በሀገራችን ዝርፍያና ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ባለስልጣኖችን ማደኑ ተጠናክሮ መቀጠሉ የተሰማ ነው

አባይ ሚዲያ ዜና
በአሰግድ ታመነ

በሀገራችን ላይ ዝርፊያ፣ወንጀልንና የሀገር ክህደት የፈጸሙ በቁጥጥር ስር ማድረግ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የደረሰን መረጃ እንደሚያሳየው በመከላከያው ውስጥ ተጠናክሮ የቀጠለው ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር የማዋል እርምጃ በደንነቱ መስርያ ቤትም ገብታል ተብላል።
በቅፅል ስሙ ኢንሳ ተብሎ በሚጠራው የደህንነት መስርያ ቤት ውስጥ ላለፉት 27 አመታት ከፍተኛ ወንጀል መፈፀሙ የሚታወቅ ነው። የሀገሪቱ ጠ/ሚንስትር በይቅርታ  ስለወደፊቱ የሀገሪታ እጣፋንታ እናስብ በሚል ለማለፍ ቢፈልጉም ለዘመናት ወንጀልና ዝርፊያ ሲፈፅሙ የነበሩት ከፍተኛና ዝቅተኛ ባለስልጣናት ከዚህ ድርጊታቸው ተምረው ለመለወጥ ባለመፈለጋቸው ምክንያት ሀገሪታን በማበጣበጥ ስራ ተጠምደው መቆየታቸው በመታወቁ ዶክተር አብይ ወደ ማይፈልጉት እርምጃ ለመሸጋገር መገደዳቸውን መረጃው ያሳያል ::

በወንጀል ተጠርጥረው ከተያዙት የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት መስሪያ ቤት አመራሮች መካካል የሦስት ዳይሬክተሮች ዳይሬክተር የነበረው፤ ሌላኛው የጌታቸው አስፋ ምክትል እና ቀኝ እጅ የነበረው ዶ/ር ሀሺም ይገኝበታል። ዶ/ር ሀሺም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤቱ ዋና እና ቁልፍ ሰው ሲሆን የሰው ኃይል ምልመላ፣ መረጣ፣ ስምሪት፣ ስልጠና፣ የመስሪያ ቤቱ አጠቃላይ አደረጃጀት፣ መዋቅርና የውጭ ግንኙነት በበላይነት የሚመራ እና ጌታቸው አሰፋ የሚተማመንበት ዋነኛ ሰው ነበር።

በዚህም ምክንያት ሰሞኑን አሰልሶ የለውጥ ሀይሉ በወሰደው ጥበብ የተሞላበት እርምጃ በጌታቸው አሰፋ እዝ በብሄራዊ ደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣኖች የሚከተሉት በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግራል።

-አቶ ደረሶ አያና:- የሰሜን ምዕራብ መምሪያ ኃላፊ

-.አቶ ኢዮብ ተወልደ:- የደቡብ ክልል መረጃ እና ደህንነት ኃላፊ

-ዶ/ር ሀሺም ተውፊቅ:- የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ም/ኃላፊና የአቅም ግንባታ ዘርፍ የዳይሬክተሮች ዳይሬክተር

-አቶ ደርበው አስመላሸ:- የኢኮኖሚ ደህንነት መምሪያ ዳይሬክተር
-.አቶ ተሾመ ኃይሌ:- የጥበቃና ኤርፖርቶች ደህንነት ዳይሬከተር

-አቶ አማኑኤል ኪሮስ:- የአገር ውሰጥ ደህንነት መምሪያ ኃላፊ

-አቶ አስገለ:- የውጭ ደህንነት መምሪያ ም/ዳይሬክተር እና ለጊዘው ስማቸውን ያልያዝናቸው አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግራል።