ዶ/ር አብይ አህመድ ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በመሆን በባሌ ከነዋሪዎች ጋራ ተወያዩ

አባይ  ሚዲያ ዜና 

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በመሆን በባሌ ዞን ከነዋሪዎች ጋር ውይይት አደረጉ። 

ዶ/ር አብይ አህመድ በዚህ የባሌ ጉብኝታቸው የቀድሞውን  የብርታኒያ ጠቅላይ ሚንስትር ቶኒ ብሌየርን በቦታው በመቀበል በጋራ ጉብኝት አድረገዋል። 

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን እንዲሁም  የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ለማ መገርሳም በዚህ የባሌው ጉብኝት ላይ ተሳትፈዋል።

በባሌ ዞን ጊኒር ወረዳ ነዋሪዎች ጋር የተወያዩት ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በዞኑ በልማት ላይ ያሉ የእርሻ ምርቶችን ጎብኘተዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በባሌ እየተከናወኑ ያሉትን የልማት እንቅስቃሴዎችን በጎበኙበት በዚሁ ፕሮግራም ላይ አለም አቀፍ አጋሮችም እንደተሳተፉቡት ተገልጿል።