በጎንደር በትምህርት ቤት አቅራቢያ የፈነዳ ቦምብ በተማሪዎች ላይ ጉዳት አደረሰ

አባይ ሚዲያ ዜና 

በጎንደር በሚገኝ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አቅራቢያ የፈነዳ ቦምብ በተማሪዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ  ተገለጸ።

ቡሬ ተብሎ በሚጠራው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አከባቢ በደረሰው በዚህ የቦምብ ፍንዳታ በትንሹ ስድስት ህጻናት የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ተዘግቧል።

በጎንደር ጠገዴ ወረዳ በሚገኘው በዚህ ትምህርት ቤት አከባቢ የፈነዳው ቦንብ አይነቱ  ኤፍ 1 የተባለ ሲሆን በፍንዳታው የሁለት ህጻናት ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

ፖሊስ ቦንቡ ተቀብሮ የቆየ እንደነበረ በመጥቀስ ጉዳቱ የደረሰባቸው ህጻናት በዋርካ ስር ተቀምጠው እያነበቡ በነበረበት ወቅት እንደነበረ ፖሊስ በተጨማሪ ገልጿል። 

የቦንብ ፍንዳታው የተከሰተበት ቦታ ከቡሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ350 ሜትር ርቀት በሚገኝ ስፍራ  ላይ እንደሆነ ፖሊስ አሳውቋል።  

በፍንዳታው ህይወታቸውን ባጡ ህጻናት የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለጽን ለህጻናቱ ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን።