አሜሪካ ለአባ ጅፋር ቤተ መንግስት እደሳ ድጋፍ እንደምትሰጥ ተገለጸ

አባይ ሚዲያ ዜና

የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስት ለሚደረግለት እደሳ እና ጥገና አሜሪካ እርዳታ እንደምታደርግ ተዘገበ።

ቤተ መንግስቱን ለማደስ የሚያስችል ስምምነትም በአሜሪካ ኤምባሲ እና በቅርስ ጥናት እና ጥበቃ መስሪያ ቤት እንደተፈጸመም ታውቋል።

የአሜሪካ አምባሳደር  በአባ ጅፋር ቤተ መንግስት ተገኝተው ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ ቤተ መንግስቱን ለማደስ የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱ ተዘግቧል።

ቤተ መንግስቱን ለማደስ 7 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ከአሜሪካ፣ ከኦሮሚያ ክልል እንዲሁም ከቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ቢሮ መመደቡ ተገልጿል።

የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ቤተክርስቲያንንም ለማደስ እና ለመጠገን የሚያገለግል እርዳታ የአሜሪካ ኤምባሲ እንደሚሰጥ መዘገቡ ይታወሳል።