ኢት-ኢኮኖሚ      /ET- ECONOMY

ስሚኝ እማምዬ፣ለምን ታለቅሻለሽ

በወፍጮ ላይ መጁ፣ሲጨፍር እያየሽ!!!

%e1%8b%88%e1%8d%8d%e1%8c%ae

ማምዬ ስሚኝ፣ለምን ታነቢያለሽ

በመሬት ቅርምት፣አገር ተሸጠልሽ

መብራት ወሃ የለ፣በደሳሳው ጎጆሽ፣

በመሬት ቀማኛ፣ ቀላድ መተሩብሸ

አጃና ባቄላ፣ አንቺ ነሽ የከካሽ

አሻሮና ብቅል፣ በተራ የፈጨሽ

ዓለም ተሸዓተ፣ ወያኔ እያለሽ

የትም፣ የትም ፍጪው

ዱቄት፣ ድቄቱን አምጭው

ሰው ስው ባልሸተተ ልማት

ልጆችሽ አለቁ፣ በርሃብና ስደት

ከጥንት ከጠዋቱ፣ በተካንሽው ዘዴ

ከወፍጮ ስር እህል፣ ከመጁ ስር ስንዴ

አልመሽ አድቅቀሽ፣ከሆነብሽ ሁዳዴ

ሰጪው ዱቄትሽን፣ ለንፋስ ዘመዴ፣

እንኮን የመሶቡን የጄን ተውኩላችሁ

እነ ዘር ቆጣሪ፣ እነ አጥር አጣሪ

ቀረ ዓለም ከእንግዴ፣ ከሰው ከፈጣሪ!!!

‹‹ስሚኝ እማምዬ፣ለምን ታለቅሻለሽ

በወፍጮ ላይ መጁ፣ሲጨፍር እያየሺ!!!

ጦቢያ ወፍጮ ሆና፣ መጁ ወየነልሽ

አንዱ ጡት ሲጠባ፣አንዱ ተጠማልሽ

የእንጀራ እናት ጡጦ፣ አጉርሽው እባክሽ!!!

ዱቄትሽ ተነጥቀው፣ ተራቡ ልጆችሽ

መሬት ላራሹ! ይሉ እንዳልነበር

አራሹም መሬቱም የተመነጠር!!!

የደም ግብር ለአግአዚ ጦር

እስከ መቼ እንገብር!!

ተሰደድ ከቀያቸው

ተነቀሉ ከቤታቸው

የተከሉ ከወንዛቸው

ኮበለሉ ድንበር ዘለው

የዓባይ ልጅ ውሃ ጠማው

ከውቅያኖስ ጠጡ ሰምጠው

አፈር ገፍተን፣ድቄት ፈጭተን

ታሰርን ሞተን፣የተገፋን

አብረን ተርበን የተጠማን

ዛሬም ነገም እየገበርን

ያልሰማህ ስማ ለአዋጁ አዋጅ

‹የማን ቤት ፈርሶ፣ የማ ሊበጅ

የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ!!!››

የአበው ቃል ስማ፣ እንደ እሣት የሚፋጅ

ሃይማኖት የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው

ወፍጮ ላይ ታዝሎ፣ አይጨፍርም መጅ!!!››

የእናት ጡት ነካሽ፣ ያዘው እጅ በእጅ

የአበው ቃል ስማ፣ ለሃገር የሚበጅ፡፡