the-harrar-gate

አውቃለው አይፈራም ሃረሪው ወገኔ

ጨክኖ አይዘጋውም በሩን እሱ በኔ ።

ከላዩ ቁጭ ብለው አሳዘኑት ዛሬ
ክብሩን አወረዱት የዋሁን ሃረሬ ።
ይፈራል ወይ ግንቡ ይፈራል ወይ ጀጎል
ጀግኖቹ ሲመጡ ከቶ ላይቀበል ።
ዘር አምላኪ ፈሪ ወኔው የሌላቸው
ለስሙ ቁጭ ብለው ከሩቅ ሲያዩዋቸው
ለካስ ከጅቦች ጋር ተቀናሾች ናቸው ።
ሰው በሰውነቱ ከቶ ላይከበር
ተማምለው ከጅብ ብቻ ለአንዲት ወንበር
የመጣን እንግዳ ከሩቅ ለማባረር ።
ጉዳይ አስፈጻሚ ተላላኪ ሁላ
ቢፈራም አይደንቅም ፍለጋ ከለላ ።
ግን አይደሉም ከቶ ሲያልፍም አይነካቸው
በስሙ ተጠርተው ሃረሪዎች ተብለው
ለካስ የቀን ጅቦች ትርፍራፊ ናቸው ።
በል እሪ በል ጀጎል የደጋጎች መንደር
ይፈራል ወይ ጀጎል ይፈራል ወይ ሃረር
ከልካይ የሌለበት ውብ አጥርህ ሲደፈር ።
ወይስ ፈራህ አንተም ጀጎል ሰው አክባሪ
በአጥርህ ተከልለህ ሆዳሞችን ጧሪ ?
ይፈራል ወይ ጀጎል ይፈራል ወይ ሃረር ?
ማን ይሆን ከልካዩ ግንቡን ለማቋረጥ ለማለፍ በስሩ
ኢትዮጵያዊነት ነው የሃረሪው ክብሩ ።
ስቶክሆልም
ኦክቶበር 2018