የሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣናትን የያዘች ሄሊኮፕተር ተከስክሳ የባለስልጣናቱ ህይወት አለፈ

አባይ ሚዲያ ዜና 

የሱዳንን ከፍተኛ ባለስልጣናት ይዛ ስትበር የነበረች ሄሊኮፕተር ባጋጠማት አደጋ ተከስክሳ በመውደቅ እንደጋየች ተዘገበ።

በምስራቅ ሱዳን መከስከሷ የተነገረላት ይህች ሄሊኮፕተር በውስጧ ከነበሩት ከፍተኛ ባለስልጣናት በትንሹ አምስቱ ህይወታቸው እንዳለፈ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የሟቹቹ ባለስልጣናት ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችልም የተለያዩ የዜና አውታሮች በአደጋው ዙሪያ በሚያወጡት ዘገባ ጠቁመዋል። 

በተከሰከስችው ሄሊኮፕተር ከነበሩት እና ህይወታቸው ካለፉት ባለስልጣናት መካከል የአል ገዳሪፍ ግዛት ገዢ የሆኑት ሜርጋኔ ሳሌህ እንደሚገኙበት ዘገባዎች ያመለክታሉ። 

ከአል ገዳሪፍ ገዢ  ሜርጋኔ ሳሌህ በተጨማሪ የካቢኒያቸው ዋና ባለስልጣን እንዲሁም የግዛቱ የእርሻ ሚንስትር በሂሊኮፕተሩ መከስከስ ህይወታቸውን እንዳጡ ተነግሯል። 

የግዛቱ ዋና የፖሊስ አዛዥም በዚሁ የሂሊኮፕተር አደጋ ከሞቱት መካከል እንደሚገኙበት የተገለጸ ሲሆን በአደጋው የተጎዱ ሌሎች ሰዎችን ወደ ሆስፒታል ሲጋዙ እንደተመለከቱ የአይን እማኞች ገልጸዋል።