ኢት-ኢኮኖሚ      /ET- ECONOMY

ቻይና ለአፍሪካ ፎረም

የሙስና ሌብነት ይብቃ!!!       

የኢትዮ ቻይና የንግድና የእዳ ጫና ስምምነት በፔኪንግ 

በሃምሳ መጫኛ ተለጉማ፣

እሷም አብዳ ሰውም አሳብዳ፡፡

የቻይና ድራጎኖች ሙስናን ኤክስፖርት በማድረግ የአፍሪካ ደሃ ሃገራት ውስጥ የመንገድ የባቡር የወደብ የአውሮፕላን ማረፍያ የኮንትራት ሥራዎች ለማሸነፍ ሹማምንቶቹን ጉቦ በመስጠት በእጃቸው መዳፍ ስር በማድረግ ሥራውን ይቆጣጠራሉ፡፡ የቻይና መንግሥት የባንክ ብድር በማመቻቸትና የስራውን ኮንትራት ለቻይና ካንፓኒዎች እንዲሰጥ ያደርጋል። በአናቱ ላይ የቻይና ሙስናና የሌብነት ንቅዘት በዓለም ተወዳዳሪ የለውም፡፡ የቻይና መንግሥት ለአፍሪካ ሃገራት የሙስና ቫይረስ ኤክስፖርት ያደርጋል፡፡  በ2018 እኤአ ቻይና አፍሪካ ፎረም የቻይና ፕሬዜዳንት ዥ ጂፒንግ  ሙስናና ሌብነትን ከሃገራቸው ውስጥ ሲያጠፉ  ከሃገራቸው ውጪ የቻይና ካንፓኒዎችና ባንኮች ሙስናና ጉቦ ኤክስፖርት ማድረጋቸውን አላጋለጡም፡፡ ቻይና የአፍሪካ ሃገራትን በእዳ ዘፍቃ ጥሬ ዕቃቸውን እየዛቀች ትገኛለች፡፡ ቻይና ለአፍሪካ ሃገራት 60 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንደምትሰጥ በፎረሙ ላይ ገልፃለች፡፡ የአፍሪካ ሃገራት በእዳ ጫና የሃገራቸውን ነፃነት ለቻይና አሳልፈው እንዳይሸጡ የአሜሪካ ሴክሬተሪኦፍ ስቴት  ሬክስ ቴለርሰን  “African  countries should be careul not to forfeit their sovereignty when they accept loans from China and carefully consider the terms of those agreements.” 1  Corrupt government? You voted for them- China pushes back at Africa summit. የቻይና መንግስት ለአፍሪካ አገራት የሙስና ቫይረስ ኤክስፖርት ያደርጋል!!!  በኢትዮጵያ የቻይና ኮንስትራክሽን ካንፓኒዎች 1.1 ቢሊዮን ብር ወይም 47.2 ሚሊዮን ዶላር ዘረፋ ወንጀል ላይ በ2017 እኤአ ተሳትፈዋል፣ በዚህም የሙስና ወንጀል የቻይና ሹሞችና 30 የኢትጵያ ሾማምንት፣ የንግድ ህብረተሰብና ደሎሎች ተይዘው ነበር፡፡  በአፍሪካ አህጉር ውስጥ  3000 ሽህ የቻይና ኢንተርፕራይዝ /ካንፓኒዎች 100 ቢዮን ዶላር መዋለንዋይና ጠቅላላ ንብረት አፍሰዋል፡፡ ሆኖም ቻይና  ሙስናን ኤክስፖርት በማድረግ ከ22 ሃገራት ውስጥ ዋነኛዋ ሆናለች፣ 39.6 በመቶ የዓለም ኤክስፖርት የያዘች ስትሆን በሙስና ወንጀል በህግ ተጠያቂ አልሆነችም፡፡  “ In 2017, a Chinese construction company was allegedly involved in embezzlement of 1.1  billion birr ($ 47.2 million) in Ethiopia and its senior official detained along with over 30 senior Ethiopian government officials, businesspeople and brokers. …China, according to the 2018 Exporting Corruption report, is one of the 22 countries with 39.6 per cent of the world’s exports but has little or no enforcement against companies bribing abroad.” 2 China is leading exporter of corruption – Transparency International.

ቻይናዊው ዜጋ የሙስና ተጠርጣሪ በእስር የሚገኘው  ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶክተር አብይ አህመድ ጣልቃ እንዲገቡ ጥሪ አቀረቧል፣ ዩዋን ጂአሊን የጃያንግሲ ጃንግሊያን ኢንንተርናሽናል ኢንጂነሪንግ ካምፓኒ (Jiangxi Jianglian International Engineering Co. Ltd (JJIEC) የኦሞ ኩራዝ 5 ፕሮጀክት ካንትራክተር ሆኖ ሲሰራ በከባድ የጨረታ ማጭበርበር የሙስና ሌብነት ተጠርጥሮ በጁላይ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ዘብጥያ ወረደ፡፡ በ2016 እኤአ የኦሞ ኩራዝ 5 ፕሮጀክት ሥራ በ550 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር  የኢንቨስትመንት ወጪ ጃጃኢኢ ካምፓኒ ለመገንባት የኮንትራት ውል አስረው ነበር፡፡ የኦሞ ኩራዝ 5 ፕሮጀክት ሥራን ብድሩን ያቀረበው  አይ ሲ ቢ ሲ የተባለው የቻይናው ባንክ ነበር፡፡ በ2015 የውጭ ምንዛሪ አንድ ዶላር ዋጋ 21.8 ብር ሲሰላ  11 ቢሊዮን 990 ሚሊዮን  ብር የፕሮጀክቱ ወጪ ነበር፡፡  ዩዋን ጂአሊን መታሰር የሁለቱን አገሮች ግንኙነት እንደሚያሻክረው ገልፆል፡፡  “Yuan Jialin was detained on July 25,2017, in relation to an alleged corruption committed while he was the head of Omo Kuraz 5 sugar project, contracted to Jiangxi Jianglian International Engineering Co. Ltd (JJIEC) …The project was contracted to a Chinese company in 2016 with an investment outlay of USD550 million obtained from a CHINESE bank ICBC.” 3 Chinese corruption suspect petitions PM’s intervention. ለዚህ ነው የአፍሪካ አህጉር ‹‹በሃምሳ መጫኛ ተለጉማ፣ እሶም አብዳ ሰውም አሳብዳ፡፡›› ኢትዮጵያ በሃምሳ የእዳ ጫናና ብድር በአፍንጫዋ ሰርኖ ተለጎሞ ህወሓት/ወያኔም አብዳ ዜጎቹን ሁሉ  አሳብዳ የተባለው የተባለው ትንቢት የደረሰው፡፡  የቻይና መንግስት በኢትጵያ ምድር የሙስና ቫይረስ ኤክስፖርት ያደርጋል!!!  

የኦሞ ኩራዝ ስኮር ልማት ፕሮጀክት፣  በሃገሪቱ ትልቁ የስኮር ልማት ፕሮጀክት የኦሞ ኩራዝ ፋብሪካ ፕሮጀክት ሲሆን በ150,000 ሄክታር መሬት ላይ የሸንኮራ አገዳ እርሻ ማልማት የሚችል ሲሆን ስድስት የስኮር ፋብሪካዎች ሲኖሩት የፋብሪካው የግንባታ ወጭ 118.3 ሚሊዩን ብር (6.4 ሚሊዩን ዶላር) ሲሆን የመንግስታዊ ልማት ኢንተርፕራይዝ የሆነው የኢትዩጵያ የውኃ ስራና ንድፍና ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ Ethiopian Waterworks Design & Supervision Enterprise (EWDSE)ሥራው የተሰጠ ሲሆን የደቡብ ክልል የውኃ ሥራዎች የ40 በመቶ የሼር ድርሻ አለው፡፡መንግስት ለስድስት የስኮር ፋብሪካዎች 225 ሚሊዩን ዶላር የመደበ ሲሆን የብረታ ብረት ኢንደስትሪ Metal and Engineering Corp (MetEC)በመከላከያ ሚኒስቴር ስር የሚገኝ የግንባታ ና የማሽነሪዎች ገጠማ ሥራ ተበርክቶለታል፡፡

ሜቴክ ከ2004 እስከ 2010 ዓ/ም የ37 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የውጭ ሀገር ግዥዎች የሚያሳይ 5 ሺህ ያህል የክፍያ ልውውጦችን የያዘ የግዥ ሂሳብ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በኩል ሌተር ኦፍ ክሬዲት በመክፈት መፈፀሙ ግልፅ ነው፡፡ ባንኩ ክፍያዎቹን ለመፈፀም ስዊፍት፣ ዌስተርን ዩኒየን ኣለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችን ተጠቅሞል፡፡ ባንኩ የሃገሪቱን የውጪ ምንዛሪ በመስጠትና ሜቴክ ተሸከርካሪዎችና ቁሳቁሶችና መለዋወጫ እያስመጣ ለገበያ ሲያቀርብ አይቆጣጠረውም ነበር፡፡ ባንኩ ለሜቴክ 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ሲፈቅድና  የውጪ ግዥ ሜቴክ ሲፈፅም የባንኩ ባለሥልጣናት ትብብር  ማድረግ ያስጠይቃቸዋል እንላለን፡፡ ሜቴክ የአስመጪና አከፋፋይ ሥራ ሲሰራ ባንኩ የውጪ ምንዛሪ በማቅረብ ተባብሮልና ያስጠይቀዋል ምክንያቱም ሜቴክ የአስመጪና አከፋፋይ ሥራ ለመስራት አልተመዘገበምና ባንኩ ይሄን ሳያረጋግጥ መስጠቱ ያስጠይቀዋል፡፡፡፡ ከሜቴክ የተፈፀሙ ክፍያዎች በቻይና መርቻንት ባንክ፣ኮሜርሻል ባንክ፣አክሲስ ባንክና ባንክ ኦፍ ቻይና  በኩል ዘረፋው በህብረት ተከናውኗል፡፡

  • የሜቴኩ ፓወር ኢንጂነሪንግ 204 የባንክ ትራንዛክሽኖች በማድረግ ሚሊዮን ዶላር በመክፈል ከቻይና ስማርት ሜትሮች፣ ተርባይኖችና ጄኔሬተሮችን አስመጥቶ አመረትኩ እያለ ሲቀልድ የነበረ ሌባ ድርጅት ምንም ቁጥጥር አልተደረገበትም፡፡
  • የሜቴኩ ሃይ ቴክ የኤሌክትሪክ እቃዎች አምራች 47 የውጪ ግዥ በመፈፀም ቴሌቪዝንና መለዋወጫ በማስመጣት ሃገር ውስጥ እንዳመረተ አድርጎ ይሸጥ ነበር፡፡
  • የሜቴኩ የአዳማ አግሪካልቸራል ማሽነሪ አምራች ኢንዱስትሪም 179 የውጪ ሃገር ግዥ በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ትራክተርና መለዋወጫ ገዝቶ በሃገር ውስጥ እንዳመረታቸው አድርጎ ሸጦል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ለሜቴክ የአስመጪና አከፋፋይ ሥራ ሳይኖራቸው የውጭ ምንዛሪ በመስጠት ሊጠየቁ ይገባል እንላለን፡፡  

የሜቴክ ግብረአበሮች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣  የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተጠያቂ ሹማምንት ለፍርድ ይቅረቡ !!!

መቐለ የመሸጉ ሌቦች በህግ እስካልተጠየቁ በመላ ሃገሪቱ ሽብር ስፖንሰር በማድረግ ህዝብ ያሸብራሉ!!!

በፓርላማው ስብሰባ ላይ፣ የትግራይ እንደራሴዎች ከቀሩ ሰንብተዋል፣ ትግራይን ገንጥለዋል!!!   

Source

{1} Corrupt government? You voted for them- China pushes back at Africa summit ( Beeijing(Reuters)Sep 5,2018)

{2} China is leading exporter of corruption – Transparency International (Sep 14, 2018)

{3} Chinese corruption suspect petitions PM’s intervention (The Reporter, Business,   2 June 2018)