ቭላዲሚር ፑቲን እና ህወሃት እንዴት ከበሩ?

0

ቭላዲሚር ፑቲን እና ህወሃት እንዴት ከበሩ?

ጋሻው ገብሬ
መግቢያ

በአገራችን ኢትዮጵያ የለውጥ መምጣት ዋና መለኪያችን የተቋማት ነጻነት መልሶ መገኘት እንጂ የሌቦች እስር ቤት መግባት ብቻ አይደለም። ሌባን ሌባ ይተክዋል።የተቋማት ነጻነት የአገር ነጻነት ነጸብራቅ ነው።ውሉና መሰረቱም ነው!

አዲስ አበባ እና ምስኮብ ቢራራቁም በመስኮብ ከተማ “ፑቲን ሌባ” አዲስ አበባ ደግሞ “ ወያኔ ሌባ” እንዴት አንድ አይነት መፈክር ከሁለቱም ከተሞች ይሰማ ነበር?ዛሬ የመስኮቡ ፑቲን ህዝብ አፍኖ አይቀሬ ውድቀቱን የጠብቃል። አዲስ አበባ ደግሞ መንግስታዊ ሌቦች\ህወሃቶች እና ረዳቶች ለፍርድ እየቀረቡ ነው።

የጥቂቶች አገዛዝ ወደ ሌቦች ስርአት የሚለወጥበት መንገድ ደረጃ በደረጃ የሚሆን ነው።በኢትዮጵያ እና በሩሲያ የሆነው በተመሳሳይ መንገድ ነው።ግዙፉ ልዩነት የኛዎቹ ህወሃቶች በአገር ጥላቻ እልህ ሲዘርፉ ፑቲን “አገሬን እወዳለሁ” ከውርደት አድናታለሁ” ባይ ነው።

ህወሃቶች እና ረዳቶች የስርቆት እና ጭካኔ ስራት ገና ይፋ እየወጣ ነው።እነሱም ፑቲንም ተቃዋሚያቸው የሚያጠፉበት መንገድ ተመሳሳይነት አለው። አምባ ገነኖች ሰቅዘው የያዙት አገር አይበለጽግም።በህብረተሰባችን እንዲህ የሚያተራምስ ለውጥ እየተካሄደ የአምባገነኖች መውደቀት ግር የሚላቸው አሉ።እኒህ ያሳዝናሉ።

“ፑቲን፡ከጥቂቶች አገዛዝ ወደ ሌቦች ስርአት” (Putin: From Oligarch to Kleptocrat) by Ruth May በሚል ርእስ የተዘጋጀውን በኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የመጻህፍት አምድ አግኝቼ ከጽሁፉ ጭማቂ የሚሆን ከአጫጭር ምልከታዎች ጋር እነሆ አቅርቤአለሁ።


ኖቬምበር 1989 የበርሊን ግንብ ሲናድ (በጊዜው ምእራብ እና ምስራቅ ጀርመንን ሁለት አገራት ነበሩ) አንድ የሶቪየት ስለላ ድርጀት አባል ድሬስደን (ምስራቅ ጀርመን)በምድብ ስራው ላይ ነበር።በጥድፊያ የመረጃ ሰነዶችን እያወደመ ነበር።ያለበትን መስሪያት ቤት አመጽ ላይ የርነበረው የምስራቁ ህዝብ ሰብሮ ሊገባ እንደ ነበር ይህ ሰላይ ካለፈ ወዲያ ያስታውሰዋል። እሱ እየተጣደፈ የመረጃ ሰነዶችን ሲያጉር ምድጃው አልችል ብሎ ሊፈነዳ ነበር።ይህ ነገር በሆነ በአስር ዓመታት ውስጥ ይህ ሰላይ የሩሲያ ሁሉ መሪ ቭላዲሚር ፑቲን ሆኖ ተገኘ። (በኢትዮጵያ ደግሞ አገር ወድሞ ህወሃት የሚባል ተባይ ሰተት ብሎ መጣ)

አጀማመር

ቭላዺሚር፡ፑቲን እንዲያው የሚታወቅ ሰውም አልነበረም። ሩሲያ መንግስት ለውጥ ታመጡት መሪ ጎርባቾቭ በፕሬዚዳንት ቦሪስ ያልትዝን ተተክትው እየሰሩ በ1999 ዘመን መለወጫ ቀን ፑቲንን ቦሪስ ያልትዝን ምትኬ ነው በማለት ዓለምን አስገረሙ። ሆኖም ፑቲን በዓለም፡ባይሆንም፡በሩሲያ ውስጥ ግን እውቅና አትርፎ ነበር።ቀድሞ ኬጂቢ የተሰኘው የስለላ ድርጀት የፌዴራል መንግስት ጸጥታ መስሪያ ቤት በመሰኘት ተገምብቶ ነበር።በዚህ ጸጥታ ድርጀት ውስጥ ፑቲን ቆንጮው ላይ ደርሶ ነበር።ፑቲን በአዲስ ዓመት ዋዜማ የመንግስት መሪነትን ሲቀበል “የመናገር፤የህሊና ነጥጻነት፤ነጻ ጋዜጣ፤የግል ሀብት መያዝ መብት በማንኛውም የሰለጠነው ዓለም እንዳለው ሁሉ ይከበራሉ” በማለት ተናግሮ ነበር።ወዲያ ግን ይህ ቃል ታጠፈ። (ህወሃት ማለዳ የወሸከተው ከዚህ ተመሳሳይ ነበር)

ተክለ ሰውነት ግንባታ

እራሱን ለስልጣን ሲያመቻች ገና 1992 ፑቲን ለሞስኮ ከተማ ከንቲባ ሲሰራ የቴሌቪዝን ምስል ቀረጻ ኩባንያ ቀጥሮ ስለ እለራሱ ሃታች ሲኔማ አስቀርጾ ቭላስት (ትርጉም፡ስልጣን/ታላቅነት) ብሎ ሰየመው።ሩሲያን እንደገ እና ታላቅ አደርጋታለሁ ለማለት።ሲጀመር ነጻ ገበያ በሩሲያ መልካም ጅማሮ ይዞ ነበር።ከአገሩ ኢኮኖሚ 89 እጁ ከመንግስት እጅ ውጭ ሆኖ ነበር።ከአገራዊ አጠቃላይ ምርቱ 11 እጅ ደርሶ ነበር።ሩሲያ ከሚከተሉት አገራት በልማት ግስጋሴ ተደምራ ነበር።ህንድ፤ቻይና፤ብራዚል። (የህወሃትን ከመቶ 11 እጅ ከንቱ መዝሙር ታስታውሷል ታላቁ! በለራእዩ! የተባሉበት የነመላስ እንቶፈንቶስ ይችን አሃዝ ተውሷት ይሆን?)

ቀስ በቀስ መደራጀት

ፑቲን ቀስ በቀስ በዘዴ ከቀድሞ የስለላ ድርጀት መስሪያ ቤት ለራሱ በጣም ታማኝ የሆኑትን እየወሰደ በአገር ግዛት ሚኒስቲርና በመከላከያ ውስጥ ሰገሰጋቸው።በዚህም ቀድሞ በኮሚኒስት ሩሲያ እንደነበረው ሁሉ የጠበበ ቡድናዊ አሰራርን መልሶ ገነባው።ይህን እየተገበረ ለዓለም ደግሞ የነጻ ገበያ ኢኮኖሚ ተቀብያለሁ በማለት ዓለምን እያዘናጋ ውስጥ ውስጡን እፍኝ የማይሞሉ የሚያሾሩት የመንግስታዊ ከበርቴ ስራትን ገነባ። (ህወሃት የኖረውን አፍርሶ የራሱ የሌብነት መዋቅር አበጀ።ምእራቡ እሰይ እደግልን አለው።)

ነጻ የዜና ተቋማትን ማፈን

ለፑቲን የዜና ተቋማት የመጀመሪያው የጥቃት ኢላማው ነበሩ።በ1990 የግል ባለሀብቶች የሚረዷቸው ብዙ መንግስታዊ ያልሆኑ ጋዜጦች፤ራዲዮ፤ቴሌቪዥን ጣቢያዎች።አልማራቸውም።አንደኛውን በተለይ ኤን ቲቪ (NTV) የተሰኘው እና ፑቲን በተረት ተረት አድርጎ የቀለደበትን ተቋም በፒተርስበርግ ዩኒቬርሲቲ የበላይ ሰው እንዲወገዝ አድረገው። ወዲያው  ኤን ቲቪ በፖሊስ ተበረበረ።የኤን ቲቪ ባለቤት ቭላዲሚር ጉዚንስኪ ሸሽቶ ካገር ወጣ።ፑቲን አሳደደው ሊያገኘው ግን አልቻለም።አሳልፎ የሚሰጥ መንግስት ባለመኖሩ።የቭላዲሚር ጉዚንስኪ ንብረት በነፑቲን ተወረሰ። ፑቲን ተዳፈሩኝ ያላቸው ሌሎች ሀብታሞች እንደ ሚካኤል ኮርፍድኮቭስኪ የተባሉትን የነዳጅ ዘይት አምራች ኩባንያ ባለበት ዘብጥያ ወረወራቸው። (እነ መለስ የከሰሱ፤የወረሷቸው ጋዜጦችን ማሰብ ነው። ያወደሟቸውን ነጋዴዎችም)

ጁላይ 2012 ፑቲን የኢንተርኔት ግንኙንት የሚቆጣጠር ህግ አወጣ። ቀጥሎም “ጽንፈኞችን መቋቋም” የሚል አፋኝ ህግ ደነገገ። ይህን ቢያደርግም የምራብ መንግስታት፤የዓለም የንግድ ድርጀትም አልኮነኑትም ነበር። ይህ ልክ ህወሃት መሩ መንግስት መእራባውያን መንግስታት ጉያ ስር እንደነበረበት አስከፊ ወቅት ነበር። (ህወሃት ከኢትዮጵያ ስራቶች ሁሉ ለአፈና አቻ አልነበርውም።ም እራቡ ዓለም ሰጥቶት ይነበረው ድጋፍ አደልቦ አሰነበተው)

የፍርድ ተቁማትን መቆጣጠር

2008 ቭላዲሚር ፑቲን ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጦ ጊዜው በማገባደድ ላይ ነበር።የፍርድ ተቁማትን ለመቆጣጠር የራሱን መመዘኛ አዘጋጀ።ቀድሞ የነበረው የዳኞች ብቃት መለኪያን ጨርሶ ጣሰው።ፑቲን የጸጥታ፤የፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ መሆኑን አወጀ።ቭላዲሚር ፑቲን ሲሾም በ2000 ዓ ም በጥቂት መግስት ስልጣን ቆንጮ ላይ ያሉ (richest oligarch) እና በአንድ ምስኪን ሩሲያዊ ዜጋ መካከል የሀብታሙ ይዞታ ከደሃው በ250,000 ጊዜ የበለጠ ነበር።ፑቲን በአዋጅ አንድም የውጭ ኢንቬትሜንት ያለ መንግስት ጣልቃ ገብነት እንዳይሆን አገደ። (እንደ ህወሃት ከኢትዮጵያ የፍትህ ስራትን የተጠናወጠ ሌላ ስራት አይገኝም ቢባል ፈጽሞ ማጋነን አይሆንም)

ነጻ ገበያን በማነቆ መያዝ

በጥቂቶች አገዛዝ ስር የዋለ የከበርቴ ስራት ነጻ ውድድርን ገድሎ፤የአገር ሀብትን ምጥጥ አድርጎ የሚያስቀር እንደነቀርሳ ያለ በሽታ ነው።ጤናማ ነጻ የንግድ ውድድር በአስመሳይ “ውድድር” በይስሙላ ስራ ይተካና በስልጣን ያሉ ጥቂቶች ከወዳጆቻቸውን ብቻ ይዘው ሌላውን አግልለው የሚጠቃቀሙበት ቡድናዊ ተግባር ይሆናል።የሩሲያ ታላላቅ ሀብታሞች ሃያ ቢሆኑ ነው።ሃብታቸው የሚጨምረው በአንድ ምክንያት ብቻ ነው።በቭላዲሚር ፑቲን ታማኝነታቸው ብቻ።(በኢትዮጵያም ዛሬ ከብሬአለሁ፤ሀብት አፍርቼአለሁ የሚል ያልተነካካ በጣም ጥቂት ነው። ሁሉን በክለውታል።የውጭ ኢንቭቤስትመንት እና እርዳታ ሰላም እና መረጋጋት ቀድሞት እንዲኖር ይሻል።ገበያ ማነቆን አይወድም። ሰላም እና መረጋጋትን ዛሬ ኢትዮጵያ ከሁሉም በላይ የምትሻ አገር ናት።)

የተቋማት ነጻነት መከበር አገራችንን በበጎ ይለውጣታል። ሙያን ማክበር፤በሙያ መከበር፤ብቃት እና አገር መውደድን ይዞ አዲስዋን ኢትዮጵያ የዛሬው ወጣት መገንባቱ አይቀርም።