የድሬዳዋ ወጣቶች ህብረት ሳተናው አባላት ከድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ኢብራሒም እና ምክትላቸው አቶ አብደላ እንዲሁም ሙሉ የካቢኔ አባላት ወደ አዳራሹ ገብተዋል ። ውይይቱ ተጀምሯል ከህገ መንግስቱ እስከ ቻርተሩ ፣ ከኢኮኖሚ እስከ ማህበራዊ ፣ ከፖለቲካ እስከ ሙስናና ዝርፊያ ድረስ እየተዘከዘከ ነው! እስካሁን ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ እየተሰጠ ነው።  ተሳታፊው በእድሜም ፣ በፆታም ፣ በሙያም በሃሳብም ፣ በብሄርም ስብጥር የተሟላ ነበር ። የተነሱ ጥያቄዎች ለድሬዳዋ ነዋሪዎች በሙሉ የሚጠቅሙ የወል (common) ጥያቄዎች ነበሩ ። ከንቲባው ፣ ምክትል ከንቲባው ና ተሳታፊ የድርጅት ኃላፊዎች ና የካቢኔ አባላት መልስም ሆነ አስተያየት ቅን እና ግልፅ ነበር ። ጥያቄውን ያነሱ ወጣቶቻችን በመረጃ የተመሰረተ በሙያና በልምድ የታገዘ ትንታኔ ና አስተያዬት እየሰጡ ነበሩ ። ሙሉ ቪዲዮ እንደደረሰን የሚለቀቅ በመሆኑ ከወዲሁ መግለፅ እንወዳለን።

%e1%8b%b5%e1%8b%b51

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here