ኢት-ኢኮኖሚ      /ET- ECONOMY

ክፍል አንድ

የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ቦርድ 6.3 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቁ 13 የኃይል ማመንጫና 3 የፍጥነት መንገዶች በአጋርነት እንዲገነቡ ወሰነ

The early bird gets the worm; the late mouse gets the cheese.  (cartoonstock.com)

‹‹የማለዳ ወፍ ትል ትለቅማለች፣ የአደረ አፋሽ አይጥ ፎርማጆ ትበላለች፡፡››

በአዋጅ የተቋቋመው የግልና የመንግሥት አጋርነት ቦርድ፣ በሰባት ሚኒስቴሮችና ከኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በተወከሉ ሁለት አባላት እንዲሁም በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ጄነራል ኃላፊ ውክልና የሚመራ ነው። የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ቦርድ፣ መንግሥት ከግሉ ዘርፍ በተለይም ከውጭ ኩባንያዎች ጋር በትብብር እንዲገነቡ በቦርድ ውሳኔ የተሰጠባቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች አብዛኞቹ በውኃና በፀሐይ ኃይል የሚመነጭ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማምረት የሚያስችሉ 13 ፕሮጀክቶች ናቸው። በተጨማሪም ሶስት የፍጥነት መንገዶችም 357 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ እንዲገነቡ ተወስይኗል፡፡  ለአስራሁለቱ  3,071 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ወጪ በ5.263  ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን፣ እንዲሁም ሦስት የፍጥነት መንገዶች 357 ኪሎሜትር መንገድ  ከ1.115 ቢሊዮን ዶላር  የሚወጡ ናቸው፡፡ በጠቅላላው የፕሮጀክቶች ወጪ በ6.378 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት እንዲገነቡ ተወስይኗል። በገንዘብ ሚኒስቴር ሥር የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ዳይሬክቶሬት ጄነራል ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር  ጄኔራል ዶክተር ተሾመ ታፈሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡ ሆኖም መንግስት በአንድ ጊዜ እነዚህን ሁሉ ፕሮጀክቶች ተከታትሎ ለማስፈፀም አቅምና ብቃቱ  አጠያያቂ በመሆኑ 10 ድስቶች ጥዶ አንዱን ማማሰል፣ 9ኙን ለማሳረር!!! ነው እንላለን፡፡ በመጀመሪያ ያላለቁት በአግባቡ ቢጠናቀቁ ይሻላል ብለን የዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት እንመክራለን፡፡ ሃገሪቱ ያለባትን የእዳ ጫና ሳናስወግድ ለሌላ ብድር ማመቻቸት መዘዙ ብዙ  ነው፣ ለቀጣዩ ትውልድ እንደ ወያኔ እዳ አናውርሰው፡፡ የተጀመረው በውኃና በፀሐይ ኃይል የሚመነጭ የኤሌክትሪክ ኃይል 17 ሽን ሜጋ ዋት ፕሮጀክት ሥራ ሳይጠናቀቅ ተጨማሪ 13 ፕሮጀክቶች ለምን አስፈለገ። በሃገሪቱ ትንታግ ጋዜጠኛና የሃይድሮ ፓወር የተማረ ምሁር ቢኖር  ይሄን እቅድ በመቃወም ና የተጀመሩት እንዲጠናቀቁ በመሞገት የአብዩን መንግስት ቢታደገው በተገባ ነበር እንላለን፡፡

6.3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ 16 የአጋርነት ፕሮጀክቶች ይፋ ሆኑ፤-   ጥቅምት 15፣ 2011 6.3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ በትራንስፖርትና ሀይል አቅርቦት ዘርፎች  ያተከሩ 16 የመንግስትና የግል አጋርነት ፕሮጀክቶች ይፋ ሆኑ። የኢትዮጵያ የመንግስትና የግል አጋርነት ፅህፈት ቤት ካፀደቃቸው 16 ፕሮጀክቶች መካከል 13ቱ በሀይል አቅርቦት ዘርፍ ሲሆኑ፥ ሶስቱ የትራንስፖርት ፕሮጀክቶች እንደሆኑ ተጠቁሟል።

{1} ገናሌ ዳዋ 5 የሀይል ማመንጫ ፦     469 ሜጋ ዋት፦   በ793 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

{2} ገናሌ ዳዋ 6 የሀይል ማመንጫ ፦      100 ሜጋ ዋት፦    በ387 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ፣

{3} ጨሞጋ የዳ 1ና 2 የሀይል ማመንጫ፦ 280 ሜጋ ዋት፦   በ729 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

{4} ሀሌሌ ዋራቤሳ የሀይል ማመንጫ፦   424 ሜጋ ዋት ፦   በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

{5} ዳቡስ የሀይል ማመንጫ፦            798 ሜጋ ዋት፦    በ984 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

{6} ጋድ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ፦        125 ሜጋ ዋት ፦     በ150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

{7} ዲቻቶ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ፦     125 ሜጋ ዋት ፦    በ150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

{8} መቐለ የፀሃይ ሀይል ማመንጫ፦      100 ሜጋ ዋት ፦ በ120 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

{9} ሁመራ የፀሃይ ሀይል ማመንጫ፦     100 ሜጋ ዋት፦     በ120 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

{10} ወለንጪቲ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት፦ 150 ሜጋ ዋት፦ በ165 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

{11} ዌራንሶ የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ፦          150 ሜጋ ዋት፦ በ165 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

{12} መተማ የፀሀይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት፦    125 ሜጋ ዋት፦ በ150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

{13} ሁርሶ የፀሃይ ሀይል ማንጫ ፕሮጀክት፦         125 ሜጋ ዋት ፦ በ150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣

በአጋርነት እንዲገነቡ ውሳኔ ከተሰጠባቸው የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የኃይድሮ ኃይል ፕሮጀክቶች እና በፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት  በመቀሌ፣ በሑመራ የሚያመነጩ ሁለት ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በአፋር፣ በድሬዳዋ፣ በሶማሌ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና በትግራይ ውስጥ የሚገነቡ ማመንጫዎች፣ ማሰራጫዎችና የኃይል ማስተላለፊያ ጣቢያ/ ሰብስቴሽኖች ሥራ እንደሚካሄድ ታውቆል። እንዲሁም በትራንስፖርት ዘርፉ

{14} የአዳማ አዋሽ 125 ኪሎ ሜትር የፍጥነት  መንገድ በ440 ሚሊየን ዶላር፣

{15} አዋሽ ሚኤሶ 72 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ በ230 ሚሊየን ዶላር እና

{16} ከሚኤሶ ድሬደዋ 160 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ  በ445 ሚሊየን ዶላር የሚገነቡ  ሲሆን በዚህ ጨረታ ወጥቶላቸው ወደ ስራ ይገባሉ ተብሏል። በተለዩት ፕሮጀክቶች ዙሪያ በዚህ ዓመት ጨረታ ወጥቶባቸው  ወደ ግንባታ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ የመንግስትና የግል አጋርነት ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ተሾመ ታፈሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቀዋል።

ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ያልተጠናቀቁት የኃይል ማመንጫዎች በተለይ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሳይጠናቀቅ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ቦርድ 6.5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቁ 17 የኃይል ማመንጫና የፍጥነት መንገዶች በአጋርነት እንዲገነቡ ወሰነ ይለናል የሪፖርተር ጋዜጣ፣ የድሮ ጋዜጣና ጋዜጠኛ ድሮ ቀረ መሰለኝ፣ የተጀመሩት አለቁ ወይ፣ 6.5 ቢሊዮን ዶላር ከየት ይመጣል፣ በብድር ከቻይና ነው ከህንድ ወይስ  ከውጪ ኢንቨስተሮች፣  አንድ ጵሮጀክት ሲያልቅ አንዱ ቢቀጥልስ፣ እንደ ሜቴክ 10የስኮር ፕሮጀክት፣  15 ኢንዱስትሪያል ዞን፣ 10 የአግሮኢንዱስትሪ፣ አንድ አስር ስታዲየሞች፣ አንድ አምስት የመስኖ ግድብ ወዘተርፈ ተብሎ  አንዱ ሳያልቅ፣ ሱሪ ባንገት እንዳይሆን ጋዜጠኞች ካሉ ለምን  ዳይሬክተር ጄኔራል ተሾመ ታፈሰ (ዶ/ር) በመገናኛ ብዙኃን አይጠይቆቸውም? ለምንስ  ምሁራን የማይወያዩበት? ካለፈው የፕሮጀክቶች ግንባታ ያገኘንው ትምህርት ምንድነው? የአዋጭነት ጥናታቸው ለምን ለምሁራን እንዲያዩት ይፋ አይሆንም? በድረገፅ ቢሰራጭ ? ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው አስራር አይሆንም ወይ?  5 ቢሊዮን ዶላር ካላችሁ ለምን ታላቁ የህዳሴ ግድብን አትጨርሱበትም? ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚጠይቁና ከ3,000 ሜጋዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ 14 ሜጋ ፕሮጀክቶችን መገንባት ለምን አስፈለገ? ፣ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት 6400 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጭ ከእጥፍ በላይ ሆኖ ለእሱ ቅድሚያ አለመስጠቱ ለምን?  በሃገሪቱ የኤሌትሪክ መቆራረጡ እየባሰ መሄዱ፣ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ በተለይም የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችና የኢንዱስትሪ ዞኖች ሥራና ምርታማነትን እየተፈታተነ መገኘቱ እስከመቼ ይቀጥላል?ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚጠይቁና ከ3,000 ሜጋዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ 14 ሜጋ ፕሮጀክቶችን

  • በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ከኤሌትሪክ ኃይል ኤክስፖርት (የውጪ ንግድ) 636 ሚሊዩን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶል ይል ነበር ከሽፎል፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ በአግባቡ አለመጀመር ለሌላ የኢኮኖሚ ኪሣራ ሃገሪቱን ይዳርጋል እንላለን፡፡
  • የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በሆለተኛረ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ 5779 ኪሎሜትር መንገድ 4579 ኪሎሜትር አድሳትና ግንባታ አካሂዶል፡፡ በክልሎች ተፈፃሚ የሚሆነው ሁሉን አቀፍ የገጠር መንገዶች ልማት ፕሮግራም እስከ 90 ሽህ ኪሎ ሜትር መንገድ ለመገንባት ታቅዶ አፈጻፀሙ ከአስር በመቶ እንዳልበለጠ ዳሬክተሩ አቶ ሳምሶን ወንድሙ ገልፀዋል፡፡
  • ጥቅምት 14 ቀን 2011 ዓ/ም መንገዶች ባሥልጣን 14 ቢሊዮን ብር ለሚጠይቅ ፕሮጀክቶች 3 የቻይናተቆራጮች የ8.5 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክቶች

{1}  የቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽንኩባንያ (ሲሲሲሲ)ሁለት ምንገዶች ኮክስቴ ሰሚዳ ድረስ የሚዘረጋውና 53 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን መንገድበ1.98 ቢሊዮን ብር እና

{2} ከአርሲ፣ሮቤ፣ አጋርፋ፣ ኢሊኮንት አንድ ከአሊ ከተማ፣ ዋቤ ድልድይ ድረስ ያለውን 53 ኪሎ ሜትር መንገድ በ2.1 ቢሊዮን ብር

{3} ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ከመሰል/ ሞላሲ ካራቆሪ 73.5 ኪሎ ሜትር መንገድ በ1.5 ቢሊዮን ብር

{4} ከመሰል/ ሞላሲ ካራቆሪ 84.2 ኪሎ ሜትር መንገድ በ1.53 ቢሊዮን ብር እንዲሁም

{5} ቻይና ሬልዌይ 21ኛ ግሩፕ ከጅማ፣ አጋሮ፣ ደዴሳ ወንዝ 79 ኪሎ ሜትር መንገድ በ 1.3 ሚሊዮን ብር በድምሩ 8.5  ቢሊዮን ብር ፕሮጀክቶች ለቻይና የመንገድ ተቆራጮች ተሰጥቶል፡፡ በተመሳሳይ የህወሓት/ኢፈርት የፖለቲካ ፓርቲ ንግድ ድርጅቶች ሦስት ፕሮጀክቶች በ5.5 ቢሊዮን ብር ለመገንባት ተስማምተዋል፡፡

{6} ሱር ኮንስትራክሽን ከውቅሮ-አዲአቢ-ካነባ ያለውን 63 ኪሎ ሜትር መንገድ በ1.7 ቢሊዮን ብር፣

{7}  መከላከያ ኮንስትራክሽን ከጣርማ በር መለያ ሠፈር ሜዳ መገንጠያ መለያ ሞላሌ መንገድ መገንጠያና ሞላሌ ወገሬ ድረስ 118.8 ኪሎ ሜትር መንገድ ለመገንባት በ1.9 ቢሊዮን ብር፣

{8} የንኮማድ ከአዲአርቃይ ጠለምት 76.6 ኪሎ ሜትር መንገድ በ1.92 ቢሊዮን ብር በአጠቃላይ ሦስት ፕሮጀክቶች በ5.5 ቢሊዮን ብር ለመገንባት ተፈራርመዋል፡፡ በጥቅሉ የመንገድ ተቆራጮቹ 600 ኪሎሜትር መንገድ በ13.8 ቢሊዮን ብር ወጪ 1 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ በ23 ሚሊዮን ብር ወጪ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነርሀብታሙ ተገኝ ጋር ተፈራርመዋል፡፡ የህወሓት/ ኢፈርት የፓርቲ ድርጅቶች የግሉን ዘርፍ ከማቀጨጫቸው ሌላ ምንም ለውጥ የለ፡፡ አሁንም ብድር፣ ብድር ስልቻ ቀልቀሎ!!! ቀልቀሎ ስልቻ!!!

በኢትዮጵያ አጠቃላይ 45 ሽህ ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችሉ  የውሃ፣ የንፋስ፣ የፀሃይና  የጅዋተርማል የኢነርጅ/ የሃይል ሃብት በሃገሪቱ ይገኛል፡፡  እንዲሁም አስራአንድ ዋና ርግረግማ ሥፍራዎችና ርጥበታማ ቦታዎች ይገኛሉ፡፡የኢትዩጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ከኢትዩጵያ መስኖና ኤሌትሪክ ሚኒስቴር መረጃ መሠረት‹‹ኢትዩጵያ ከውሃ 45 ሽህ ሜጋ ዋት፣ ከንፋስ 1.3 ሚሊዩን ሜጋዋት፣ ከእንፋሎት 10 ሽህ ሜጋ ዋት፣ ከካርቦን ኒውትራል እና ከሌሎችም ኃይል ማመንጫዎች ከፍተኛ ኃይል ለማምረት ዕምቅ አቅም አላት›› ከወሬው ባሻገር ያለው እውነት ግን   የኤሌትሪክ ኃይል በማመንጨት ላይ ያሉ መልካዋከና፣ አዋሽ 1 እና 2፣ ተከዜ፣ ጣና በለስ፣ ግልገል ጊቤ 1 እና 2፣ ፊንጫ አመርቲ ነሼን ጨምሮ ሌሎችም የውሃና የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች ተደማምረው 2300 ሜጋዋት እና የግልገል ጊቤ ሦስት 1870 ሜጋዋት ጋር 4260 ሜጋ ዋት አቅም ይኖራታል፡፡ የህዳሴው ግድብ  6450 ሜጋዋት የሃይድሮኤሌትሪክ ሃይል ግንባታ ሲጠናቀቅ 10 ሽህ ሜጋ ዋት አቅም ይኖራታል፡፡ ከሃገሪቱ ህዝብ 70 በመቶው በጨለማ ውስጥ ይኖራል ማለትም የመብራት አገልግሎት አያገኝም፣በማለት ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል  የኢትዩጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት መሥሪያ ቤት  በአሁኑ ወቅት 2 ሚሊዮን 500 ሽህ  ደንበኞች እንዳሉት ገልፆል ስለዚህ ከ100 ሚሊዩን ህዝብ ውስጥ 2.5 ሚሊዮን ህዝብ ብቻ የመብራት አገልግሎት ይደርሰዋል ማለት ነው፡፡ በቀ.ኃ.ሥ ዘመን በ1904ዓ/ም አዲስ አበባ ከተማ ወጣ ብሎ አቃቂ የአባ ሳሙኤል ኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተገነባ፡፡ በኢትዩጵያ የመጀመሪያው የኤሌትሪክ ኃይል የሆነው ግድብ 7 ሜጋ ዋት፣የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት አቅም ነበረው፡፡ የአባ ሳሙኤል ኃይል ማመንጫ በብልሽት ምክንያት ላለፉት 40 ዓመታት ያህል አገልግሎት ሳይሰጥ ቆይቶል፡፡ የኃይል ማመንጫው በ2007-2009 ዓ/ም እድሳቱ ግዜ ተደርጎለት የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት አቅሙ 7 ሜጋ ዋት፣ በቻይና መንግስት እርዳታ የተሠራ ሲሆን አጠቃላይ የግንባታው ወጪ 95 ሚሊዩን ዩዋን ነበር፡፡ ኮንትራክተር የቻይናው ፓወርና፣ቻይና ሁዋዶንግ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በጋራ ነበር፡፡ ጊቤ አንድ እና ሁለት የኃይል ማመንጫ፣ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት አቅም 184 ሜጋ ዋት፣ እና 420 ሜጋ ዋት ነው፡፡ ጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ፣በደቡብ ክልል (ወላይታና ዳውሮ ዞኖች)፣(የግንባታው በ1999እኤአ ተጀምሮ በ2009እኤአ ተጠናቀቀ፡፡ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት አቅም 1870 ሜጋ ዋት ሲሆን (900 ሜጋ ዋት ኃይል በማመንጨት ላይ ይገኛል)፣ የፕሮጀክቱ ወጪ 1.5 ሚሊዩን ዩሮ አጠቃላይ የግንባታው ወጪ ሽፋን ድርሻ፣ የቻይና መንግሥት 60 በመቶ የኢትዩጵያ መንግስት 40 በመቶ ነበር፡፡ ኮንትራክተሮች ሳሊኒ ኢምፕሬጂሎ ኮንስትራክሽን (ሃገረ- ጣልያን)እና የቻይናው ዶንግ ፉንግ በጋራ የተገነባ ነው፡፡ ጊቤ አራት የኃይል ማመንጫ፣ደቡብ ክልል (በነገሌ ቦረና-ጉጂ ዞን) ገናሌ ዳዋ ኃይድሮ ኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት(2003-2009) የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት አቅም 2150 ሜጋ ዋት፣ የፕሮጀክቱ ወጪ 2.67 ቢሊዮን ዩኤስ ዶላር አጠቃላይ የግንባታው ወጪ ሽፋን ድርሻ፣ ቻይና 85 በመቶ ፕሮጀክቱ ወጭ የምትሸፍነው (through preferential buyer’s credit and concessionary loans) ነው፡፡ የጊቤ አራት ሃይድሮኤሌትሪክ ሃይል ፖሮጀክት/ በጁላይ 2009 እኤአ ኢትዮጵያ ከቻይና  በሲኖ ሃይድሮ ኮርፖሬሽን (Sino Hydro Corporation) ተጨማሪ የስምምነት ፊርማዋን በማኖር 2150 ሜጋ ዋት ሃይድሮኤሌትሪክ ሃይል ፖሮጀክት በጊቤ አራት (በኦሞ ወንዝ)ና ሃሌሌ ወራቤሳ ግድብ ለመስራት 2.67 ቢሊየን  ዩኤስ ዶለር  ተስማማች፡፡ ገናሌ ዳዋ ኃይድሮ ኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ በኦሮሚያ ክልል በነገሌ ቦረና-ጉጂ ዞን የሚገኝ ሲሆን፣ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት አቅም 254 ሜጋ ዋት ሲሆን፣ የፕሮጀክቱ በ2003 ተጀምሮ በ2009 እኤአ ለመፈጸም ታቅዶ ነበር፡፡  የፕሮጀክቱ ወጪ 451 ሚሊዩን ዶላር ሲሆን፣ አጠቃላይ የግንባታው ወጪ ሽፋን ድርሻ አልተገለፀም፡፡ የቻይናው ጌሹባ ግሩፕ(ሲጂጂሲ)የፕሮጀክቱ  ኮንትራክተር በመሆን ይሰራል፡፡ ተከዜ ኃይድሮ ኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ ትግራይ ክልል፣ ከ1994-2001 እኤአ  የተሠራ  የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት ግድብ ሲሆን ግድብ በተከዜ ወንዝ ላይ  በ2007 ዓ/ም ለማጠናቀቅ ታቅዶ በመሬት መንሸራተት ችግር ምክንያት ፕሮጀክቱ የተጠናቀቀው በ2009 ሲሆን አጠቃላይ የግንባታ ስራው የፕሮጀክቱ ወጭ በ1.5 ቢሊዩን ብር ወይም 365 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር ሲደርስ 360 ሜጋ ዋት ያመነጫል ቢባልም 75 ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ሃይል እንደሚያመነጭ ይታወቃል፡፡ የፕሮጀክት ተቆራጭ  ኮንትራክተር የቻይናው ዳንግ ፉንግ ግሩፕ(ሲጂጂሲ) ነበር፡፡

የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከ2003 ተጀምሮ፣በ2011 ዓ/ም በአራት አመት ይጠናቀቃል ተብሎ 8 አመቱ ተገባዶል፡፡  የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ቦርድ 6.3 ቢሊዮን ዶላር የሚጠይቁ 13 የኃይል ማመንጫና 3 የፍጥነት መንገዶች በአጋርነት እንዲገነቡ ተወስኖል ይሉናል፡፡ መንግስት ፕሮጀክቶች ተከታትሎ የማስፈፀም አቅምና ብቃት ስለሌለው ገንዘቡ ለሌብነት ይዳረጋል የተጀመሩትን ፕሮጀክቶች ማጠናቀቅ ለሃገርና ለወገን ማሰብ ይሆናል ለተጨማሪ  ለአስራሁለቱ  3,071 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ወጪ በ5.263  ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ከማውጣት የህዳሴውን ግድብ 6,450 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ  መጨረስ ታላቅነት ነው እንላለን ካለበለዛ እንደ ወያኔ አስር ድስት ጥዶ አስሩንማ ማሳረር እንዳይሆን እንፈራለን፡፡  ‹‹የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መቼ ይጠናቀቃል?

የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ዘርፍ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ የአገልግሎት ገቢ፣ የኢነርጂና ኃይል ሽያጭ፣በአዲስ ኤሌትሪክ ኃይል የተገናኙ የመንደር ከተሞች እና የደንበኞች ብዛት (በሚሊዩን) ከ2006 እስከ 2012እኤአ አፈፃፀም ለመረዳት፤

(1) በኢትዬጵያ የኤሌትሪክ አገልግሎት ገቢ በ2006 እኤአ 166 ሚሊዩን ዶለር፣2007 እኤአ 208 ሚሊዩን ዶለር፣2008እኤአ 202 ሚሊዩን ዶለር፣ 2009 እኤአ 164 ሚሊዩን ዶለር፣ 2010 እኤአ 132 ሚሊዩን ዶለር፣ 2011 እኤአ 137 ሚሊዩን ዶለር እና 2012 እኤአ  190 ሚሊዩን ዶለር ኤሌትሪክ አገልግሎት ገቢ ተመዝግቦል፡፡ ከህዝቡ ቁጥር ጋር ሲወዳደር የኤሌትሪክ አገልግሎት ገቢ አናሳ እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ እንዲሁም በኢትዬጵያ የኤሌትሪክ አገልግሎት ገቢ አመታዊ እድገት በመቶኛ አነስተኛ ነው፡፡

(2) በኢትዬጵያ የኢነርጂና ኃይል ሽያጭ በ2006 እኤአ 2,408 ጊጋዋት በሰዓት፣2007 እኤአ 2.799 ጊጋዋት በሰዓት፣2008እኤአ 2,966 ጊጋዋት በሰዓት፣ 2009 እኤአ 3,132 ጊጋዋት በሰዓት፣ 2010 እኤአ 3,264 ጊጋዋት በሰዓት፣ 2011 እኤአ 4,218 ጊጋዋት በሰዓት እና 2012 እኤአ  4,578 ጊጋዋት በሰዓት የኢነርጂና ኃይል ሽያጭ ተመዝግቦል፡፡ ከህዝቡ ቁጥር ጋር ሲወዳደር የኢነርጂና ኃይል ሽያጭ ገቢ አናሳ እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ እንዲሁም በኢትዬጵያ የኢነርጂና ኃይል ሽያጭ ገቢ አመታዊ እድገት በመቶኛ አነስተኛ ነው፡፡

(3) በኢትዬጵያ የኤሌትሪክ ደንበኞች ተጠቃሚ ብዛት በ2006 እኤአ 1.1 ሚሊዩን ህዝብ፣2007 እኤአ 1.3ሚሊዩን ህዝብ፣2008እኤአ  1.6ሚሊዩን ህዝብ፣ 2009 እኤአ 1.7 ሚሊዩን ህዝብ፣ 2010 እኤአ 1.8 ሚሊዩን ህዝብ፣ 2011 እኤአ  2.0 ሚሊዩን ህዝብ እና 2012 እኤአ  2.2 ሚሊዮን ህዝብ እና በ2018  2.5 ሚሊዩን ህዝብ የኤሌትሪክ ደንበኞች ተጠቃሚ ይገኛሉ፡፡ ከህዝቡ ቁጥር ጋር ሲወዳደር ምን ያህል ተጠቃሚው አናሳ እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ እንዲሁም በኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ደንበኞች ተጠቃሚ ቁጥር አመታዊ እድገት በመቶኛ አነስተኛ ነው፡፡

(4) በኢትዬጵያ በኤሌትሪክ የተገናኙ የመንደር ከተሞች 899 በ2006 እኤአ፣ 1,757 በ2007 እኤአ፣ 3,363 በ2008 እኤአ፣ 3,763 በ2009 እኤአ፣ 5,163 በ2010 እኤአ፣ 6,000 በ2011 እኤአ እና 7,000 በ2012 እኤአ  በኤሌትሪክ የተገናኙ የመንደር ከተሞች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ የመንደር ከተሞች ቁጥር ጋር ሲወዳደር ምን ያህል ተጠቃሚው አናሳ እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ እንዲሁም በኤሌትሪክ የተገናኙ የመንደር ከተሞች ተጠቃሚ ቁጥር አመታዊ እድገት በመቶኛ አነስተኛ ነው፡፡

(5) በኢትዬጵያ በአሃድ የኤሌትሪክ ገቢ በደንበኛ 2008 እኤአ  125.2 (በዩኤስኤ ዶለር)፣ 2009 እኤአ 94.5 (በዩኤስኤ ዶለር)፣ 2010 እኤአ 73.1 (በዩኤስኤ ዶለር)፣ 2011 እኤአ  67.5 (በዩኤስኤ ዶለር) እና 2012 እኤአ  85.2 (በዩኤስኤ ዶለር) የኤሌትሪክ ገቢ በደንበኞች ተጠቃሚ ነበሩ፡፡

የኢትዩጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት የኤሌትሪክ ጅረት ቆቶች የተዘረጉትና ሥርጭታቸው ድንበር የለሽና ወሰን የለሽ እንዲያውም የሃገር ድንበርና ወሰነ ዘለል በመሆን ከኢትዮጵያ ሃገረ ኬኒያ፣ ሃገረ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ወዘተ ድረስ የተዘረጋ የኤሌትሪክ ኃይል፣ በርካሽ ዋጋ ለጎረቤት ሃገራት ኤሌትሪክ አገልግሎት ሲሸጡ የሃገራችን ዜጎች በጨለማ ውስጥ እንዲኖሩ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ዜጎቹን በጨለማ የሚያኖር ዶላር የተጠማ መንግስት አያልፍለትም እንላለን፡፡ ምን ቢታለብ በገሌ እንዳለችው ድመት!!!

የህወሓት/ኢህአዴግ ኢፈርት፣ ጥረት፣ ዲንሾ፣ ወንዶ የፖለቲካ ፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ከግሉን ዘርፍ ኢኮኖሚ ሥራ በአስቸኳይ ይውጡ!!!

ምንጭ Source:

@africaprogress 16.09.2016 / Africa Progress Report 2015

Ethiopian Electric Power Corporation, September, 2009