ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል የካቤኔ ሹመት አደረጉ

አባይ ሚዲያ ዜና 

የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር  ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል የክልሉን የካቤኔ አባላት ለሹመት አቀረቡ። 

ክልሉን ያገለግላሉ ያሉትን ዘጠኝ እጩ ግለሰቦችን ሹመት እንዲጸድቅላቸው ምክትል ርእሰ መስተዳድር  ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ያቀረቡት ጥያቄም ተቀባይነት ማግኘቱ ተዘግቧል። 

ከካቤኒ አባላቱ በተጨማሪ ለዞን ዋና አስተዳዳሪነት ሶስት ግለሰቦች ሲሾሙ የክልሉ ምክር ቤትም አዲስ  አዲስ አፈ ጉባኤ ተመርጦለታል።

የዶ/ር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል የአሁኑ የካቤኔ ሹመት ከወትሮ እጅግ እንደሚለይም ተገልጿል። በምክትል ርእሰ መስተዳድር  ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ከቀረቡት 9 የካቤኔ አባላት መካከል 6ቱ ሴቶች መሆናቸው ከምንም ጊዜ በላይ የካቤኔ ሹመት አሰጣጡ ለየት እንዳደረገው ተነግሯል። 

የጾታ ልዩነት ለአገር ግንባታ እንቅፋት መሆን አይችልም በሚል እሳቤ በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የካቤኔያቸውን ግማሽ በመቶ  የስልጣን እርከንን በአንስት ጾታ  እንዲያዝ በማድረግ ሴቶች በአገር ግንባታ ላይ ያላቸውን ጉልህ ሚና እንዲወጡ ማድረጋቸው አይዘነጋም።