ዩናይትድ ስቴትስ ታሪካዊ የተባለለትን የሞቃዲሾ ኤምባሲዋን ከፈተች

አባይ ሚዲያ ዜና 

በሶማሊያ ለበርካታ አመታት ዘግታ የቆየችውን ኤምባሲዋን አሜሪካ ዳግም መክፈቷን  አስታወቀች።

የኤምባሲው ዳግም መከፈት በሶማሊያ እና በአሜሪካ መካከል አዲስ  የዲፕሎማሲያዊ ምእራፍ እንደተጀመረ ማሳያ እንደሆነ ተገልጿል።

በ 1991 እኤኧ በሶማሊያ በነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት በሞቃዲሾ የነበረውን ኤምባሲዋን በመዝጋት አምባሳደሮቿን በአየር ማስወጧትዋ ይታወሳል።

ከ ሁለት አስርተ አመታት በሃላ አሜሪካ ኤምባሲዋን በሶማሊያ ሞቃዲሹ መክፈቷ በምስራቅ አፍሪካ በርግጥም አበረታታች ለውጥ መምጣቱን ማሳያ እንደሆነ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እንዲሁም በሶማሊያ ያለው ፖለቲካዊ ሁነታዎች ከቅርብ ወራቶች ጀምሮ መሻሻሉ በምስራቅ አፍሪካ ያለውን ተጨባጭ ለውጥ እንደሚያመለክት ተነግሯል።