant chill deep inside

Shouting gun, on they run through the endless grey

On they fight, for they’re right, yes, but who’s to say?

For a hill, men would kill. Why? They do not know

Stiffened wounds test their pride

Men of five, still alive through the raging glow

Gone insane from the pain that they surely know

For whom the bell tolls

Time marches on

For whom the bell tolls

Take a look to the sky just before you die

It’s the last time he will

Blackened roar, massive roar, fills the crumbling sky

Shattered goal fills his soul with a ruthless cry

Stranger now are his eyes to this mysteryHears the silence so loud

Crack of dawn, all is gone except the will to be

Now they see what will be, blinded eyes to see

For whom the bell tolls

Time marches on

For whom the bell tolls