የተዋሐደች ኢትዮጵያን ለመገንባት አዲስ የመንግሥት የአስተዳደር አካባቢዎችን ለመወሰን የሚያሰችል ውጥን ሀሳብ (በእንግዳሸት ቡናሬ እና በሺፈራው ሉሉ)

0

የተዋሐደች ኢትዮጵያን ለመገንባት አዲስ የመንግሥት የአስተዳደር አካባቢዎችን ለመወሰን የሚያሰችል ውጥን ሀሳብ

Proposed New Ethiopian Government Administrative Boundary System for Unified Nation Building

ለሕዝብ ውይይት የቀረበ

Presented for National Debate

የጽሑፉ ዋናው ፍሬ ሀሳብ በአጭሩ በዐማርኛ ተተርጉሞ የቀረበ

By
በእንግዳሸት ቡናሬ / Engidashet Bunare (Water Engineer) andበሺፈራው ሉሉ / Shiferaw Lulu (Hydrogeologist)
E-mail: [email protected]/engidash[email protected] [email protected]

ነሐሴ 2010 /September, 2018
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ / Addis Ababa, Ethiopia

page1image5688page1image5848page1image6008page1image6168

Page 1 of 12

መግቢያ

ይህ ጽሑፍ በእንግሊዘኛ ቋንቋ “Proposed New Ethiopian Government Administrative Boundary System For Unified Nation Building” በሚል ርዕስ በነሐሴ ወር 2010 ዓ.ም.

ተዘጋጅቶ ከቀረበው የጥናት ጽሑፍ በአጭሩ የቀረበ ነው፡፡ የቀረበው የጥናት ሀሳብ በእንግሊዘኛ በመሆኑና ለብዙ ሰዎች አመቺ ላይሆን ይችላል ብለን በመገመት፤ እንዲሁም ሁሉንም ለመተርጎም ጊዜ የሚወስድ

በመሆኑ ጠቅለል ያለ ሀሳቡን በአጭሩ በዐማርኛ ተርጉመን አቅርበናል፡፡

ለረዥም ጊዜ የአገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ወይም መጻይ ዕድልን በተመለከተ ስንጨነቅ ነበር፡፡ ካለንበት ጎሳን መሠረት ካደርገ ፖለቲካ፤ በተለይ ጥላቻን፣ ስግብግብነትን እና ሙስናን በማነሳሳት እና በመጨረሻም ሀገሪቱን ለማፈራረስና ለመለያየት ከወጠነ ፖለቲካ የሚያላቅቅ የመፍትሔ ሀሳብ ለማግኘት ስንወያይ ነበር፡፡ በዚህ ዉይይት ወቅት፣ የዚህ ጽሑፍ ሀሳብ የተጸነሰዉ እ.ኤ.አ. በ 2006/07 በደቡብ ክልል በ 10 ወረዳዎች ዉስጥ የዉሃ ሀብት አለኝታ ዳሰሳ ጥናትና በሃይቅ እና በወንዝ ውሃ የብክለት ጥናት የማማከር አገልግሎት እያካሄድን በነበረንበት ወቅት ነበር፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህንን የተጸነሰዉን ሀሳብ ስለ አገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ወይም መጻይ ዕድል ተመሳሳይ ሀሳብ ላላቸው ሰዎች እንዴት እንደምናደርስ ሀሳቦችን ስንለዋወጥ ነበር፡፡

የአገራችን ሰዎች በተለያዩ ጎሳዎች መስመር አበጅተው የተከፋፈሉ በመሆናቸዉ እ.ኤ.አ. እስከ 2016 ድረስ እንደነዚህ ያሉ ሀሳቦችን ለማቅረብ በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ ሆኖም ግን እ.ኤ.አ. ከ 2015 ጀምሮ በአገሪቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ በፍጥነት እያሽቆለቆለ፣ የጎሳ እና ፖለቲካ ግጭቶች እና አለመግባባቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተባባሱ መጡ፡፡. እ.ኤ.አ. ከ 2017 ጀምሮ ሰዎች ስለጎሳ ፖለቲካ መጠየቅ መጀመራችዉ እና የጎሳ ፖለቲካ ችግር የህዝብ ግንዛቤ በማግኘቱ በይፋ ስለችግሮቹ ማንሳት በመጀመሩ፤ ይህ ሁኔታ የተጸነሰዉን ሀሳብ እንድንጽፍ እና እንድናቀርብ አነሳስቶናል፡፡

በመሆኑም እ.ኤ.አ.ከ 2018 መጀመርያ ጀምሮ በየጊዜዉ በትንሽ በትንሹ እየጻፍንና በተጓዳኝ የፖለቲካ ሁኔታዉን እያየን ሳለን በድንገት እ.ኤ.አ. 2018 መጋቢት ወር ውስጥ ሁኔታው ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር

ዶ/ር አቢይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት ምክንያት በእጅጉ ተለውጧል፡፡ ይህም ሁኔታ ህዝቡ በይፋ አንድ ስለሆነች፣ ዲሞክራቲክ እና የለማች ኢትዮጵያን ለማየት መዘመር እንዲጀምር ሁኔታዎችን ሊፈጠር

ችሏል፡፡

በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ አንድነቷ የተጠበቀ፤ ዲሞክራቲክ የሆነች፤ ክብሩ የተጠበቀ ሕዝብ የሚኖርባት አገር ለማድረግ የሚያስችል፤ ፖለቲከኞችና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ አንድ መፍትሔ ሀሳብ በመነሻነት ለመወያየት የሚያግዝ ዉጥን ሀሳብ ለማቅረብ ጊዜው መሆኑን በመረዳታችን በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ዘጠና አምስት (95) ገጽ ያለው “Proposed New Ethiopian Government Administrative Boundary System For Unified Nation Building” በሚል ርዕስ የጥናት ጽሑፉ በነሐሴ ወር2010 ዓ.ም. አቅርበናል፡፡

ይህ ጽሑፍ በሀገሪቱ ውስጥ ፈጣንና ተለዋዋጭ የፖለቲካ ሁኔታን በማገናዘብ በፍጥነት የተዘጋጀ ነበር፡፡ ጽሑፍን ስናዘጋጅ በእጃችን ያሉትን መጽሐፍት ሁሉ ለማየት ሞክረናል ቀሪዎቹን ክፍተቶች ለመሙላት የኢንተርኔት ድህረ ገፅን ተጠቅመናል፡፡ ጽሑፉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተዘጋጅቶ ስለቀረበ ሰዋሰዋዊ እና የሀሳቡ አቀራረብ ተከታታይነት ውስጥ ስህተቶች እንደሚኖሩ እናምናለን፡፡አንባቢያን ሀሳቡ ከዘርና ከጎሰኝነት የጸዳ አስተዳደራዊ ክፍፍል ለመገንባት እንደ አንድ አማራጭ የቀረበ፤ በተለያዩ ሕዝቦች መካከል በሰላማዊ ሁኔታ የመኖር እና አንድነቱን የጠበቀ ሀገር ግንባታን ግምት ዉስጥ በማስገባት የቀረበ እንደሆነ

ተገንዝባችሁ ሀሳቡን እንድታበለጽጉት እናሳስባለን፡፡ ሙሉ ሀሳቡን ለማግኘት “Proposed New

page2image25176

Page 2 of 12

page3image408

Ethiopian Government Administrative Boundary System For Unified Nation Building” በሚል ርዕስ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተዘጋጀዉን የጥናት ጽሑፉ እንድታነቡ አንመክራለን፡፡

“ያለውን የወረወረ ፈሪ አይባልም”

መልካም ንባብ!

እንግዳሸት ቡናሬ ሽፈራዉ ሉሉ

page3image4208

Page 3 of 12

የጽሑፉ ዋና ፍሬ ሀሳብ ባጭሩ

የዚህ ጥናት ጽሑፍ ዓላማ (የተዋሐደች ኢትዮጵያን ለመገንባት አዲስ የመንግሥት የአስተዳደር አካባቢዎችን ለመወሰን የሚያስችል ውጥን ሀሳብ) እና ዋንኛ ሀሳብ የሀገሪቱን ታሪካዊ፤ ሕጋዊና የአገር ዉስጥ የአገዛዝ/የአስተዳደር ስርዓትን በመገምገም፣ አሁን ያለው በቋንቋ እና በዘር ላይ የተመሠረተውን

page4image3184

የወሰን አከላለልና የዘርና የጎሳ ፖለቲካ በሀገሪቱ ውስጥ በተለያዩ ክልሎች እና የዘር-ጎሳ-ቡድኖች ውስጥ ያስከተለውን ችግሮች በዘላቂነት ሊፈታ የሚያስችል የአስተዳደራዊ የወሰን አከላለል መሠረተ ሀሳብ ለማቅረብ ነው፡፡

የሀገር ግንባታ ስለ ታሪክ፣ ባህል፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት እና በትኩረት ማየትን ይሻል፡፡ እንዲሁም ሕዝብን የሚያስተሳስሩና አንድ የሚያደርጉትን፤ ዲሞክራሲንና የህግ የበላይነትን ለማዳበር፤ በእኩልነት እና የሕዝቦችን ክብር ለማረጋገጥ፤ እርስ በርስ የሚያያይዙትን ጉዳዮች መለየት ያስፈልጋል፡፡

ሕዝብ/ሀገር ለአስተዳደራዊ ዓላማ ሲባል የውስጥ ክፍፍልን ሊያደርግ ይችላል፡፡ እነዚህ የተከፋፈሉ የአስተዳደር አካባቢዎች፤ የራስ-ገዝ ፌዴራላዊ ወይም የተዋሐዱ ግዛቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አስተዳደራዊ

ክልሎችን በዘር፣ በቀለም፣ በአይነት ወይም በሃይማኖት ልዩነት ላይ ተመስርቶ መከፋፈልና ማስተዳደር አገርን ከሚያዳክሙ / ከሚያፈርሱ ቁልፍ ምክንያቶች ዋንኛዎቹ ናቸው፡፡ እነዚህ ሕዝብን የሚለያዩ ምክንያቶች ለህዝቦች አንድነት እና ልማት ሲባል ሀገርን በሚያስተሳስሩ ምክንያቶች/ዘዴዎች መተካት አለባቸዉ፡፡

ክልላዊነትና ብሔረተኝነት የፖለቲካ ፅንሰ ሀሳብ ሲሆን ክልላዊ ፍላጎቱን ለመጠበቅ በሚል ክልላዊ ግዛቶችን ለመፍጠር ወሰንን ከፖለቲካ ሁኔታ ጋር ለማያያዝ የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፡፡ በአጠቃላይ ክልላዊነት እንደ ማህበረሰብ፣ ቋንቋ፣ ቀለም ወይም ባህል ያሉ አንዳንድ ማህበራዊ እና ባህላዊ ባህሪዎችን መሠረት ያደርጋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የአካባቢ መሪዎች / ፖለቲከኞች ይህንን ሃሳብ ለዘር ለሉኣላዊነት፤ ለከፍተኛ የፖለቲካ ስልጣንና፤ የኢኮኖሚ የበላይነትን ለማግኘት ይጠቀሙበታል፡፡ በዚህም ምክንያት የችግር

መንስኤ ይሆናል፡፡
ምንም እንኳን ዓለምአቀፋዊነት / ግሎባላይዜሽን እና ዘመናዊነት በሰፈነበት ዓለም ውስጥ ያለን ቢሆንም ፤

ክልላዊነትና ብሔረተኝነት በመላው ዓለም፤ ማለትም ባደጉትና በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ውስጥ በስፋት ይታያል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ክልላዊነት የአከባቢያዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮችን በመፍታት ረገድ ሊረዳ ይችላል፤ ነገር ግን በአጠቃላይ በሀገር ግንባታ ሂደትም ሆነ በብሔራዊ ውህደት

ውስጥ ትልቅ እንቅፋት ነው ፡፡

ያለፉትን 27 ዓመታት ዘርን መሠረት ያደረገ ፖለቲካ እና አስተዳደር፤ ዘርን መሠረት ያደረገ ጥላቻ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በስፋቱና በብዛቱ የመጀመሪያ የሆነውን ግጭቶች ሊያስከትል ችሏል፡፡ ያለፉትን 27 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ከዘረኛነት ለመማር የቤተ ሙከራ ዓመት አድርገን ልንወስደው ይገባል፡፡ ምንም እንኳን በራሳችን ላይ መሞከር ባይመከርም፣ ድርጊቱ አንዴ የተፈጸመ በመሆኑ ያለፈውን መለወጥ አንችልም፣ ይህን ችግር ለወደፊቱ ለመለወጥ መስራቱ ብልህነት ነው፡፡ የሚከተለው የአማርኛ ምሳሌያዊ አነጋገር ለትምህርት ሊሆነን ይችላል፤

“ሞኝ በራሱ ይማራል፤

ብልጥ ግን ከሌላው ይማራል፡፡Page 4 of 12

page4image22832

ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን ከስህተቶች ለመማር እና የማስተካከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ አልዘገየም፡፡ ከኢትዮጵያውያን ቤተ ሙከራ በግልጽ መረዳት የተቻለዉ ዘርን መሰረት ያደረገ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዋናው የሰላምና የእድገት እንቅፋትና የማይበጅ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል አንድነትን፣ ብልጽግና እና መተማመንን የሚያመጣ መንገድ መፍጠር ይገባል፡፡ አንደኛው መንገድ የአስተዳደር ወሰኖች ዘርን መሰረት ያላደረጉ መስፈርቶች ላይ እንዲመሰረት ማድረግ ነው፡፡

አሁን ያለው ህገ-መንግሥት እንደሚገልጸው የሉዓላዊነት መሰረት የተጣለዉ “በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች” ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራል ስርዓቱ የዘር መለያዎችን እንደ እውነተኛ የአስተዳደር ቅርጽ እና አስተዳደራዊ አካላትን ለማደራጀት መሰረታዊ አሰራርን ይቀበላል፡፡

በዚህ መሠረት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ለማስከበር በወጣው “የብሔራዊና ክልላዊ መንግሥታት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 7/1992” አዋጅ ታውጇል፡፡

በሽግግር ወቅት የተመሰረቱት ዘጠኝ ብሔራዊ ክልሎች ራሳቸውን የሚያስተዳድሩት በአዲስ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (የአንቀጽ 46 (1)) ውስጥ የተካተቱ ናቸው፡፡ እነዚህ ክልሎች-1 / የትግራይ ክልል፣ 2) የአፋር ክልል፣ 3) የአማራ ክልል፣ 4) የኦሮሚያ ክልል፣ 5) የሶማሌ ክልል፣ 6) የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ 7) የደቡብ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፣ 8) የጋምቤላ ህዝቦች፣ 9) የሐረሪ ክልል(አንቀጽ 47፤ (1)፤ (1-9)).

እንዲህ ዓይነቱ የክልል ወሰን አደረጃጀት፣ በአሁን ጊዜ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ፈጥሯል፣ ለምሳሌ፡-. በኦሮሞ እና በሶማሌ፤ በኦሮሞ እና በአማራ፤ በኦሮሞ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና በአማራ፤ በትግራይ እና በአማራ ክልል መካከል የሚደረጉ የዘር ግጭቶችን፣ ወዘተ … በተጨማሪም በክልሉ ውስጥ ማለትም በሲዳማ እና በወላይታ፤ በጉራጌ እና በቀቤና ፤መካከል የተደረጉ በዘር ላይ የተመሰረቱ ግጭቶችን አስከትሏል፡፡

የወደፊቱን የአገሪቱን ሁኔታ ለማሻሻል ከታሪክ በመማር፣ ታሪክን እና ያለፉትን ክስተቶች የመማሪያ መሣሪያ አድርገን መጠቀም አለብን፡፡ ታሪክን እና በኢትዮጵያዊያን መካከል ያለውን የአንድነት መሠረቶችንና

እሴቶችን ችላ ማለት በአሁኑ ጊዜ የምንመለከተውን በቋንቋ ላይ የተመሰረቱ የክልሎች አስተዳደራዊ ወሰኖችና ተዛማጅ ግጭቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ አድርጎ ልማትን በፕሮግራም እና በፕሮጀክት በቅደም ተከተል መርሃ ግብሮችን አቅዶ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ ካለምንም የጥቅም ግጭት ለማልማት ከተፈለገ አሁን ካለዉ በቋንቋዎች

ላይ የተመሠረተ የአስተዳደር ስርዓት መላቀቅና አዲስ ሀሳብ ማፈለቅ ግድ ይላል፡፡ ይህ እርምጃ ብሔራዊ ጥቅምን ለማግኘት እና የህብረተሰቡን ፍላጎቶች ያለጎሳ ግጭት ለማሟላት ጥርጊያ መንገድ ይከፍታል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በዘር ላይ የተመሰረተዉ የአስተዳደር ወሰኖች እና ፍትሃዊ ያልሆነ እና የማያስተማምን የፖለቲካ ስርዓት ለረጅም ጊዜ ዘላቂነት ያለው ልማትን አያመጣም፣ ለኢንቨስትመንት የተመቻች ሁኔታ እንዳይኖር ያደርጋል እንዲሁም የህብረተሰቡን በነጻነት ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመስራትና የመዘዋወር ነጻነትን ያግዳል፤ ሲያግድም በተግባር አይተነዋል፡፡ የተገነቡ መሠረተ ልማቶችና የኢንቨስትመንት ተቋማት ሲወድሙ ተመልክተናል፡፡

ኢትዮጵያ በታሪኳ ውስጥ የዘር አስተዳደር ተግብራ አታውቅም፡፡ ይህ የራሱ ታሪካዊ ዳራ አለው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምናስታውሰው ኢትዮጵያ እግዚአብሔር የሰውን ዘር ፈጠሮ ካስቀመጠባት የገነት

page5image22920

Page 5 of 12

አካባቢ አንዷ ናት (ዘፍጥረት ምዕራፍ 2)፡፡ ከጥንታዊው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዘመን ጀምሮ በባቢሎን (ባብኤል) ወይም በሰናዖር (ሜሶፖታሚያ) ከተመሠረተው የመጀመሪያው የካም (ኩሽ) ስልጣኔ

እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ወደያገሩ ከበተነበት ከ4000 ዓመታት ያህል ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ የተለያዩ ሕዝቦች የሰፈሩባት ከስልጣኔ ጀማሪዎች አንዷና ለዓለም ስልጣኔን ካስተዋወቁ አገሮች አንዷ ናት፡፡ እንዲያውም ኢትዩጵያ የሚለው ስያሜ ከአፍሪካ እስከ ሕንድ ድረስ ያለውን አካባቢ ለማመልከት

ይጠቀሙበት እንደነበር የታሪከ ጸሐፍት ያስረዳሉ፡፡ የኢትዮጵያ አቀማመጥ አፍሪካን፣ ኤሲያን እና አውሮፓን በሚያገናኘው መስመር ላይ በመሆኑ የተለያየ ማንነት ያላቸው ሰዎች እንዲደባለቁ የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ በምስራቃዊ አፍሪካ የነበረው የጥንት ስልጣኔ በርካታ የተለያዩ ሕዝብን ለንግድ፤ ለወዳጅነት፤ ለወታደራዊ የበላይነት በመሳቡ የሁሉም ዓለም ሕዝብ ለመደባለቅ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያ የሁሉም አይነት የህዝብ ዝርያ ውህድ ስለሆነች ማንም ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ የተለየ ማንነት ወይም የዘር ግንድ ሊጠቀስ አይችልም፡፡ ኢትዮጵያ በሺዎች አመታት መካከል በተለያዩ ሕዝብ መካከል በተደረገ መዋሐድ የተፈጠረች አገር ናት፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሰዎች ከሚናገሩባቸው የተለያዩ ቋንቋዎችና ለጎሳቸው/ለብሔራቸው በሰጡት ስያሜ ካልሆነ በስተቀር አንዳቸውም የተለየ የዘር ግንድ ማበጀት አይችሉም፡፡ ለዚህ ነው ለአትየጵያዊያን፤ ኢትዮጵያዊነት ልንገልጸው የማንችለው የውስጥ ነገር

የሚሆንብን፡፡

በታሪክ ሂደት ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝቦች እርስ በርሳቸው የተደባለቁ፤ አንድ ላይ ተባብረው የሚኖሩ፤ በችግሮች ጊዜ አንድ ላይ ሆነው ሐዘናቸውን የሚገልጹ፤ ሀገራቸውን በጋራ ሲከላከሉ የኖሩ ወዘተ … ልዩ ልዩ ተወራራሽ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ያላቸው፤ተመሳሳይ ባህላዊ ሕግ ያላቸው፤ ተመሳሳይ ዓይነት

የአኗኗር ዘይቤ ያላቸው፤ ወዘተ … ለዓለም ቴክኖሎጂን ካስተዋወቁ የዓለም ሕዝቦች አንዷ ናት፡፡ የሌላው ዓለም ህዝብ እንኳን ኢትዮጵያን የስልጣኔና የሰው ዘር መነሻ እንደሆነች ያስባሉ፡፡

ብናምንም ባናምንም እግዚአብሔር/ፈጣሪ አለ፤ የፈጠረንም ያኖረንም እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን በተወሰነ ቦታ እንድንኖር እና እንድናገለግል እድል ሰጥቶናል፡፡ እያንዳንዳችን በኢትዮጵያ ውስጥ የተወለደነው ለምንድን ነው? ለምን በአውሮፓ፤ በእስያ ወይም አሜሪካ አልተወለድንም? ይህ አጋጣሚ አይደለም፡፡ ማናችንም የትውልድ ቦታችንን እና የእኛን ጎሳዎች ወስነን አልተወለድንም፤ ማንም

ሰው የትውልድ ቦታው በአዲስ አበባ፤ ነቀምት ወይም አዋሳ፤ ወዘተ … እንዲሆን ወስኖ አልተወለደም፡፡ ማንም ሰው ከኦሮሞ፤ ዶርዜ፤ ሶማሌ ወይም ወዘተ … ለመወለድ አልመረጠም፡፡ የእያንዳንዳችንን የትውልድ ስፍራ የመወሰን የእግዚአብሔር ሥራ ነው፡፡ እግዚአብሔር እኛ ኢትዮጵያ ውስጥ እንድንወለድ እድል የሰጠንየኢትዮጵያንሕዝብለማገልገል እንጂእንድንከፋፍለውአይደለም፡፡ከ80በላይየሚሆኑቋንቋዎች

ቢኖሩም እግዚአብሔር እኛን እንደ ኢትዮጵያዊ ያውቀናል፡፡ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ የመወለድ እድል ሰጥቶናል፤ ኢትዮጵያውያን ለመሆን፤ እንደ ኢትዮጵያውያን ለመኖር እና ኢትዮጵያውያንን ለማገልገል እድል ሰጥቶናል፡፡ ይህ አንዱ የአንድነታችን መሠረት ነው፡፡

ኢትዮጵያ በመንግሥት ከተደራጁና፤ ነገሥታትና ወታደራዊ ሀይል ከነበራቸው ቀደምት መንግሥታት አንዷ ናት፡፡ ነገሥታት ለኢትዮጵያ አንድነት አገልግለዋል ብዙ ዋጋም ከፍለዋል፡፡ ከመንግሥት ሥልጣን ወይም ታላቅነት ጋር በተዛመደ ልዩነት ቢኖራቸውም እንኳን በኢትዮጵያዊ ማንነታቸው ላይ ጥያቄ ኖሯአቸው አያውቁም እንዲሁም በቋንቋ ማንነት ላይ ተመስርተው አያውቁም፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝቦች አንድነትና ለወሰኗ ብዙ ተዋድቀዋል፡፡ በቅርቡ ያለውን ታሪክ ከተመለከትን ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ፤ በጎጃም ንጉሥ ተክለኃየማኖት፤ በቤጌምድር ራስ ጉግሣ ወሌ፤ በትግራይ ራስ መንገሻ

ሥዩም፤ በወሎ ራስ ሚካኤል፤ በነቀምት ደጃዝማች ኩምሣ ሞረዳ (ገብረእግዚአብሔር)፤ በቀሌም ወለጋ (ሌቃ ቄሌም) ደጃዝማች ጆቴ ቱሉ፤ በጂማ፣ ጂማ አባጂፋር፤ በቤንሻንጉል ሼክ ሆጅል አል ሁሴን፤

page6image25936

Page 6 of 12

በወላይታ ንጉሥ ጦና፤ በሀረር አሚር አብዱላሂ፤ በአፋር ሡልጣን አሊሚራህ፤ በከፋ ንጉሥ ጋሊቶ ወዘተ.. በዚህ ዝርዝር ዉሰጥ ያልገቡ ንጉሦችና የአካባቢ መሪዎች ነበሩን፡፡ እነዚህ ነገሥታት እና ዘሮቻቸው ለኢትዮጵያ አንድነት ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ይህም ለአንድነታችን አንዱ መሠረት ነው፡፡

ስለሆነም ከብሔር/ዘር አስተሳሰብ ሳጥን ውስጥ በመዉጣት የሕዝብን ክብር ለመጠበቅ፣ የዲሞክራሲ

ሥርዓትን ለማስፈን፣ የህግ የበላይነት እና ህጎችን መሰረት በማድረግ የሚኖር ትውልድ ለመቅረጽ እና የበለጸገች ሀገርን ለመገንባት ታላላቅ ሃሳቦችን እና አማራጭ መንገዶችን ለማየት መሞከር አለብን፡፡ ታሪክ እንደሚያስተምረን ባለፉት 27 ዓመታት ካልሆነ በስተቀር ኢትዮጵያ በቋንቋዎች አስተዳደራዊ ስርዓት ላይ ተመስርታ አታውቅም፡፡ በታሪክ ውስጥ ያለው አስተዳደራዊ ስርዓት ፖለቲካዊ እና ጂኦግራፊ / አካላዊ ወሰኖችን ያካትታል፡፡ ያለፉት አከላለሎች የንጉሦችን፣ የመሳፍንቱንና፣ መኳንንቶች/በባላባቶች ሥልጣን/ኃይልን መሠረት ያደረገና እንዲሁም በጂዮግራፊ ወይም በአካላዊ ወሰኖች የተመረኮዘ እና አካባቢያቸውን ከጠላት ለመከላከል አመቺ በሆነ መንገድ ነበር፡፡

ከዘር-ቋንቋ ፌዴራሊዝም ስርዓት በፊት ዘመናዊ ታሪካችን እንደሚያመለክተው አስተዳደራዊ ክልሎች ታሪካዊ ክስተቶችን፣ አካላዊ እና ጂኦግራፊያዊ ድንበሮችን ያካትታሉ፡፡ ለስተዳደራዊ ክልሎች የትውልድ ቋንቋ መስፈርት ሆኖ አያውቅም፡፡ እያንዳንዱ የአስተዳደር ክልል የተለያዩ የጎሳ-ቋንቋ ማህበረሰብን ያካተተ ነበር፡፡

በዘር ላይ የተመሰረተ የፖለቲካን በሽታ በአንድ አይነት መድኃኒት ማከም አይቻልም፡፡ ማለትም የዘር

ፖለቲካን በሽታ በዘር ፖለቲካ መድሃኒት ማከም አይቻልም፤ ምክንያቱም የዘር ፖለቲካ በሽታ /ባክቴሪያ/ረቂቅ ሕዋሳት የዘር መድሃኒትን በመላመዱ ምክንያት ሊፈውሰው አይችልም፡፡ ይህም የሆነው ባለፉት 40 አመታት ውስጥ በዋነኝነት በማርክሲስት ሀሳብ ላይ የተመሰረተው የጎሳ-ፖለቲካ በተለዬ ሁኔታ /በአሰገራሚ ሁኔታ/ በሀገራችን በመተግበሩ ሕመምተኝነታችን ወደ አፓርታይድ አስተሳሰብ በማሳደጉ ነው፡፡ ይህንን ጥልቅ የሆነና ሥር የሰደደ የጎሳ/ዘር ስርዓትን ለማስወገድ እና ኢትዮጵያን ማንም ሊያስተዳድራቸው ወደማይችልበት አነስተኛ ግዛቶች እንዳትበታተን ለመከላከልና መከፋፈልን ለመቀነስ፣ የአገራችን የአስተዳደር ግዛቶችን አደረጃጀት መለወጥ እና አሉታዊ ተፅእኖን ማስወገድ ይኖርብናል፡፡

ይህ ጽሑፍ በአገራችን ውስጥ ለወሰን ግጭትና ብጥብጥ መሠረት የሆኑትን ጠባብ አክራሪ ዘረኝነትን /ብሔረተኝነትን/ ለማስወገድ ለወሰን ማካለል የጂዮግራፊያዊ ክልል መሰረታዊ መርሆችን ጥሩ አማራጭ አድርጎ ወስዷል፡፡ የጂኦግራፊያዊ ክልል መሰረታዊ መርሆዎችን ከወንዞች የተፋሰስ ወሰኖች /ከሃይሮሎጂክ ወሰኖች/ ጋር በጣምራ የአስተዳደራዊ ወሰኖችን ለማካለል ሥራ ላይ ብናውል ተፈጥሯዊ ድንበር/ወሰን በመሆኑ ምክንያት ዘርን መሠረት ስለማያደርግ በወሰኑ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዬ ህዝብ ብዘሀነትና

ብሔራዊነት በእኩልነት ለማክበርና ለማስተዳደር ይረዳል፡፡

ኢትዮጵያ ታላላቅ የተፈጥሮ ስጦታ ያላት አገር ናት፡፡ እነዚህም ታላቅ የኢትዮጵያ ተፈጥሮአዊ ስጦታዎች አገሪቱን በሁሉም ሥፍራ የከፈሉ የተለያዩ የሃይሮሎጂክ /ተፋሰሶች/ ክልሎች አሏት፡፡ እነሱንም

ለአስተዳደራዊ ግዛቶች መጠቀም ይቻላል፡፡ ስለሆነም በተለያዩ የዘር ግዛቶች የዘር ግጭቶችንና አለመተማመንን ለማስወገድ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ወደ ልማትና ውህደት ለማሳደግ አካባቢያዊ የአስተዳደር ወሰኖችን በሃይሮሎጂክ /የወንዞች ተፋሰስ/ ወሰኖች መሠረት ማድረግ የተሻለ ሞዴል እንደሆነ እናምናለን፡፡ በመሆኑም አሁን ያሉትን የዘር ግዛቶች አስተዳደራዊ ወሰኖችን እና ተዛማጅ ግጭቶችን ለማስወገድ፣ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የኢትዮጵያ መንግስት መዋቅር እና የአስተዳደር ክፍፍሎችን

page7image23232

Page 7 of 12

በመለወጥ የአካባቢ አስተዳደር ስርዓቱ በሃይሮሎጂክ /ተፋሰሶች/ አካባቢያዊ አስተዳደሮችን መሠረት ያደረገ እንዲሆን አማራጭ የመፍትሄ ሀሳብ አቅርበናል፡፡

የዚህ ዓይነቱ አስተዳደራዊ የወሰን አከላለል የውኃን እና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶችን በአግባቡ በዘላቂነት ለማልማት ማለትም፤ ለማቀድ፣ ለመተግበር እና ለማስተዳደር፣ የሀብት አመዳደብን ያለ ጥቅም ግጭት፤ የፕሮጀክት እና ፕሮግራሞችን ቅደም ተከተል ከግምት ውስጥ በማስገባት ሰላማዊ የልማት ሁለገብ ተሳትፎን ለማሻሻል ይረዳል፡፡

እንዲህ ዓይነቱ አሠራር የማህበረሰቦችን ፍላጎት በእኩልነት ካለጎሳ ግጭት ፍትሃዊ በሆነ ስርዓት ከሀገራዊ ጥቅም ጋር በተጣጣመ መልኩ የአሁኑን ህብረተሰብ ፍላጐትን እና የመጪው ትውልድ ፍላጎት ሳያስተጓጉል ሁሉን ያካተተ መንገዶችን ያመቻቻል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን ስምንት የወንዝ ተፋሰስ ግዛቶች ለተሻለ ልማት / ስልጣኔና ለሀገሪቱ ትልቅነት እና ብሔራዊ ውሕደትን በተሻለ ሁኔታ ለማራመድ ሀሳብ ቀርቧል፤

1) የአባይ ተፋሰስ ግዛት፣

2) አዋሽ፤ አይያሻ እና ደናከል ተፋሰስ ግዛት፣3) የባሮ-አኮቦ ወንዝ ተፋሰስ ግዛት፣
4) የገናሌ-ዳዋ ተፋሰስ ግዛት፣

5) ተከዜ እና መረብ ተፋሰስ ግዛት፣
6) ዋቢ-ሸበሌ እና ኦጋዴን ተፋሰስ ግዛት፣
7) የኦሞ-ጊቤ ተፋሰስ ግዛት፣ እና
8) የስምጥ ሸለቆ ሃይቆች ተፋሰስ ግዛት ናቸዉ፡፡

እነዚህ ተፋሰሶች አገሪቱን ለማስተዳደር በሚያመች ሁኔታ መከፋፈላቸውን በሚቀጥሉት ምስሎች ላይ መመልከት ይቻላል፡፡

page8image12408

Page 8 of 12

page9image528

ምስል-1 የኢትዮጵያ የወንዝ ተፋሰሶች

page9image1424

ምስል-2 በመፍትሄ ሀሳብ መሰረት የቀረበዉ የወንዝ ተፋሰስ የአስተዳደር ግዛቶች

page9image2360

Page 9 of 12

ከዚህም በተጨማሪ በተመሳሳይ አስተዳደር አካባቢ ወሰን ውስጥ የሚፈጠሩ ንዑስ የአስተዳደር ወሰኖችና የሃይድሮሎጂክ ክፍሎችን በተቀናጀ የወንዝ ተፋሰስ መርሃ ግብር ለመተግበር አግባብነት ያላቸው አደረጃጀቶችን ለመፍጠር ይረዳል፡፡ እንዲሁም ንዑስ ተፋሰሶችን፤ ዞኖችን፤ ወዘተ… ለመከፋፈልና ለተፋሰሱ የልማት ስትራቴጂዎች/ስልቶች እንደአስፈላጊነቱ ለመቀየስ ይጠቅማል፡፡

የፌዴራል መንግስቱ በወንዝ የተፋሰስ ግዛቶች መካከል የሚኖረውን የሀብት አለመመጣጠንና እና የተፈጥሮ ሀብትን ሚዛን ለመጠበቅ እና እንዲሁም የብሔራዊ የልማት ዕቅድ ትግበራን ተከትሎ የሀገሪቱን ፍላጎት በማገናዘብ ተግባራዊ ለማድረግ ይረዳዋል፡፡ እንደዚህ ያሉ የተፋሰስ የአስተዳደር ግዛቶች ከዘር/ብሔር ጋር የተያያዙ መሰናክሎችን እና ችግሮችን ያስወግዳል እንዲሁም ከዘር/ብሔር ላይ ከማተኮር ይልቅ ለፖለቲካ እና ለኢኮኖሚ ዉጤታማነት/ስኬት አመቺ ሁኔታን ይፈጥራሉ፡፡

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አ.አ.ድ.) በተቋቋመበት ጊዜ ኢትዮጵያ ከመስራች አባላት እና ዋነኛ ተዋናዮች

አንዷ እንደሆነች ታሪክ ይነግረናል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የወንዞች ተፋሰስ ወሰን አከፋፈል የሚለው ሀሳብ፣ ተመሳሳይ የአስተዳደር ክልል/ወሰን ችግር ላለባቸው የአፍሪካ ሀገራት አስተዋፅኦ ያበረክታል፤ እንዲሁም በአፍሪካ ሕብረት (አ.ሕ.) አህጉራዊ አንድነት፣ የኢኮኖሚ ትስስር/ትብብር እና ነጻ የአፍሪካ ቀንድ ሕዝቦች

ዝዉዉርን በማሳካት ረገድ ኢትዮጵያ ተመሳሳይ የመሪነት ሚናን እንድትጫወት ታሪክን ለመድገም ዕድል ይሰጣል፡፡

ለዉጥን ለመቀበል ብዙውን ጊዜ ሰዎች ይቸገራሉ፣ አስፈላጊ መሆኑን ቢረዱም ደኅንነት አይሰማቸዉም፡፡ ብዙውን ጊዜ መልካም ሕጎች ወይም የተሻሻሉ አካሄዶች በባለስልጣኖቻቸው ወይም በዜጎች ተገቢዉን ግንዛቤ ካላገኙ/ ካልተረዱአቸው ወይም ተቀባይነት ከሌላቸው የታሰበዉ ዉጤት ላይገኝ ይችላል፡፡

እያንዳንዱ አገር ተሃድሶን እንዴት እንደሚያስፈጽም የሚወስነው አሁን ካለው ሁኔታ እና ለወደፊቱ ምን ማሻሻያ ማድረግ እንዳለበት ከሚለዉ ቢሆንም፤ በተቀናጀ የዉሃ ሀብት አስተዳደር ትግበራ የተገኙ ልምዶች አንዳንድ መሰረታዊ አቅጣጫዎችን ያሳያሉ፣

የተሃድሶ እንቅስቃሴዎች በተቀናጀና በተዋሃደ መንገድ እና ከሀገሪቱ ሰፋ ያሉ የማህበራዊ እና የፖለቲካ ፖሊሲዎችን አጣጥሞ ማከናወን አለበት፣

 ግንዛቤ ማሳደግ፣ መረጃዎችን ማካፈል እና ትርጉም ያለው አሳታፊ ክርክር የማንኛውም የማሻሻያ ሂደት ቁልፍ ነገሮች ናቸው፣

እንዲሁም የውሃ አስተዳደር ለውጦች በውኃ ዘርፍ ብቻ የተገደቡ ሳይሆኑ፣ ነገር ግን ተፅእኖ

በሚያስከትሉ እና በውሃ የውሳኔ አሰጣጥ ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ ሌሎች ዘርፎችን ከግምት ውስጥ ማስገባት ናቸው፡፡

የቀረበው በወንዝ ተፋሰስ ላይ የተመሠረተ የአስተዳደር ወሰን ውጥን ሀሳብ ብሔራዊ ትስስር እና ዉህደትን ከማመቻቸቱ በተጨማሪ ለሀገሪቱ የሚከተሉት ጥቅሞች ይኖሩታል፣

❖ከብዝሃነት እና ከአንድነትጋር የተያያዙት ችግሮች መፍትሔ ያገኛሉ፣
❖ ብዝሃነት እና ዜግነት ሁለቱም የተከበሩ እና በዘር ልዩነት ላይ የተመሠረተ ግጭት

ይቀነሳሉ/በሂደትም መፍትሔ ያገኛሉ፣

❖ በዘር ላይ የተመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አያበረታታም፣

❖የዜጎች መብት፤ የስራ፣ የኢንቨስትመንት እና ሌሎች ፍላጎቶችን ለማሟላት፤ በሀገሪቱ ውስጥ ሁሉ ምንም ዓይነት የጎሳ እና የጂኦግራፊያዊ ድንበር/ወሰን መሰናክል ሳይኖር ያስከብራል፣

page10image23104

Page 10 of 12

❖ በተፋሰስ ዉስጥ በውሃ ፍትሃዊ አከፋፈል እና በፕሮጀክቶች ቅደም ተከተል አሰጣጥ መካከል የሚነሱ ግጭቶች አስተዳደራዊ መፍትሄ ያገኛሉ፣

 የኢንቨስትመንት ዋስትና ይሻሻላል፣

❖ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ደህንነት ያድጋል፣
❖ በአየር ሁኔታ ላይ የተመሠረቱ የግብርና ልማት ዞኖች ሊቋቋሙ ይችላሉ፣
❖ በብሔራዊ ጥቅም እና የልማት ዘላቂነት ዋስትና ለማረጋገጥ ይረዳል፣
❖ለሀገራዊ የልማት እቅድ፣ ለክልል ዕቅድ እና ለተቀናጀ የውሃ ሀብት ልማት ዕቅድ ስትራቴጂ

/ስልት ያለተግዳሮት በታችኛው እና በላይኛዉ ተፋሰስ አካባቢ የሚገኙትን ሁሉ በተስማማ ሁኔታ ተጠቃሚ አድርጎ ለማስተዳደር ይረዳል፡፡

❖ የተቀናጀ ፕሮግራም ይከናወናል፣ የሃብት ምደባና አጠቃቀም ውጤታማነት ይሻሻላል፣ አላስፈላጊ የተደጋገሙ የልማት ጥረቶች እንዳይኖሩ ያደርጋል፣

❖በተፋሰስ ወሰን አስተዳደር ግዛቶች ውስጥ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የወንዞችን ተፋሰስ በሙሉ ለማቀድ፣ ለማልማትና ለማስተዳደር፣ የወንዝ ተፋሰስ ድርጅቶች ሊቋቋሙ ይችላሉ፣

❖ለአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 አህጉራዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውህደት ከጎረቤት አገራት ጋር ለማድረግ መንገድ ይጠርጋል፡፡

ላለፉት 27 አመታት የተገበርነው የፌዴራል ስርዓት የዘር መለያዎችን እንደ እውነተኛ የአስተዳደር ቅርጽ እና አስተዳደራዊ አካላትን ለማደራጀት መሰረታዊ አሰራርን በመከተል ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ አስተዳደራዊ መዋቅር በኢትዮጵያ ታሪክ፣ ተፈጥሮአዊ/ አካላዊ ወሰኖች እና በኢትዮጵያ ህዝቦች አንድነት ላይ የተመሠረተ አልነበረም፡፡ በውጤቱም በሰዎች መካከል የማያቋርጥ ግጭትን ፈጥሯል፡፡

የውጥን ሀሳቡ /የፕሮፖዛሉ/ መነሾ የኢትዮጵያን ታሪክ በጥልቀት በመገምገም፣ እንዲሁም በወቅታዊ የፖለቲካ እና የአስተዳደር ስርዓት ውስጥ ግጭቶችን እና ምክንያቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነዉ፡፡ ይህ ውጥን ሀሳብ /ፕሮፖዛል/ ለኢትዮጵያ ህዝብ የቀረበው አሁን ካለው ለውጥ ጋር በተጣጣመ መልኩ የተሻለ የወደፊት የመንግሥት የአስተዳድር ከፍፍልን በተመለክተ እንዲያወያይ ነው፡፡ ስላለፉት ስህተቶች ብቻ አስተያየት መስጠት የተሻለ ጊዜ እንደማይመጣ እናምናለን፣ ካለፈው ጊዜ በመማር እና ለወደፊቱ የሚሆን የተሻለ ሀሳብ በማቅረብ የተሻለ ጊዜን መፍጠር ይቻላል፡፡

የቀረበው ውጥን ሀሳብ /ፕሮፖዛል/ የሚመለከተውን የህገ መንግስት፣ የመንግስት አስተዳደር ስርዓት እና

የተቀናጀ የወንዝ ተፋሰስ አስተዳደርን በመገምገም ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ሃይድሮሎጂካል ድንበር/ወሰን ዉስጥ የተለያዩ ሰዎች፣ ውሃ፣ ማዕድን፣ ተክሎች እና የእንስሳት ሀብቶችን ወዘተ… ያካትታል፡፡ በዚህ አካባቢያዊ ወሰን ውስጥ ያለውን ሀብት ለማልማት እና በእኩልነት ለማስተዳደር እጅግ በጣም ተስማሚ

የሆነ ተፈጠሮአዊ ወሰን ነው፡፡ የሃይድሮሎጂ ወሰን ዘርንና ቋንቋን መሠረት አያደርግም፣ በመሆኑም ፖለቲከኞች በዘር/በጎሳ/በቋንቋ በመጠቀም ጥላቻን ለማስፋፋት በዘር ልዩነት ስግብግብ የሥልጣን ማግኛ የሚጠቀሙበትን መንገድ ይዘጋል፡፡

ፓርቲዎችን በዘር፣ በሃይማኖት ወይም በቋንቋ መስመሮች ላይ ማደራጀት በጣም አደገኛ ነው፡፡ በሀገሪቱ የተከፋፈሉ እና የተበታተኑ የማይገዙ ትናንሽ ግዛቶች በአፍሪካ ቀንድ እንዲፈጠሩ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም የፖለቲካ ፓርቲዎች መደራጀት የሚገባቸዉ በፖለቲካ ሀሳብ ላይ ብቻ እንጂ በብሄር/ጎሳ ነፃነት ግንባር፣ በኃይማኖት ላይ እንዳይመሠረቱ እናሳስባለን፡፡

page11image22776

Page 11 of 12

ኢትዮጵያን ለመዋሐድ የጋራ የሆኑ፣ ታሪካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ግብረገባዊ/ ሥነ-ምግባራዊ እና ሕጋዊ እሴቶች አሉን፡፡ ስለዚህ በቅንነት በሀገራዊ የጋራ ታሪካዊ፣

ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ባህላዊ፣ ኃይማኖታዊ፣ ሥነ ምግባራዊ እና ሕጋዊ እሴቶች ላይ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ለዘላቂ ስላማዊ ልማትና፣ ለልዩነት እና ለአንድነት ትኩረት በመስጠት ለሀገራዊ ግንባታ ለሚደረገዉ ጥረት መንገድ ይጠርጋል፡፡ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የፈጠርነውን የስህተት አጀንዳ ለመዝጋት፤ የብሔራዊ ዕርቅ/ መርሃ ግብርን ተግባራዊ ለማድረግ መንገድ ይከፍታል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ የጋራ እዉቅና የተሰጣቸዉን ታሪካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ሥነ ምግባራዊ እና ሕጋዊ እሴቶችን መሰረት በማድረግ ግልጽ የሆነ የተጠያቂነት እና የኃላፊነት ሚና ያላቸዉ ተቋማትን ማቋቋም ይኖርብናል፡፡ የህግ ሥርዓቱን እና አስፈላጊ የሆኑትን የሕግ ክፍሎችን እና የአስተዳደራዊ ጉዳዮች የሆኑትን እንዲሁም የሕገ-መንግስታዊ ክፍሎች እንዲገመግሙ

ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሁሉም የልማት ዘርፎች እና ሌሎች ከተሻሻለው የሕግ ማዕቀፍ ጋር በማጣጣም ፖሊሲዎቻቸውን እና ስልቶቻቸዉን መገምገም ያስፈልጋል፡፡

ከላይ እንደተጠቀሰው የተለያዩ የአገሪቱ ነገሥታት የእትዮጵያን የአገርና የሕዝብ አንድነት በማስጠበቅ ልዩ አሰተዋጽኦ ነበራቸው፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊነታችን ለእነዚህ ነገሥታት እና ዘሮቻቸው እውቅና መስጠት ይገባናል፡፡ ኢትዮጵያውያንን አንድ በማድረግና ህዝቡን በማዋሃድ ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የእነዚህን የነገሥታት ዘሮች/ዝርያዎች እወቅና ሰጥተን እንደ አባቶቻቸው የኢትዮጵያ አንድነት እና የሕዝቡን አንድነትን ለመጠበቅ ከመንግሰት ጋር የሚሠሩበትን የመንግሥት ሥርዓት እንዲቋቋም እንመክራለን፡፡ እንደ እንግሊዝ፤ ጃፓን፤ ታይላንድ ወዘተ .. የመሳሰሉ ሀገራት ንጉሦቻቸውን እንደ ታሪካቸው ዓምድና የአገር አንድነት ተምሳሌት እውቅና ሰጥተዋቸዋል፤ እንዲሁም ለተባበረና ለበለጸገ ሀገር ምልክት ሆነው ያገለግላሉ፡፡ከታሪካችንልንማርካልቻልንቢያንስቢያንስከሌሎችልንማር ይገባናል፡፡

የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ለኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ ሀሳብ ለዉይይት ለማቅረብ እና ሕዝቡ የወደፊት

አቅጣጫውን/መንገዱን በተመለከተ በተሻለ ሀሳብ ላይ እንዲወያይ ለማድረግ ነው፡፡ ከሌሎች ወገኖች ሌሎች የመወያያ ሀሳቦች ሊቀርቡ ይችላሉ ብለን እናምናለን፤ ሆኖም ግን ይህ ያቀረብነው የመወያያ ሀሳብ /ፕሮፖዛል/ ከሚቀርቡት ሌሎች ጥሩ ሀሳቦች መካከል አንዱ ነው ብለን እናስባለን፤ በመሆኑም በአብዛኛው

ኢትዮጵያውያን ተቀባይነት እንደሚኖረው እናምናለን፡፡

እግዚአብሔር/ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ልጆችዋን ይባርክ፤ ማስተዋልንም ይስጠን!!

page12image17664

Page 12 of 12