የኢትዮጵያና የአካባቢው ፀጥታ (security) – ለ7ኛው ራዕይ ለኢትዮጵያ ጉባኤ የቀረበ (በሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ)

የኢትዮጵያና የአካባቢው ፀጥታ (Security) በሽግግር ወቅት

ለቪዥን ኢትዮጵያ 7ኛ ኮንፈረንስ

አዲስ አበባ ታህሣስ 18-19 የቀረበ የምርምር ወረቀት

ከዳዊት ወልደጊዮርጊስ

መግቢያ

ከሰላሳ ዓመት በኋላ ይህችን የተወለድኩባት፣እትብቴ የተቀበረባት፣ የተማርኩባት፣በውትድርና ሙያም፣ በሲቪልም በተለያዩከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ የታገልኩላት፣የቆሰልኩላት፣ ወድጄ ሳይሆን ተገድጄ ትቻትሄጄ የነበረችውን ክቡር አፈር ለመርገጥ ላበቃኝአምላክና ይህንንም ሁኔታ ላመቻቹልኝለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምስጋናዬታላቅ ነው፡፡ በቀሪ ዕድሜ ይህንንእመሰክራለሁ ብዬ አልገመትኩም ነበር፡፡የዶክተር አቢይን አመራርና ራዕይ እንድንደግፍ  ጥሪ ካስተላለፉት የመጀመሪያዎቹ ነኝ፡፡ Let us Rally around Prime Ministir Abiy በሚል ፅሑፍ  ድጋፌን፣ አድናቆቴን ቀደም ብዬ ገልጫለሁ፡፡ አሁንም አቋሜ ይህ ነው፡፡

በሀገራችን ውስጥ ዘለቄታ ያለው ሰላምና ዕድገት እንዲኖር ይህ ሥርአት መለወጥ እንዳለበት አጠያያቂ ሊሆን አይገባም፡፡ ይህም ማለት ኢህአዲግና ይህ ሕገ መንሥት ተለውጦ ወደ አዲስ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ካልተሸጋገርን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም አይኖርም ከሚለው  ፅንሰ ሃሳብ ተነስቼ ነው ይህንን ወረቀት ያዘጋጀሁት፡፡

ዛሬ የምንጣላው ከራሳችን ጋራ እንጂ ከውጪጠላት ጋር አይደለም፡፡ ስለዚህም የኢትዮጵያህልውና በተለየ መልኩ ልዩ የሆነ ፈተና ውስጥገብቷል፡፡

ታሪካችን ባህላችን ማንነታችን የማይደግፈውከጠባብ እውቀት የመነጨ ስተሳሰብ አሁንበሀያ እንደኛው ክፍለ ዘመን ለኢትዮጵያምለአፍሪካም ለመላው ለምም የሚያሳየው ቀርነትን ብቻ ስለሆነ ይህች የታሪክ መሰረትያላት ኢትዮጵያ ጥሩ አመራር ካላት በአጭር ጊዜውስጥ ልታጠፋው ትችላለች::እውነት ጠፍታከርማለች፡፡ የሚያድነን እውነት ነው::

ዛሬ ትኩረት እንዳደርግበት የተሰጠኝ ርዕስሴኩሪቲ በአገሪቱና በአካባቢው በሽግግር ላይያለው ተጽእኖየሚል ነው፡፡ሰፋ ያለ በመሆኑበአጭር ጊዜ ውስጥ የሚሸፈን አይደለም፡፡ ዋና፣ዋና አንኳር የሆኑትን በኔ ግምት አቀርባለሁ፡፡

በአሁኑ ዘመን በአፍሪካ ውስጥ ያለው የጸጥታሁከት ካለፈው ዘመን የተለየ ነው፡፡ ፀረ-ኮሎኒያሊዝም ጦርነቶች ወረራዎች  ዛሬ የሉም፡፡ ዛሬ በአፍሪካ የሚታዩ የጸጥታ ችግሮችየመብት ጥያቄዎች፣ የነጻነት ጥያቄዎች፣የዲሞክራሲ ጥያቄዎች፣ ከዚሁ ጋር የተያያዙበአክራሪዎች በተቋቋሙ ንቅናቄዎችየሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች ናቸው፡፡ እኔየምሠራበት የምርምር ተቋም የአፍሪካየጸጥታና የጸጥታ ስትራቴጂ ጥናት ማዕከል(AISSS) ኢትዮጵያን የመሰሉ ሀገሮች በሚያንዣብብባቸው ችግሮች ላይ ጥናትየሚያካሄድ ድርጅት ነው፡፡ ሙሉ ጊዜዬንም በዚህ ላይ ስለማሳልፍ ከብዙ ሰው የተሻለ ግንዛቤ አለኝ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት፣ በአፍሪካ አንድነትድርጅቶች ንግግርና ስምምነት መሰረት ሴኩሪቲየሚያተኩረው እንደቀድሞው በመንግሥትናበስርዓት ጥበቃ ላይ ብቻ ሳይሆን በሰውናበማህበረሰብ ላይ ነው፡፡ በእግንሊዘኛ (People Centric) ይሉታል፡፡ ሴኩሪቲ በሰብአዊመብቶች በእኩልነት በጠቅላላው በእድገትጥያቄ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ እነዚህ በመጓደላቸውለሚፈጠረው የጸጥታ ጉድለት በመጀመሪያተጠያቂ መንግሥት ነው፡፡ ከዚያ ቀጥሎየኢንተርናሽናል ህጎች ይመለከታል::

የዛሬው ውይይታችን የሚያተኩረው በህዝቦችመሀከል እና በህዝብና በመንግስት መሀከልስላለው ግጭት እና ጉዳያችን ጉዳያቸውከሆኑት የጉረቤት ገሮች ጋር ስላለው ግንኙነትነው::

የፀጥታ መደፍረስና የሀገር መሪዎች ሚና

ኢትዮጵያ በሰላም ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትለመሸጋገር በምትጥርበት በአሁኑ ወቅት፣ ብዙየጸጥታ ችግሮች እንዳሉ ይነገራል፡፡ ከኢትዮጵያከወጣሁ በኋላ ለሃያ አምስት ዓመት በአፍሪካጸጥታ በደፈረሰባቸው፣ በተፈጥሮም ሆነ በሰውሰራሽ ችግሮች  ምክንያት የመንግሥታት አቅምፈተና ላይ በወደቀባቸው ከሱማሊያ በስተቀርበሁሉም ሀገሮች በአማካሪነት ሰርቻለሁ፡፡በሩዋንዳ፣ አንጐላ፣ ላይቤሪያ፣ ሱዳን፣ ደቡብሱዳን ሴራሊዮንና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክኮንጐ የህዝብ እልቂትን፣ የመንግሥታትንናየሀገር ውድቀትን መስክሪያለሁ፤ ጽፌአለሁኝ፤ፕሮጀክቶችንም አስተዳድሬአለሁ፡፡ በሴንትራልአፍሪካ ብሊክ በሞዛምቢክ ማሊአይቬሪኮስት ለአጭር ጊዜ ጥናት ሄጃለሁ:: ስለዚህም ካነበብኩት ካዳመጥኩት ብቻ ተነስቼሳይሆን የምናገረው በቦታው ላይ ተገኝቼከርኩትና ባገኘሁት ልምድ ላይ ተመስርቼ ነው::

በሁሉም ሀገሮች የውድቀት የዕልቂትየጦርነት ዋና ምክንያቶችና ተጠያቂዎችመሪዎች ናቸው፡፡ ምክንያቶቹ የመልካምአስተዳደር ጉድለትና የመሪዎች ሆዳምነትለህዝብ ፍላጐት ተገዢ ለመሆን አለመፍቀድ፣ወይንም የህዝብን ፍላጐት ለማወቅ አውቆምለመረዳት አለመቻል ናቸው፡፡ የሀገሪቱ ታሪክመጀመሪያም፣ መጨረሻም እኛ ነን ብለውየተነሱ ብዙዎች ነበሩ፡ አሉም::በዓለም ታሪክታላላቅ ስህተቶች ተሰሩ የሚባሉት ሁሉ የታሪክድግግሞሽ ናቸው፡፡ መሪዎች ካለፈው መማርአለመፈለጋቸው፣ አለመቻላቸው፣ ጤናማአስተሳሰብን (Reason and common sense ) ለመከተል ፍቃደኛ ባለመሆናቸው የራሳቸውየግል ምኞት፣ ማለትም (Ego) እያሸነፋቸውራሳቸውን ከሚያስተዳድሩት ህዝብ በላይበማየታቸው ለእነሱም ለሀገሪቱም ውድቀትምክንያት ሆነዋል እየሆኑም ነው፡፡

ከክርስቶስ ልደት በፊት በግሪክ ሥልጣኔከተጀመረ እስካለንበት ዘመን ያሉን ታላላቅስህተቶችን (folly) መርምራ ያቀረበች የታሪክሊቅ፣ አዋቂ ባርባራ ቱክማን፣ (The March of folly) በሚለው መጽሐፍ እንዲህ ትላለች፡፡

A phenomena noticeable throughout history regardless of place or period is the pursuit by governments of policies contrary to their own interests…..why do holders of high office so often act contrary to the way reason points and enlightened self interest suggests? Why does intelligent mental process seem so often not to function?”

Misgovernment is four kinds(የተሳሳቱ አስተዳደሮች 4 ዓይነት ናቸው)

Tyranny or oppression ( ምባገነነትና ጭቆና)

Excessive ambition ( ልክ በላይ የሆንየስልጣን ጥማ)

Incompetence ( ችሎታ ማነስና የትምህርትመዳከም )

Folly or perversity ( ትክክል ሁኔታንእለመገመትና ሆን ብሎ በጥፋት መንገድ መሄድመሪዎች የዚህ ሰለባ ሲሆኑ ሀገር መውደቅና ሰላም ማጣት ትጀምራለች፡፡)

መሪዎች መፈለግና ማቅረብ የሚገባቸውየሚጠይቃቸውን፣ የሚከራከራቸውን፣ ነው፡፡በታሪክ እንደታየው ብዙ መሪዎችተታቸውን ማወቅ አይፈልጉም፡፡ ቢያውቁምማረም አይፈልጉም፡፡ ከጊዜ በኋላ ሁሉን ነገርአዋቂ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ አካባቢያቸው በዕውቀትና በተሞክሮ ሳይሆን በሌላ መሥፈሪያ የተመረጡ ሰዎች እንዲሆኑ ሲደረግ በመሪዎች ፍላጐት ብቻ ሀገር ትመራለች፡፡ መከበር ቀርቶመፈራት ይመጣል፡፡ መፈራት ሲመጣበአካባቢው ያሉት ባለሙያዎች ሁሉ መሪየሚፈልገውን እንጂ፣ እውነትን ከመናገርይቆጠባሉ:: ያለው ሕገ መንግሥት ለእነሱ አገዛዝ መቆየት እንዲያመች ማረምና መለወጥ ይጀምራሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ጥሩ ነገርንየጀመሩ መሪዎች መጨረሻቸው አያምርም፤ከክፋትም ሆነ ከሞኝነት በመነጨ የግል ውሳኔእየተመሩ ስህተት ውስጥ ይዘፈቃሉ::የወደዳቸውን ያህል ህዝብ ይተፋቸዋል፣ይወድቃሉ፣ አገርንም ለጊዜውም ቢሆን ያናጋሉ፡፡ስለዚህ ነው መሪዎቻችንን በእክብሮት ግንበድፍረት ቀርበን የህዝብን ፍላጉትና ድምፅማሰማትና የሚወስዱ እርምጃዎች ሁሉየተመከረባቸው የአብዛኛውን ህዝብ ፍላጎትማንፅባረቅ እንዳለባቸው ማስገንዘብ ያለብን::ከጥቂት ዓመታት በፊት የአፍሪካ Renaissance መሪዎች ተብለው ስማቸው ለጥቂት ጊዜ የገነነው መሪዎች የት እንደደረሱ መገንዘብ ያስተምራል፡፡ ስለዚህም ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ ከነዚህ ሁሉ ትምህርት ለመቅሰም የሚያስችል ዘመን ላይ ስላሉ ይህንን የመሰለ ታሪክን እንደማይደግሙ ሙሉ እምነት አለኝ፡፡

ለሰላምና ለሀገር ሕልውና አጣዳፊ ተግባሮች

በአገራችን ውስጥ የሰፈነውና የጸጥታ ችግርበህግ የበላይነትን አለመጠበቅ ምክንያት ነውእየተባለ ብዙ ይነገራል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥያለውን የጸጥታ ሁኔታ አሻሽሎ ህዝብእንደፈለገ መንቀሳቀስና መሥራት አብሮ መኖርእንዲችል የህግ የበላይነት ማስጠበቅ ተገቢ ነው ፡፡ ግን የህግ የበላይነት ሊከበር የሚችለውህግ ሲኖር ነው::አለ የሚባለው የሁሉምጐች ምንጭና መሰረት መንግሥትበህዝብ ምክክር (ፓርቲሲፔሽን) ያልተደነገገ ስለሆነ፣ አብዛኛው ህዝብ ይህንን ነው ብሎ ሊያከብረው አልቻለም፡፡ሊያከብረውም አይገባውም፡፡ እራሱ ህዝብለህዝብ እንዲጋጭ በጥቂቶች ተጠንቶ ከጫካበመጣ በጥላቻና ከፉፍሎ የመግዛት ርእዪትላይ የተመሰረተ ነው:: ዛሬ ጥያቄው መሆንያለበት እንዴ እዚህ ደረጃ ላይ ደረስን ሳይሆንእንዲት እስከዛሬ ህዝቡ ርስ በርሱ አልተላለቀምነው? ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ እርስ በርሱየማይተላለቀው

እግዚአብሔርን ፈርቶ፣ ወይንም ባህሉ፣ የብዙዘመናት የአብሮነትና የኢትየጵያዊነት ስሜትስላሸነፈው እንጂ፣ እንደ መንግሥቱቢሆንማ ይህ ህዝብ ከብዙ ዓመታት በፊትተላልቆ አገሪቱ ተበታትና ነበር::

የቀድሞ ፕሬዚዳንት / ነጋሶ ጊዳዳ አርቃቂ ኮሚቴ አባልና መንግሥቱን ያፀደቀው አካል ሰብሳቢ ነበሩ፡፡ የምክር ቤቱምሊቀመንበር እሳቸው ነበሩ፡፡ ለአዲስ ስታንዳርድጋዜጣ በሰጡት ኢንተርቪው ላይ እንዲህይላሉ፡፡

That is one of the major points where looking back in retrospect we did not think properly. We knew that there was no proper atmosphere where different parties could organize meetings with their members to discuss on the draft constitution before it became final. That is one of the biggest shortcomings ….እንደገና ሌላ ቦታላይ ደግሞ ሌላ ትልቅ የሽግግሩ ፓርላማምረቂቁን ካፀደቀው በሁዋሏ We should have presented it back to the people of Ethiopia in a form of referendum where the people could have had the chance to decide on whether what we formulated was according to their own wish. That we did not do. I believe it was a mistake…. I fear if something is not done this constitusion will not hold the country together.

ዛሬ የህዝብ ጥያቄ ስህተት ይታረም ነው:: ሬፈረንደም ይካሄድ ነው:: በዚህ ህግ አንገዛምነው:: ይህንን ታሪካዊ ስህተቶች አርመውየኢትዮጵያ ህዝብ የመከረበት መንግሥትእንዲረቀቅና እንዲጸድቅ ነው ጥያቄው::

የኢትዮጵያ ህዝብ / አብይ አህመድን ነውእንጂ፣ መንግስቱን ወይም ኢህአዲግንአይደለም የተቀበለው:: ኢህአዲግንማሲዋጋው፣ ሲታገለው ኖረ፡፡ መንግስቱየዘር ፖለቲካ ትኒክ ፖሊሲ መስርቶ ህዝቡንሲያፋጀው ነው የኖረው፡፡ / አብይ አህመድንህዝብ የተቀበላቸው የዘር ፖለቲካን ያጠፋሉ፣የኢትዮጵያን ህዝብ ያስተባብራሉ፣ ያስማማሉበሚል እምነት ነው፡፡ / አብይ የኢትዮጵያህዝብ አልመረጣቸውም፡፡ አንድ ፓርቲ ነውየመረጣቸው፡፡ ነገር ግን አብዛኛው የኢትዮጵያህዝብ እንደ አንድ ፓርቲ ተመራጭ ሳይሆን፣እንደ ኢትዮጵያዊ ተመራጭ አድርጐ ነውየተቀበላቸው፡፡

/ አብይ አህመድ የአንድ የብሄር ፓርቲሊቀመንበር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርበመሆናቸው ኃላፊነታቸው እንደሚጣረዝያውቃሉ፡፡ ፓርቲው ከፓርቲው መሪነትቢያነሳቸው ከጠቅላይ ሚኒስትርነትም ይነሳሉ፤በኢትዮጵያ ውስጥ ታላቅ ሁከት ይፈጥራል፡፡የብሄር ተወካይ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብተመራጭ ሲሆኑ ብቻ ነው ነው / አብይሙሉ ስልጣን ከመላው ኢትዮጵያ ተረክበውህግን ማስከበር፣ ኢትዮጵያን የዲሞክራሲያዊየሰላምና የአንድነት ሞዴል አድርገውየኢትዮጵያዊያንን ፍላጐትና የአፍሪካን ምኞትሟሟላት የሚችሉትና ታሪክ የሚሰሩት፡፡ ሐቁ ግን ይህ አይደለም፡፡

በዚህ ሁኔታ / አብይ የመጀመሪያኃላፊነታቸው ለመረጣቸው ፓርቲ ነው ወይስለኢትዮጵያ ህዝብ? የሚለው ጥያቄ አነጋጋሪነው፡፡ / አብይ ከዚህ ወጥመድ ውስጥመውጣት የሚችሉት ራሳቸውን ከፓርቲአቸውተጽእኖ አላቀው የኢትዮጵያን አጀንዳ ይዘውሲራመዱ ብቻ ነው፡፡ ይህንንም ማድረግየሚያስችላቸው ብዙ አማራጭ እንዳለ እሳቸውያውቃሉ፤ ወይዘሮ መስከረም አበራ ባቀረበችውፅሁፍ ላይ በፓርሊያመንታሪ ስርአትናፕሬዚዳንሺያ ስርዓት መካከል አማካኝመንገድ እንዳለ ጠቁማለች:: ይህንንም ሌላ አማራጭ ለውይይት አቅርባለች ጥሩ የአዋቂ ተመራማሪ ትንተና ነው፡፡እኔ ደግሞ እንድገርበት የማቀርበው ሐሳብ ዶ/ር አብይ የኢህአዲግን ሕገ መንግሥትና ፓርላማ በአዋጅ እንዲያፈርሱ፣ እሳቸው በአዋጅ በሚሰጣቸው ሥልጣን መሰረትና የጊዜ ገደብ እስከ ምርጫው ድረስ በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲያገለግሉ፡፡ አዋጁ የብሔር የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሳይሆን ሀገራዊ አጀንዳ ያላቸውን ፓርቲዎች ብቻ ተፎካካሪ ፓርቲ እንዲሆን እንዲያውጅጠቅላይ ሚንስትር አብይ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲን ወደ ኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ለውጠው ሀገራዊ አጀንዳ ይዘው ለውድድር እንዲያቀርቡ፤ የብሔር ድርጅቶች የብሔረሰባቸውን መብት ለማስጠበቅ በፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ የሲቪ ድርጅቶች እንዲሆኑ ነው፡፡ ይህ የሆነ እንደሆን የዘር ፖለቲካ ቀስ በቀስ መጥፋት ይችላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ከብሔር ፖለቲካ በላይ የሆኑ መሪ ይሆናሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም የሙሉ  የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ ሊኖረው የሚችል የኢትዮጵያ አጀንዳ ይዘው በተጠናከረ ማዕከላዊ መንግሥት ሀገርን መምራት ይችላሉ፡፡ በግርድፉም ይህንን የሚመስል ሐሳብ አቀርባለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ መጣየሚችለው የተለያዩ ማራጮችን መርምሮ ነው አዲስ ስርአት መገንባት የሚቻለው::

በዓለም ውስጥ በዘር ፓርቲ የተመሰረተየፌዴራል ሲስተም ፈልጌ አጣሁ፡፡ በዘርየተመረጠ ፓርቲ ስልጣን ላይ የወጣ የትም ቦታበዓለም ውስጥ የለም፡፡ በአፍሪካ ውስጥ ሶስትአገሮች ናቸው የፌዴራል ስርዓት ያላቸው፤ኮሞሮስ፣ ናይጄሪያና ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያ ብቻናት በዘር፣ በቋንቋ የተመሰረተ ፌዴራሊዝምያላት፡፡

ለምንድነው አዲስ ዲሞክራሲዎች በአፍሪካምበሌሎችም አሁጉሮች ቶሎ የሚፈርሱት? በሚለው ጥያቄ ላይ ሁለት ታላላቅ የፖለቲካናየታሪክ ሊቆች በጻፉት ላይ፣ Athoritorianizm and Elite origins of Democracy የሚለውን መጽሐፍመመልከት ይጠቅማል፡፡Over 2/3 of countries that have transitioned to democracy since World War II have done so under constitutions written by the outgoing regimes”

በእብዛኛው እነዚህ ሀገሮች ናቸው ሰላምናመረጋጋት አጥተው ያሉት:: ምክንያቱምገመንግስቱን የቀረፀው ያፅደቀው መንግስትበመሆኑ ነው::  በዲሞክራሲ ስርአትገመንግስት ነው መንግስትን የሚወልደው:: ኢትዮጵያ ይህንን የማድረግ እድልዋ አሁንነው:: ይህ ጊዜ ካመለጠ ትዮጵያ የዘወትርሽብርና ምንዓልባትም የመበታተን እድሏከፍተኛ ይሆናል ብዬ እገምታለሁኝ:: የአገሪቱንሁኔታ ጥሞና ለተከታተለ ይህ እማራጭየሌለው መፍትሄ እንደሆነ የሚስማማበት ይመስለኛ፡፡

ለዶ/ አቢይ ይህንን ማድረግ አስቸጋሪ መሆኑጥርጥር የለውም፡፡ ግን ይህንን ውስብስብሁኔታ ጥሰው ለመውጣት የአብዛኛው የህዝብድጋፍ ይኖራቸዋል፡፡ ይህንን የመሰሉ ሀሳቦችን ይዞ ሕዝብ የሚነጋገርበት፤ ተነጋግሮም የሚስማማበት መድረክ ለመፍጠር እና የሀገርን አቅጣጫ ለመቀየስ ሁለት ጉባኤዎች ያስፈልጋሉ ብዬ አምናለሁ፡፡  

1. የሽግግር ጐባኤ፡ሽግግር ጉባኤአስፈላጊነት

 

ኢትዮጵያ ውስጥ የዘለቄታ ሰላምን ለመመስረትየኢትዮጵያ ህዝብም ከርስ በርስ ግጭትእንዲድን ህልውናውም እንዲጠበቅየሚያስችል፣ ንድፈ ሀሳብ  የሚቀርጽ፣ ከህዝቡጋር ቀጥታ የሚያነጋግር ጉባኤ ማዘጋጀትአስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የኢትዮጵያንአቅጣጫ የሚቀይሰው ህዝብ መሆን አለበት፡፡ስለዚህ / አብይ አህመድን የሚያግዝናህዝባዊ የሆነ አቅጣጫ ሊሰጣቸው የሚችልጉባኤ በአስቸኳይ መጠራት አለበት፡፡ ሁሉምብሔረሰቦች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሰብአዊመብት ጠባቂዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣የወጣት ማህበራት፣ አክቲቪስቶች የተወከሉበትጉባኤ ተጠርቶ የጥቂት ቀናት ወይም እንደ አስፈላጊነቱ የብዙ ቀናት ውይይት አድርጐአቅጣጫ (Road Map) የሚያሳይ ውሳኔ ላይእንዲደርስ መደረግ አለበት፡፡ እዚህ ጉባኤውስጥ ለመግባት መመዘኛው በግልጽየማያጠያይቅ መሆን አለበት፡፡ በኢትዮጵያአንድነት፣ በዳር ድንበሯ፣  በህዝቦቿ እኩልነት፣በዲሞክራሲ ስርዓትና በሰላማዊ ትግልየሚያምኑ መሆን አለባቸው፡፡ ይህንን የማያሟሉድርጅቶች እዚህ አገርም፣ እዚህ ጉባኤምመገኘት የለባቸውም፡፡ አለበለዚያ የሚፈለገውንአጠቃለይ ስምምነት ላይ መድረስ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ይህ ጉባኤ የሚነጋገርባቸው ዋናዋናዎቹ፣ ህግ መንግሥቱን ስለማረም ወይንምስለመለወጥ፣ የምርጫ ቦርድን ስለመመስረትየእውነት፣ የእርቅና የፍትህ ኮሚሽንንስለማቋቋም በሚሉት ርእሶች ላይ ነው:: እነዚህእባላት የሚመረጡት በመንግስት ሳይሆንበህዝብ ነው:: ይህንን አመራረጥ ዘዴየሚያጠና ቡድን ማቋቋም የመጀመሪያው ሊሆን ይገባል::

ነዚህ ጉዳዮች ላይ የሚደረስባቸውንስምምነቶች እንዴት አድርጐ ለህዝብማቅረብና ህዝብ እንዲወያይበት ለማድረግይህን ጉባኤ የሚቀርጽ አዘጋጅ ኮሚቴከመንግሥት ተቋማት ሳይሆን ከህዝብ መካከልይመረጣል፡፡ ይህ ሁሉ ረጅም ጊዜ ሊወስድይችላል፤ ግን ይህ ፕሮሰስ እስከተጀመረ ድረስህዝቡ ወዴት አቅጣጫ እንደሚሄድስለሚያውቀው ተረጋግቶ የእለት ኑሮውንሊቀጥል ይችላል፡፡

  

2. ሁለተኛው ጉባኤ

የሰው ልጅ ኑሮ ከእግዚአብሔር ባሻገርበሀገራዊና በኢንተርናሽናል ላይየተመሰረተ ነው፡፡ መንግሥታት በሀገራቸውውስጥ በተፈጠረው የጸጥታ መደፍረስ፣ወንጀለኞችን ህግ ፊት ለማቅረብ ይገደዳሉ፡፡ይህንንም ለማድረግ አቅም ከሌላቸው ወይንምሁኔታው የማያመች ከሆነ ገለልተኛ ለሆኑአቅሙ ላላቸው የኢንተርናሽናል ፍርድ ቤቶችወይም ትሪቡናሎች ያቀርባሉ፡፡ እንደ Hague, ICC, Tribunal በሩዋንዳ ጉዳይ ላይ አሩሻ ላይየተቋቋመ ኢንተርናሽናል ትሪቡናል ምሳሌነው፡፡ በላይቤሪያና በኬንያ፣ በዲሞክራቲክሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ለደረሰው ግፍ ተጠያቂየሆኑ ወደ ICC ተልከዋል፡፡ አሁን በባለፈውዘመን የተፈጠረ አዲስ ሀሳብ (transitional justices) ወይም የሽግግር ፍትህ (restorative justices)  በተወሰኑ የአፍሪካ ሀገሮችተሞክሯል፡፡ ይህም የመጀመሪያው የሀቅ፣የዕርቅና የፍትህ ኮሚሽንን በማቋቋም ነው፡፡ዴሞክራሲያዊ ካልሆኑና ብዙ ኢሰብአዊድርጊቶች ከፈጸሙ ስርዓት ወደዲሞክራሲያዊያና ሰላማዊ ስርዓት ለመሸጋገርብሔራዊ ዕርቅና መረጋጋት ያመጣል ተብሎበብዙ ታዛቢዎችና አዋቂዎች ታምኖበታል፡፡መንግሥት የጥፋቱ አካል ሆኖ፣ ተጠያቂ ሆኖየጥፋቶች ሁሉ የበላይ ተመልካች ሆኖ ራሱይህንን አይነት ኮሚሽን ሊያቋቁም አይችልም፡፡ትርጉም አይኖረውም፤ ይህ አሰራር ከአፍሪካውስጥ ሶስት አገሮች ውስጥ ተሞክሯል፡፡በመጀመሪያ ደቡብ አፍሪካ፣ ከዚያም ሩዋንዳናላይቤሪያ በሶስቱም ሀገሮች ሰርቻለሁ፡፡የሶስቱንም ሀገሮች የኮሚሽን የስራ ውጤትበቅርብ ተከታትያለሁ፡፡ ይህ አሰራርየሚያጠቃልለው አራት ነጥቦችን ነው፡፡በወንጀል መጠየቅ(Criminal prosecution) እውነትን ፍለጋ (Truth seeking) ካሳ የመክፈል(Reparations) አዲስ ህጉችን(Reform laws) ስለማውጣት ጉዳይ ነው፡፡ ይህ (Prescriptive)ወይም ቋሚ የሆነ የአሠራር ሕግ ሣይሆን መንፈሱን ያዘለ ከሀገሩ ባህልና ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የተዛመደ አሰራር እያንዳንዱ ሀገር መፍጠር ይኖርበታል፡፡

 

ኢትዮጵያን ወደፊት የሚያራምዳት ፍትህናብሔራዊ እርቅ ነው፡፡ ብሔራዊ እርቅያለእውነት ሊኖር አይችልም በማናቸውም ወገንየተፈጸመው ግፍ ጥርት ብሎ መውጣትናመነገር አለበት፡፡ ያጠፉ ሰዎች በይፋ መውጣትአለባቸው፡፡ በዳይና ተበዳይ ፊት ለፊት መተያየትአለባቸው፡፡ የተበደለውም ካሳ ሊያገኝ ይገባል፡፡አለፍትህና አለእውነት እርቅ አይኖርም በሚለው ጽንሰ ሐሳብ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

 

በደቡብ አፍሪካ በቢሾፕ ዴዝሞንድ ቱቱ ይመራየነበረው ትሩዝ ኤንድ ሪኮንሲሌሽን ኮሚሽንለብዙ ዓመታት በይፋ ተካሂዷል፤ ውጤቱአከራካሪ ነው፤ አብዛኛው ህዝብ አውነቱበሚገባ አልወጣም፣ ፍትህም አልተሰጠምይላል፡፡ ስለዚህ ነው ዛሬ አፓርታይድ ውርስበሀገሪቱ ሙሉ ለሙሉ ያልተገፈፈው የርስበርስ ጥላቻ ገሪቱ ውስጥ በእኩልነትለመኖር የሚያስችል ሁኔታ ኮሚሽኑአላመቻቸም እየተባለ የሚነገረው፡፡ የደቡብአፍሪካ ህዝብ እንደተከፋፈለ ነው፡፡ በሶስቱ ዋናህብረተሰቦች መካከል ያለው ግንኙነትናየሚያነጋግር ጥላቻ ገና ብዙ ጊዜ ይቀረዋል፡፡እንደታሰበው በዳይና ተበዳይ ኮሚሽን ፊትቀርቦ ለምን ያን ሁኔታ እንደተፈጸመተነጋግረው፣ ተላቅሰው፣ በኋላም ተባርከውበሰላም ይኖራሉ የሚለው ግምት ብዙአከራክሯል፡፡ ምክንያቱም የአፓርታይድ መሪዎችኢሰብአዊ ድርጊቶች በፈጸሙት ላይ ፍትህአልሰጡም፡፡ ለተበዳዮችም ካሳ አልተሰጠም፤ሁሉም እውነት አልወጣም የሚሉ ብዙዎችናቸው፡፡ ከአፖርታይድ በኋላ በነጻዋ ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው ፕሬዝደንት የMr Nelson Mandela ባለቤት የነበሩት  / ዊኒ ማንዲላየባለቤታቸውን ውሳኔና ይህንን አሰራርውግዘዋል::

 

/ ዊኒ ማንዴላ ሲናገሩ እንዲህ አሉ “look at the truth reconciliation shared He should never have agreed to it what good dose a truth do how does it help any one where and how their loved once were killed and buried”

 

ከሀያ ስምንት ዓመት በፊት ያከተመው  የአርባሶስት ዓመታት የአፓርታይድ ስርአት ቁስልናመከፋፈል አልተፈወሰም፡፡

ላይቤሪያም ነበርኩኝ፤ በኮሚሽኑ ብዙስብሰባዎች ላይ ተገኝቻለሁ፡፡ ባጠቃላይ ከባድግፍ ጽመዋል የተባሉት አንዳንዶቹ በህዝብተመርጠው አዲስ መንግሥት ውስጥ ገቡ፡፡ሌሎቹም በተፈጸመው ግፍ የሚጠየቁትከተለያየ አቅጣጫ ድጋፍ ስላገኙ ትሩዝ ኤንድሪኮንሲሊዬሽን ኮሚሽን በአስራአራት ዓመትውስጥ ለሞቱት፣ ለተሰደዱት፣ ለተቆራረጡት፣ለተሰቃዩት እና ለቤተሰቦቻቸው ፍትህም፣እርቅም ሳያገኝ ካሳም ሳይከፈል በብዙ መቶሺህ ገጾች የሚቆጠር ሪፖርት አቅርቦ ተበትኗል፡፡የላይቤሪያ ችግር ኮሚሽኑን ያቋቋመውመንግሥት ስለሆነና የመንግሥቱ አባሎችአብዛኞቹ በወንጀሉ የሚጠየቁ በመሆናቸውህዝቡን የሚያሰባስብ፣ የሚያቀራርብ፣የሚያስታርቅ ባለመሆኑ ፋይዳ የሌለው ሙከራነበር:: የኢትዮጵያ ጉዳይ ይህንን አቅጣጫ የያዘይመስላል፡፡

ሩዋንዳ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችከተገደሉ በኋላ የመጀመሪያውንየዩናይትድኔሽን አርዳታ ሰጪ ቡድን የመራሁትእኔ ነበርኩ፡፡ ሬሳዎች ሲለቀሙ፣ ሲሰባሰቡአገሪቱ ከባድ ትርምስ ውስጥ ላይ ሆና የሩዋንዳፓትሪዮቲቭ ፍሮንት(Ruwanda Patrotive Front) አገሪቱን ለማረጋጋት በሚሞክርበት ጊዜ እዚያውነበርኩ፡፡ ሩዋንዳ ከዚያ እልቂት በኋላ ህዝቡንአንድ ለማድረግ ብዙ ጥረት አድርጋለች፡፡ እነዚህብዙ የተለያዩ ቅን ሙከራዎች፣ ህዝቡንአረጋግቶ ወደ እርቅ ጉዞ ማሸጋገር ተችሏል፡፡እርቅ በአንድ ቀን በጥቂት ዓመታት የሚመጣአይደለም፡፡ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ በማጨብጨብናበመተቃቀፍ፣ በመላቀስ የሚፈታ አይደለም፡፡ጊዜ፣ ጥረት፣ ግስት እና መልካም አስተዳደርይጠይቃል፡፡ በሩዋንዳ ጉዳይ ላይ እውነትወጥቷል:: ያልተነገረ እውነት የለም፡፡ ከፍተኛወንጀል የሰሩ በአገር ውስጥ ፍርድ ቤትና በአሩሻትሪቡናል(Arushia Tribunial) እንዲሁምበሄግ(Hague) ፍርድቤት ቀርበው ፍርድአግኝተዋል፡፡ በመካከል ላይ የሚገኙ ገዳዮች፣አጥፊዎች፣ ተባባሪዎች በህብረተሰቡ ውስጥተቀላቅለው እንዲኖሩ፣ ጋቻ በሚባል ባህላዊስርዓት ህብረተሰቡ የእያንዳንዱን አጥፊዎችወንጀል እየተመለከተ የሚቀጡበትንና ወይንምከህብረተሰብ ውስጥ ተቀላቅለው የሚኖሩበትንሁኔታ አመቻችቷል፡፡ አጥፊዎች ብዙ ስለነበሩ፣ተበዳዮችም ብዙ ስለነበሩ የሀገሪቱን አንድነትለማስከበር ሀገሪቱ በአንድነት ወደ እድገትእንድታተኩር እነዚህ የተለያዩ እርምጃዎችበመወሰዳቸው ዛሬ ሩዋንዳ በእድገት ከፍተኛእምርታ አስመዝግባለች፡፡ ቁስሉ በቀላል የሚረሳስላልሆነ በጥንቃቄ ተይዞ ብዙ መሻሻልአሳይቷ::

የኢትዮጵያ ሁኔታ በመጠንም በአይነትም ከዚህጋር የሚወዳደር አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥበግልጽ የወጡ ወንጀሎች ተፈጽመዋል፡፡በቅርቡ እንደተፃፈውና በይፋ በሚዲያእንድተገለፀው መንግስት በህዝብ ላይየፈፀመው በደል በጣም ዘግናኝና አስቃቂ ነበር:: ብዙ ጊዚያት በፅሁፍም በንግግርም ኢትዮጵያእንደ ሩዋንዳ እንዳትሆን መጠንቀቅ አለብንስል ብዙ እሹፎብኛል:: ” የኢትዮጵያ ህዝብእንደዚህ ያለ ጨካኝ አይሆንም:: ባህል ታሪክናእምነቱ ይህንን እንዲያድርግ እይፈቅድለትምይሉኝ ነበር:: ህግና አመራር ሲጠፋ የባህልና የእምነትን መስመሮች አልፎ በስው ውስጥ ያለክፋት ገሀድ ይወጣል:: ማን እንደዚ ያሉድርጊቶች በአገራችን ይፈፅማል ብሎ አስቦ ያውቃል? በህብረተሰቡ መካከል ዘርንአስመልክቶ ብዙ መፈናቅል፣ ብዙ የጥላቻዘመቻ፣ ብዙ ተነግሮ የማያልቁ ወንጀሎችናጭካኔዎች ተፈፅመዋል:: እነዚህ ሁሉ በህዝብመካከል በቀላሉ የማይሽሩ የአካልና የስነልቦናጉዳቶች አድርሰዋል፡፡ ህዝቡም ተባብሮ፣ተቻችሎ እንዳይኖር እንቅፋት ሆነዋል፡፡እውነቱም አልታወቀም፤ እውነቱን ከውሸትአጥርቶ አውቆ ከፍተኛ ወንጀል የፈጸመ ፍርድየሚያገኝበት ቀላል፣ ወንጀል የፈጸሙ ወይንምተባባሪ የነበሩ፣ ጥላቻ ያሰራጩ ሁሉበተበዳዮች ፊት እውነቱን ተናግረው በዳይናተበዳይ ይቅርታ ሰጪና ይቅርታ ተቀባይ አብረውሆነው ኢትዮጵያን ለመገንባት ብሔራዊየእውነት፣ የይቅርታና የፍትህ፣ ከመንግስት ነፃየሆነ ኮሚሽን መቋቋም አስፈላጊነቱ ሊፈተሽይገባል፡፡ ይህንን ሊያደርግ የሚችል ግንኢህአዴግ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ራሱ ተጠያቂስለሆነ፡፡ እነዚህ የተፈፅሙት ብዙ ወንጀሎችጥፋቶች በስርአ ተቋማት የተፈፅሙ እንጂበግለስብ የተፈፀሙ ድርጎ ማቅረብ ትልቅስህተት ነው:: እያድበሰበሱ ማለፍ ችግሮችንማካበት ነው:: ስለዚህ የመጀመሪያ ተጠያቂ ይህመንግስት ነው:: ይህ መንግስት ከሳሽምተከሳሽም ሊሆን ይችልም:: ፍትሃዊ ሥርዓትተግባራዊ ሊሆን የሚችለው የስርአት ሽግግርሲኖር ብቻ ነው፡፡ ሰላምም በመላው ኢትዮጵያሊስፍን የሚችለው ለግጭት ምክንያት የሆኑትተጠይቀው እውነት ሲወጣ ካሳ ሲከፈልናፍርድ ሲሰጥ ብቻ ነው::

 

ወጣቱ ትውልድ

ይህንን ለውጥ ያሽከረከረው ታላቁ ሞተርወጣቱ ትውልድ ነው፡፡ ኢትዮጵያን የመምራትኃላፊትም፣ ብቃትም ሊኖረው የሚገባውወጣቱ ነው፡፡ ታላቁ ፈላስፋ አርስቶትልእንዳለው፣ወጣቱ ተስፋ ለማድረግስለሚጣደፍ ስህተትም ይሰራል፤ በቀላሉምይታለላል (youth is easly decived because it is quick to hope)”   

ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ እድልም ነው፣ስጋትም ነው፡፡ ብዙ መስዋዕትነት ከፍሎየኢትዮጵያን ህዝብ እዚህ አድርሷል፡፡ ነገር ግንባለመማር፣ ባለማወቅ፣ ባለማንበብ፣ በስሜትበመገፋት፣ አውቆም ሆነ ሳያውቅ ከኢትዮጵያአንድነት ውጪ ሌላ አጀንዳ ባላቸው የብዙዎችመሳሪያ ሆኗል፡፡ ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታትበተጠና መንገድ ሲሰራጭ በነበረውየመንግሥት ፕሮፖጋንዳ በመታለሉ የአጥፊተልእኮ ያላቸው ለፈጠሩት ሐሰት ታሪክየተጋለጠው ወጣቱ  ነው:: በዚህ ሁኔታ ላይየሚገኘውን የወጣቱን አንድ ክፍል ወደኢትዮጵያ አጀንዳ ለመመለስና ገንቢ እንጂአፍራሽ እንዳይሆን የሰላምና የአንድነት ዘብእንዲሆን ብዙ ትግል ይጠይቃል፡፡ በትምህርት ቤት ከሚሰጠው መደበኛ ትምህርት ውጪ ለወጣቱ በያለበት ስለሚሰጠው ትምህርት አዲስ ስትራቴጂና ተቋማት መፈጠር አለባቸው፡፡ ካድሬዎች፣ አክቲቪስቶች አሰባስቦ በየቦታው በየቦታው ኢትዮጵያዊነትንና የጋራ ባህሎችን እሴቶችን፣ ስነምግባሮችን ለመስጠት ታላቅ አብዮታዊ ዘመቻ(Revolutionary Campain) ለመስጠት የሚያስችል ታላቅ የረዥም ጊዜ ዘመቻ (Revolutionary Campain) መከፈት አለበት፡፡ ይህ የፖለቲካ ፓርቲዎችንና የብሔረሰብ ድርጅቶችንትብብር ይጠይቃል፡፡

2018 .. አልሙንዲ ኢንዴክስእንደሚያሳየው የኢትዮጵያ ህዝብ ዲሞግራፊ0-14 43.4% 15-24 20.11% 25-5429.58% 55-64 3.9% 65 በላይ 2.8% ነውየህዝቡ አከፋፈል፡፡ ይህ የሚያሳየው ምንድነው፣64% የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ እስከ 24 ዓመት ህጻንና ወጣት መሆኑን ነው፡፡ ከዛሬ 27 ዓመት ጀምሮ ከሰባት ዓመት በላይ የሆኑት 10 እስከ 54 ያሉት ብቻ 70% በኢህአዴግ ጊዜ ያደጉየተማሩ የሰሩ ወጣቶች ናቸው፡፡ ዛሬ 54 ዓመትየሆኑት የኢህአዴግ ሲገባ 27 እድሜስለነበራቸው ወጣቶች ነበሩ፡፡ በስራም ሆነበትምህርት ዓለም ኢህአዴግ የዘር ፖለቲካየተበከሉ፣ ወይንም የተጎዱ፣ ወይንም የተጋለጡናቸው፡፡ ይህ አስደንጋጭ ነው፡፡ አብዛኛው ሥራአጥ እዚህ ውስጥ ይጠቃለላል፡፡ አብዛኛውየታሰረ  ወንድሙ፣ እህቱ የቅርብ ዘመድየታስረባቸው የተገደለባቸው በተለያዩመንገዶች የተጠቁ ሁሉ እዚህ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ይህ ህዝብ በጣም የተቆጣ ህዝብ ነው:: ይህ የሚያሳየው ኢትዮጵያን ወደ ሰላማዊዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማሸጋገር ብዙ ስራእንደሚጠይቅ ነው፡፡

በተባበሩት መንግሥታት (UNFPA) ጥናትመሰረት፣ 2050 0-24 ያለው ትውልድ ብዛትአፍሪካ ወስጥ 50% ይጨምራል፡፡ 2050 አፍሪካ በወጣት ህዝብ ብዛት ታላቋ አህጉርትሆናለች፡፡ 18 ዓመት በታች ካሉት ወጣቶችበዓለም ውስጥ ከሰላሳዎች አንዷ ኢትዮጵያነች፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 2050 መቶሰማንያ ስምንት ሚሊዮን አራት መቶሃምሳ(188,450,000) ይሆናል ተብሎይገመታል፡፡ ከናይጄሪያ ቀጥሎ በአፍሪካ ውስጥከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ያላት ሀገር ሆና ትቀጥላለች ማለት ነው:: ኢትዮጵያ ዛሬ 18 ዓመት በታች ያለው ህዝብ ብዛት 48.7% ከሠላሳዓመት በኋላ ይኸው ትውልድ ከሚወልዳቸውልጆች ጋር ተደምሮ ምን ዓይነት ደሞግራፊእንደሚኖር ስንረዳ አሳሳቢነቱ ግልጽ ነው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በዚያ ጊዜ72 ዓመት ዕድሜ ላይ ይደርሳሉ፡፡ በጡረታዘመናቸው ይህንን የመሰለ መድረክ ላይወጥተው ዛሬ ስላዘጋጁት ወይንምስላላዘጋጁት ወጣት በጸጸት ወይንም በኩራትየሚናገሩበት ወቅት ይመጣል፡፡ ይህም ኢትዮጵያዛሬ እንደምናውቃት ትቆያለች በሚል ግምትነው::

ያልተማረ፣ ስራ የሌለው፣ ማንበብ፣ ማዳመጥ፣የማይፈልግ፣ የማይችል፣ ሁሉን የሚያውቅየሚመስል፣ እውቀትን የሚያጣጥል፣ከማናቸውም ወገን በሚነዛ ወሬ እንዳመቸውየሚዋዥቅ ወጣት በበረከተ ቁጥር የኢትዮጵያሴኩሪቲ ስጋት እየከረረ ይመጣል፡፡ እያደገበሚመጣው ሥራ አጥነት ድንበር አቋርጦየሚሄደው ቁጥር ብዛት ሌላ አማራጭበማጣት ሽብርተኞች ሰፈርበመግባት(Rdicalization) በሰውና በመሳሪያ ወጥ ትራፊክ ውስጥ በመሳተፍ የአካባቢውምየሀገሪቱም  የጸጥታ ችግሮች ምንጮችየሚሆኑት የዛሬዎቹ ወጣቶች ስለሚሆኑ፣በሰውና በሰው ኃይልና ላይ ከባድኢንቨስትመንት (በማስተማር፣ በማሰልጠን፣በማደራጀት) ካልተደረገ የኢትዮጵያናየአካበቢው ጸጥታ ወደ አልታወቀ አደገኛ ሁኔታያመራል፡፡

 

 

 ህገወጥ የመሣሪያ ዝውውር

የህገወጥ መሣሪያዎች እንቅስቃሴ በኢትዮጵያውስጥ እየጨመረ መሄዱ ይነገራል፡፡ ለግልጥበቃና ዝና ከሚያስፈልገው በላይ ብዙመሣሪያዎች በአንድ ማህበረሰብ፣ በአንድቤተሰብ ውስጥ ይገኛሉ ይባላል፡፡ ይህ ከፍርሃትከስጋት፣ በመንግሥትና በክልል ሃይሎች እምነትማጣት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በቅርቡ ዘአበሻበሚለው ድረ ገጽ እንደ አዳመጥኩት፣መትረየስ፣ ስናይፐር፣ ሽጉጥ፣ ክላሽ፣ ጥይቶችናቦንቦች በይፋ  ኢትዮጵያ ውስጥ ይሸጣሉይባላል፡፡ አርፒጂ መቶ ሃያ (120,000)ብር፣ክላሽ ከስልሳ አምስት እስከ ሃምሳ (65,000-50,000) ብር፣ ሽጉጥ ከአርባ እስከ አስራሁለት (40,000-12000) ብር መግዛት ይቻላልይባላል፡፡

ኢትዮጵያ አምስት ሀገሮችን ታዋስናለች፣ከድንበሮች ባሻገር ያሉ ብዙ ጊዜ አንድ ባህልያላቸው፣ ተመሳሳይ ቋንቋ የሚናገሩ አንድቤተሰብ ናቸው፡፡ የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤቶችወይንም የድንበር ኬላዎች ካሉባቸው አንዳንድስፍራዎች በስተቀር ከሀገር መውጣትም ወደሀገር መግባትም ቀላል ነው፡፡ በመኪናየሚገቡም በቀላሉ ድንበር  ያሉ ሰዎችን ጉቦበመስጠት ያልፋሉ፡፡ በዚህም መልክ በዛሬ ጊዜየሰው፣ የድራግ፣ የመሣሪያ፣  ህገ ወጥእንቅስቃሴዎች በቀላሉ ይፈፅማሉ:: የተደራጁደላሎችና ነጋዴዎች በሽብርተኞች አማካይነትእንደልብ መንቀሳቀስ ችለዋል:: ኤኤክስኤክስአፍሪካ (AXX Africa) የሚባለው በእንግሊዝአገር የሚገኝ መረጃ ኢንቲትዩት ባለፈው ነሐሴወር “Arms Trade in the Horn of Africa” በሚልርእስ ባወጣው ጥናት ላይ ጅቡቲ ዋና የህገ ወጥ መሣሪያ ማመላለሻ ማዕከል እየሆነች መሄዷን ዘግቧል፡፡

ነጋዴዎች መሳሪያዎች የሚያገኙት ጦርነትካለባቸው ሀገሮች ነው፡፡ በጅቡቲ የሚመጣውከየመን ጦረኞች የሚገዛ ነው፡፡ ከሱማሊያ፣ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳን ከነሱ አዋሳኝ ሀገሮች፣ሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ከዲሞክራቲክኮንጐና ከሊቢያ መሣሪያዎች በገፍይዘዋወራሉ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በመሣሪያአጠቃቀምና አያያዝ ልውውጥ ንግድ ለየት ያለ አውጥቶ የጠበቀ ቁጥጥር ካላደረገ ማስከበር ከመንግሥትና ከክልሎች ቁጥጥርውጭ ሆኖ ሀገሪቱ ወደ ውድቀትእየተንሸራተተች ትሄዳለች፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት በኡጋንዳ ካምፖላ ዋናመስሪያቤቱ ለሆነው ዩናፍሪ ( UNAFRI) በአፍሪካ ውስጥ የቀላል መሣሪያዎች ወጥእንቅስቃሴ ጥናት እንዳደርግ ተመድቤ ለአንድዓመት ጥናቱን አከናውኛለሁ፡፡ ጥናቱንም ውጤት አፍሪካ አህጉር የሚገኙ ሀገሮች ፖሊሲ ኮሚሽነሮች  ስብሰባ ላይ አቅርቤአለሁ፡፡አቅራቢው እኔ ስለሁንኩ ይመስለኛል፤የኢትዮጵያ መንግሥት ተጠሪ አልላከም፡፡ ይህንጥናት ባደረኩበት ጊዜ በመሳሪያ አምራቾች፣በመሳሪያ ደላሎች፣ መሣሪያውን በሚያጓግዙትየትራንስፖርት ባለቤቶች እና በተጠቃሚዎቹመካከል (End users) ያለው ግንኙነት የተወሳሰበመሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ ምንም እንኳን ይህ ጥናትትንሽ የቆየ ቢሆንም ሁኔታው ከመባባስበስተቀር ሆዳሞች መሣሪያ ለመሸጥ ሲሉበአንድ ሀገር ውስጥ እንዴት አድርገው ሽብርናስጋት እንደሚፈጥሩ ለዚህ ኔታየመንግሥት አካላት ሳይቀሩ ተባባሪእንደሚሆኑ የሚያመለክት ነበር፡፡

ከአራት ዓመት በፊት በተደረገ ጥናት The Gulf of Guinea ብዙ የምዕራብ አፍሪካ ጠረፎችንየሚያካትተው ባህረ ሰላጤ The most dangerousmaritime zone in the world ተብሎ ነበር፡፡ ከዚያበፊት የኛው አጠገባችን ያለው Gulf of Eden ነበር አስጊው አካባቢ፡፡ ቀደም ብሎከኮሎምቢያ ድራግ ካርቴል በአውሮፓ አድርገውየሚያመላልሱት   ወጥ እንቅስቃሴምመንገድ ለውጦ አሁን Gulf of Guinea የተመረጠ ሆኗል፡፡ Gulf of Guinea አድርጐእስከ ሊቢያና በሜዲቴራንያን ጠረፍ አገሮችለማጓጓዝ በጣም ቀላል ሆኖ አግኝተውታል:: ከባህረ ሰላጤው ጀምሮ እስከ ሜዲታራንያንባህር ድረስ በቦኮሃራምና በሌሎች ህገወጥእንቅስቃሴዎች የተወረረ ምድረበዳ ኮሪደርፈጥረው አለብዙ ችግር ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ይህእንቅስቃሴ መሣሪያዎችን ይጨምራል፡፡ከጥቂት ዓመታት በፊት ጊኒቢሳውም Narco Capital of the Wrold ተብላ ተሰይማለች፡፡የጊኒቢሳው አድሚራል ዋናው ለዚህ ድራግናመሳሪያ አመላላሽ ካርቴል ኃላፊ ነው ተብሎተጠርጥሮ FBI ተይዞ ፍርድቤት ቀርቧል፡፡ብዙም የመንግስት ባለስልጣኖች ከዚህ ጋርበተያያዘ ፍርድ ቀርበዋል:: ይህን ያነሳሁበትየመንግስት ባለስልጣኖ በዚህ የተወሳሰበ ሕገ እንቅስቃሴ ውስጥ ዋና ተዋንያን ሊሆኑእንደሚችሉ ለማሳየት ነው::

ወጥ መሣሪያ እንቅስቃሴ ብዙ ዘርፎችንስለሚነካ ጦርነት ለመቀስቀስም ለማፋፋምምየንግድ ብቻ ሳይሆን እንደ ፖለቲካ አጀንዳየተያዘ ስለሆነ ግና ቁጥጥር ያስፈልገዋል፡፡

የፅጥታ ሀይሎች ጥራት

የመከላከያና የፖሊስ ሀይሎች በአመራር ደረጃም ሆነ በሠራዊቱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ብቃትአላቸው ብሎ ለመናገር ያስቸግራል፡፡ አንዳንድየኢትዮጵያ የጦር መሪዎችን ሩዋንዳም፣ ሱዳን፣ላይቤሪያም አግኝቻዋለሁ፤ አልኮራሁባቸውም፡፡እኔ በተለያዩ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ውስጥ የሰለጠንኩ ወታደር ስለሆንኩኝ መመዘንእችላለሁኝ:: ብዙ ላላቅ አዋቂ እዛዦችም ጋርስርቺአለሁኝ:: ዛሬ በሜቴክ ሙስና የተያዙ ለክስየቀረቡ ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸው የሰራዊቱአባሎች በሥነ ምግባራቸውና በዕውቀታቸውየሚያሳፍሩ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ህዝባችንበኃፍረት ነው የተሸማቀቀው:: በየደረጃው ያሉይህንን የመሳሰሉ አለቆች ለፀጥታው መደፍረስመፍትሔ ሳይሆኑ ችግሮች ይሆናሉ፡፡

በየክልሉ ያሉት ኃይሎች ፖሊስና ልዩ ኃይልየሚባሉት የክልሉን ጥቅም ወይም መመሪያየሚጠብቁ እንጂ በፌዴራል መንግሥትየሚመሩ ባለመሆናቸው ታላቅ ቀውስፈጥሯል፡፡ የፖሊስና የልዩ ኃይሎች ገደብየሌለው ሥልጣን አደገኛ መሆኑ ለሁሉም ግልጽነው፡፡ በመከላከያ ኃይልና በልዩ ኃይል የሥራኃላፊነት ልዩነት የለም፡፡ በተግባር ሲታይ በክልልያሉ ፖሊስና ልዩ ኃይሎች ኃላፊነታቸውንየሚመለከቱት ሰፋ ባለ ኢትዮጵያዊነት መነጽርሳይሆን በክልላቸውና በብሔራቸው መነጽርነው:: የክልል መንግሥቱ የፌዴራል መንግሥቱን ይጣረዛል:: የክልሉ ሠራዊቶችይዋጋሉ፣ ይገላሉ:: ልክ የሁለት ሀገሮች ጦርነትየሚመስል በየድንበሩ ጦር አሰልፈው ያጠቃሉ፤ይከላከላሉ: አቅም ሲያጥራቸው ፌዴራል መንግሥቱን ኃይሎች ይጠራሉ ባላቸው ኃይልከሥልጣናቸው በላይ የሆነ ምንም ነገር የለም፡፡

ወደ ምርጫ እየተቃረብን ባለንበት ወቅትእንዴት አድርጐ ነው አንድ ክልል አቋርጦ ሌላክልል ሲገባ፣ ሌላ አገር የገቡ በሚመስልበተወጠረ የፖለቲካ ሁኔታ ህዝብ ተንቀሳቅሶየፖለቲካ ፖርቲዎች እንደልብ ተናግረው፣አስተምረው ህዝቡን አደራጅተው ነው ለምርጫ የሚያዘጋጁት? ይህ ስንት ዓመት ሙሉካድሬዎች ሲታጠብ የነበረ ሰራዊት እንዴትአድርጐ ነው ኢህአዲግ ውጪ ለሌላ ተመራጭሁኔታውን ማመቻቸት የሚቻለው? ከስር ጀምሮ  ኢትዮጵያ በሚለው ታላቁ ስእል ክልል ውስጥለማሰብና ለመስራት እንዲቻል በሠራዊቱ ውስጥ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም ብዙ ይቀራል፡፡

 

ትጥቅ መፍታትና ከህብረተቡ ጋር መቀላቀል

(Demobilization Re-Intigration)

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውየትጥቅ ትግል በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮችከምናያቸው የተለየ ቢሆንም፣ የትጥቅ ትግልንበመጠቀም መንግሥትና ሥርዓትንእንለውጣለን ብለው የተነሱ ኃይሎች ነበሩ፡፡አሁን / አብይ እንደ ጀመሩት፣ እነዚህኃይሎች፣ የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር እየተመለሱ ናቸው፡፡ እኔ የአንጎላ ጦርነትሲቆም፣ የትጥቅ መፍታትና ከህብረተቡ ጋርመቀላቀል (Demobilization Re-Intigration Technical Officer) ሆኜ በተባበሩት መንግሥታትፕሮግራም ውስጥ ሰርቻለሁ፡፡ ትጥቅማስፈታትና ከህብረተሰቡ ጋር መቀላቀሉለዘለቄታዊ መፍትሔ ወሳኝ ነው፡፡ ይህምአካሄድ ሥርዓት አለው፡፡ ሥርዓቱ ካልተጠበቀሰላምን ሊያደፈርስ የሚችል ሁኔታ ይፈጠራልተብሎ ይታመናል፡፡ የአንጎላን ፕሮግራም ስንሰራከሞዛምቢክ ልምድ ለመውሰድየሞዛምቢክንም ተሞክሮ ፈትሸናል፡፡ የናሚቢያነፃነት በሁዋላ የነበረውን የትጥቅ መፍታትናወደ ሰላማዌ ይወት መቀላቀል ስኬታማየሆነውን እንደ ሞዴ አድርገንተጠቅመንበታል፡፡ የሩዋንዳ Ministry of Rehabilitation Social Intigraion ሲቋአማካሪ ሆኜ ሰርቻለሁ፡፡ የታጠቁትንምያልታጠቁትንም Genocide ጊዜየተፈናቀሉትን፣ የተሰደዱትን መልሶ ህብረተሰቡውስጥ ለመቀላቀል እንዲቻል የተቋቋመሚኒስትሪ ነበር፡፡ እነዚህ የተለዩ ሁኔታዎች ቢሆኑም ከልምዶቻቸው ብዙ ተመክሮ መውሰድ ይቻላል፡፡

ትጥቅ መፍታት በመንግሥስትና በታጣቂኃይሎች መካከል ሚኖር ስምምነትይጀምራል፡፡ በስምምነቱ መሰረት የታጠቁኃይሎች ስም ዝርዝር፣ የታጠቁት መሳሪያብዛትና ዓይነት ይመዘገባል፡፡ ትጥቅ የፈቱትኃይሎች አንድ ማረፊያ ሰፈር ይገባሉ፡፡ በዚህምማረፊያ ሰፈር ህብረተሰብ ውስጥ ተቀላቅለውበሰላም እንዲኖሩ የሚያስደርጋቸውን ትምህርትይቀበላሉ፡፡ በሀገሩ የመላከያ ኃይል ውስጥለመቀላቀል ብቃትና ፍቃደኝነት ያላቸው ወደሰራዊቱ ይቀላቀላሉ ሌሎቹም እንደጥያቄአቸው ሥራ እየተፈለገ ይሰጣቸዋል፡፡በሙያ ለመሰልጠን የሚፈልጉ ትምህርት ቤትእንዲገቡ ይደረጋል፡፡ የመቋቋም ችግርያለባቸው በስምምነቱ መሰረት እርዳታይደረግላቸዋል፡፡ ይህ ሳይደረግ የቀድሞተዋጊዎችን ህብረተሰቡ ውስጥ እንዲቀላቀሉማድረግ ለሰላም ጠንቅ ሊሆ ይችላል::ይህንንም በተመለከተ ብዙ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን እገነዘባለሁኝ፡፡

 

ራስን የመግለጽ ነፃነት (Freedom of Expression)

ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትና ግዴታበተለይም አዲስ የዲሞክራቲክ ስርዓትበሚገነቡ ሀገሮች በሚገባ ባለመታወቁ፣በአንዳንድ ሁኔታ ውስጥ ሰላምን ሊያናጋይችላል፡፡ በአንድአንድ ሀገር እንደ ሁኔታው፣በግዴታና በመብት መካከል መስመር መዘርጋትይኖርበታል፡፡ ችግሩ መንግሥት ትንሽ ፍንጭሲያገኝ፣ ስንዝር ሲሰጡት አንድ ክንድይወስዳል፡፡ የፀረ ሽብርተኛ አዋጁ በምሳሌነትሊጠቀስ ይችላል፡፡

በ2001 እ.አ.አ. ከደረሰው የአሜሪካ የሽብርጥቃት (Nine Eleven) በኋላ ብዙ ሀገሮች የፀረሽብርተኛ አዋጅ እንዲኖራቸው አሜሪካአበረታታለች፡፡ በአፍሪካና በሌሎች አህጉሮችያሉ መንግሥታት ይህንን ሀሳብ ያለምንምማንገራገር ቀለብ አድርገው ለራሳቸውመጠቀሚያ አደረጉት፡፡ ሽብርተኝነት የጠራዓለም አቀፍ የሆነ ትርጉም ስለሌለውእያንዳንዱ መንግሥት እንዳመቸው እየተረጐመነፃነትን፣ ክርክርን፣ ሰላማዊ ሰልፎችን፣በአጠቃላይ ስላማዊ ትግልንና የሀሳብ መግለፅንነፃነት ማጥቂያ ህጋዊ ዘዴድርገውጠቅመውበታል::

ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ እውነትና ውሸትንመለየት በጣም ያስቸግራል፡፡ የመንግሥትንሚዲያ እያዳመጥን ምንጫችን ከአንድ ወገን ብቻ ሲሆን እውቀታችን ውስን ይሆናል፤ወይንም የመንግሥስት መሣሪያ እንሆናለን፡፡የግል ሚዲያዎች የሚናገሩትን፣ የሚጽፉትንበሁሉም ሶሻል ሚዲያና ሌሎችም ወይንምገንዘብ ለማግኘት፣ ወይንም ሰንሴሽንለመፍጠር የፖለቲካ ተልዕኮ አጀንዳ ያላቸው፣ወይንም የማያውቁ ሰዎች ሚዲያ ለመቅረብእድል በማግኘታቸው የሚናገሩት የሚጽፉትሁሉ ሀገሪቱን ምን ያህል አደጋ ላይ እየጣለእንደሆነ ማጥናት አስፈላጊ ነው፡፡

በተለይ ወጣቱ ከብዙ ዓይነትአስተማማኝነታቸው ካልተረጋገጠ ምንጮችበሚያገኘው ዜና ወይም ወሬ እየተዋከበለመወገን፣ ለማገዝ ይቸኩላል፡፡ ይህ ወጣትትውልድ ብዙ የማያነብ ግን ብዙ የሚናገርለማሞጐስም ለማውገዝም የሚቸኩል፣ ሶሻልሚዲያ ላይ ጥቂት አረፍተ ነገሮችን አንብቦበታላቅ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ አቋምመውሰድ የሚደፍር በስድብ፣ በዘለፋ፣የሃቀኞችን ልሳን የሚዘጋ፣ ከአንድ ከሚፈልገውአቅጣጫ ብቻ መረጃዎችን የሚቀበል፣ ሳያውቅሳያመዛዝን የጠላት መሣሪያ ሊሆን የሚችልበመሆኑ ለሀገራችን ጸጥታ ትልቅ ስጋትይሆናል፡፡

አሁን ኢትዮጵያ ባለችበት በጣም ስስ፣ በቀላሉየሚሰበር (Fragile) አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ ውስጥአንድ የሀሰት ወሬ ብዙ ህዝብ ሊያስጨርስየሚችልበት ሁኔታዎች ብዙ ናቸው:: በሚዲያአማካኝነትም ሆነ በአደባባይ ወጥቶየሚነገረው ገደብ እንዲኖረው አንድ መፈጠር አለበት፡፡ አሁን ባለበት ዲጂታልጀነሬሽን መቆጣጠር በጣም አስቸጋሪ ቢሆንምበማስተማር፣ ግዴታንና ሀላፊነትን ከማሰወቅጋር የተያያዘ ሊሲ ሊቀየስ ይገባል::

ይህ በኢንተናሽናል ግም የተደገፈ ነው፤የአፍሪካ ቻርተር Human and Peoples Right Freedom of Speech Shall be exercised in respect of the right of others collective security morality and common interest ይላል፡፡ ከዚያም ቀጥሎይህ ገደብ ዓላማው ምን መሆን እንዳለበትበዝርዝር አስቀምጦታል፡፡ በእንደዚህ ዓይነትየሽግግር ወቅት በግልጽ የኢትዮጵያን አንድነትየማይደግፉ፣ ድብቅ አጀንዳ አላቸው ተብለውየሚጠረጠሩ አናርኪስቶች ይሁኑ፣ በተለያዩምክንያቶች የተቆጡና የግልም ችግርያለባቸው፣ ሀገር የመከፋፈል፣ ህዝብ የሚያጣላህዝብን ከማያቀራረብ ከይቅርታ፣ ከፍቅርየሚያርቁ በሀሰት ላይ የተመረቱ ማስረጃሌላቸው ታሪክና ዜና በሚያስራጩድርጅቶችና ግለሰቦች ትኩረት መደረግአለበት፡፡

የሚዲያና የፓለቲካ ድርጅቶች የገንዘብምንጫቸውን ለመንግሥት ማሳወቅአለባቸው:: ይህ በሁሉም ዴሞክራቲክ ሀገሮችበሕ የተደነገገ ነው:: ይህም የኢትዮጵያየውስጥ ፓለቲካና የፀጥታ ሁኔታ በውጭጀንዳ እንዳይመራ ያረጋግጣል:: በንግግርበጽሁፍና በመሳሰሉት freedom of expression ነፃነት ሽፋን አድርገው የኢትዮጵያን አንድነትየሚጐዱ ግለሰቦች ካሉ የሚታገዱበት ኖር ይገባል::

 

የአካባቢ ሁኔታና ሽግግር

የአካባቢያችንን የፀጥታ ሁኔታ ከውስጥየፀጥታ ሁኔታ ለይቶ ማየት አስቸጋሪ ነው፡፡የኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣የዲሞክራሲ መመስረት፣ የሰብአዊ መብትመጠበቅ፣ ከአካባቢው ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው፡፡የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርብም በሩቅምበአይነቁራኛ የሚከታተሉ ብዙዎች ናቸው፡፡የአፍሪካ ቀንድ በአሁኑ ጊዜ The most militarized zone in the world ይባላል፡፡ ታላላቅሁኔታዎች በዓለም በተለይ በመካከለኛውስራቅና በአረቡ ለም ሲከሰቱ አዲስ የሃይልአሰላለፍ በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ እየታየ ነው፡፡የመካከለኛው ምስራቅ የፖለቲካ ሁኔታ ግልጽበሆነ መንገድ ለሁለት መከፈሉና የአፍሪካቀንድ ከዚህ ሁኔታ በቀጥታና በተዘዋዋሪመንገድ ከመቸውም ጊዜ ይልቅ ትኩረትየሚሰጡት ቦታ መሆኑ ኢትዮጵያን በቀጥታይመለከታታል::

ኤርትራ

ስለጎረቤት ሀገሮች ስንነጋገር በመጀመሪያ ከላይከጠቀስኩት ሁኔታ ጋራ ያልተያያዘ ስለ ኤርትራናኢትዮጵያ ግንኙነት ትንሽ መናገር እፈልጋለሁ፡፡እኔ የኤርትራ ፌዴሬሽን ከመፍረሱ ስምንት ወርበፊት በምክትል የመቶ አለቃ ማዕረግ ኤርትራነበርኩ፡፡ ፌዴሬሽኑ የፈረሰ ዕለት ጦር ይዤአስመራ አካባቢ ተሰማርቼ ነበር፡፡ ዛን ጊዜጀምሮ የኤርትራን ሁኔታ በቅርብ ተከታትያለሁ፡፡ኤርትራ በውጊያ ግንባር ተሰልፌአለሁ፣ክፍለሀገሩን በበላይ አስተዳዳሪነት መርቻለሁ፡፡ከአገር ከወጣሁም በኋላ ከኤርትራ መንግሥትከፍተኛ አባሎች ጋር በግል ጓደኝነትም፣በፖለቲካም በቅርብ ሰርተናል፡፡ የኤርትራንህዝብ፣ የኤርትራን ፖለቲካ ከብዙ ሰዎች በተሻለሁኔታ አውቃለሁ፡፡

የኢትዮጵያና የኤርትራ እጣ ፋንታ ወደፊትአብሮ እንጂ ተለያይቶ እንደማይሆንምመገንዘብ ይቻላል፡፡ እኔ የአንድነት ወገንነበርኩኝ:: አልተቻለም፤ ነገር ግን ተቀራርቦመስራት ለጋራ ጥቅም፣ ለጋራ ህልውናአማራጭ የለውም፡፡ በመንፈሴ አሁንምኤርትራንና ኢትዮጵያን መለየት አልችልም፡፡ከዚህ በፊትም፣ ከዚህ በኋላም ኤርትራኢትዮጵያ ነች፤ ኢትዮጵያ ኤርትራ ነች ብዬ ነውየማምነው፡፡ ግን በግልፅ መታወቅ ያለበት ኤርትራ እሯሳን የቻለች ዳር ድንበሯ በዓለም አቀፍ ሕግ የታወቀች ሀገር sovereign state ነች፡፡ የሁለቱ መንግሥታት መለያየት የህዝቡንአብሮነትና አንድነት አይለውጠውም፡፡በኤርትራ ላይ የሚመጣ ጉዳት ኢትዮጵያንይጎዳል፤ በኢትዮጵያ ላይ የሚመጣ ጉዳትኤርትራን ይጎዳል፤ ይህ የመልካም ጉርብትናፖሊሲ መሰረታችን መሆን አለበት:: / አብይበወሰዱት እርምጃ በግል በጣም ተደስቻለሁ፡፡ The moment of Truth: Eritrea and Ethiopiaበሚል ርእስ ድጋፌን ለመግለፅ በወቅቱበሰፊው የተነበበ ጽሁፍ አቅርቤአለሁ፡፡

በሁለቱ ህዝብ መካከል ብዙ ጉዳት ደርሷል፡፡ይህንን ያህል ዘመን በኤርትራ ምድር ላይበአንድነትና በነፃነት ኃይሎች መካከል ውጊያሲካሄድ ይህ ጦርነት ህዝባዊ ጦርነት(Civil War) ሆኖ አያውቅም፡፡ ጦርነቱ በሁለቱ ኃይሎችመካከል ነበረ፡፡ ህብረተሰቡ ተጋብቶ ተዋልዶባሕሉን አክብሮ እንደ አንድ ቤተሰብ ተቀራርቦጦርነቱ እንዲቆም ሰላማዊ ኑሮ እንዲኖርእየተመኘ እየፅለየ እዚህ ደርሰናል፡፡ በሁለቱምወገን ብዙ ተዋጊዎች አልቀዋል፡፡ የኤርትራተዋጊዎች የሚገባቸውን ክብር አዲሱመንግሥት ሰቷቸዋል፡፡ ነገር ግን አሁንየተጀመረው አብሮ የመኖርና የማደግ ፍላጐትናምኞት እውነት ሊሆን የሚችለው ህዝባዊ ዕርቅሲፈፀም ብቻ ነው፡፡ የሁለቱ መንግሥታትመሪዎች መጨባበጥና መተቃቀፍ መሰረታዊየሆነ ብሔራዊ ዕርቅ አያመጣም፡፡ በኢትዮጵያበኩል በሰላሳ ዓመት ውስጥ ከመቶ ሺህ በላይወታደሮች በኤርትራ ምድር ላይ አልቀዋል፡፡ቤተሰቦቻቸው ከመቀሌ ጀምሮ እስከ አዲስአበባና ከዚያም ባሻገር በእያንዳንዱ የኢትዮጵያክፍለ ሀገራት ከተሞችና መንደሮች ተበትነውበጉስቁልና የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ቆስለው፣ተሰናክለው፣ የተጣሉም የተረሱም ብዙዎችናቸው፡፡ ኤርትራ ውስጥ የሞተ፣ የቆሰለ፣ ዘመድየሌለው ለማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ ጦርነቱየታሪካችን ጠባሳ ነው፤ ታሪክ ይዘግበዋል፡፡የዛሬውና የሚመጣው ትውልድ ግንየተፈጸመውን ታሪክ ትቶ እንዴት እንደዚህ ያሉጥፋቶች እንደደረሱ የሁለቱን ህዝቦች የታሪክቅርበት ያገናዘበ ውይይት በማካሄ ከእንግዲህወዲያ መቼም እንደዜህ ያለ ሁኔታ ይፈጠርም(Never again) ብሎ ተነጋግሮ፣ ተላቅሶ፣ ተቃቅፎ፣እውነቱን አውቆ፣ እርቅ የሚመርትበትህዝባዊ ጉባኤ ማመቻቸት ተገቢ ነው::

ይህም ጉባኤ የትዮጵያ ሰማዕታትምየሚከበሩበት፣ የሚታወሱበት ኃውልት ከኤርትራ መንግሥት ጋር ተነጋግሮ ፈቃድ እንዲሰጥና በመንግሥት ወጪ ሳይሆን ከህብረተሰቡ በተዋጣ ገንዘብ እንዲቆም ይነጋገርበታል፡፡ መንግስትም ድጋፍ ሊሰጥይገባል:: በኤርትራ ምድር ላይ የፈሰሰው ደም፣ያለፈው ሕይወት በሁለቱም ሀገሮች ታሪክውስጥ አቻ የለውም፡፡ ይህንንም የመሰለ ጉባኤበሁለቱም ህዝቦች መካከል የሃይማኖትአባቶች ወገኖቻቸውና ዘመዶቻቸው፣የጠፋባቸው፣ የተጎዱባቸው ሰዎች፣ በሁለቱምወገን በውጊያው ወቅት የነበሩ ታጋዮች፣መስካሪዎች፣ ታሪክ አዋቂዎች ተሰባስበውይህንን ምዕራፍ ዘግተው ለታሪክ አስረክበውበሰላም እንዲኖ ማድረግ ተገቢ ይመስለኛል፡፡ይህ ዘላቂ ሰላም ያስገኛል ያረጋግጣል፡፡

ሶማሊያ      

ሶማሊያ 1978 ..  ኢትዮጵያን በወረረችበትጊዜ እኔ በውጭ ጉዳይ ሚኒስት ቋሚ ተጠሪነበርኩ፡፡ ይህንን በወቅቱ እጅግ አሳሳቢ የሆነሁኔታ International Community ለማስረዳትናድጋፍ ለማግኘት ወደ United Nation delegation መርቼ ሄጃለሁ፡፡ በገለልተኛ ሀገራት መንግሥታትስብሰባ አቤቱታችንን አሰምተናል፤ ድጋፍጠይቀናል፡፡ በኩባ፣ በአውሮፓ፣ በላቲን አሜሪካ፣በየመን ተመላልሰን ድጋፍ ለማግኘትበዲፕሎማቲክ ዘርፍ ብዙ ትግል ድርገናል::

በሜዳ ላይ የሶማሊያ ጦር ጅጅጋን ያዘ፤ሐረርንም፣ ድሬደዋንም ከበበ፤ አርሲ፣ ባሌሐረርጌን ማስታጠቅ ጀመረ:: በዚያን ወቅትበኮለኔል ብርሃኑ ባዬ የሚመራ ልጅ ጌታቸውክብረት፣ ልጅ ሚካኤል እምሩ እና እኔ ያለንበትልዑካን ቡድን ሶቪየት ዩኒየንን ለመማፀንናሶማሊያ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያቆሙአስራ ሰባት ቀናት የቆየ ውይይት አካሂደናል፡፡ሶማሊያ  ወረራ የፈጸመችው ነፃነት ካገኘችበትጊዜ ጀምሮ በሕ መንግሥቷ አንቀጽ 6 እናበባንዲራዋ ላይ የተመለከተውን አምስቱንየሱማሌ ህዝብ የሚኖርባትን ሀገሮች አጠቃላታላቋ ሶማሌያን ለመፍጠር ነበረ፡፡ ለዚህምወረራ ሽፋን እንዲሆን የምዕራብ ሶማሊያነፃነት ንቅናቄ ግንባር (Western Somalia Libration front) ብላ አቋቋመች፡፡ መሪዎቹምከዚያው ከሱማሊያ ጦር ውስጥ ኃላፊዎችየነበሩ ታላላቅ የጦር መሪዎች ነበሩ፡፡ ONLF መሪ በዚያድ ባሬ መንግስት ወቅት ከፍተኛመኮንን የነበረው Rear Admiral Mohamed Omar Osman ነው፡፡

ሶማሊያ ከነፃነት ጊዜ ጀምሮ ወቅት እየመረጠችኢትያጵያን ወራለች፡፡ በጄኔራል መንግሥቱነዋይ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጊዜኢትዮጵያ ተዳክማለች ብላ በዳኖት በኩልጦርነት ከፈተች፤ ተሸንፋ ተመለሰች፡፡ በደርግጊዜ አገሪቱ በአብዮተኞችና በፀረ አብዮተኞችመካከል በነበረው የሥልጣን ትግል፣ ከዚያምበሀገሪቷ ሰሜናዊ አካባቢ የነበረው ጦርነትተፋፍሞ ስለነበረ ኢትዮጵያ ተዳክማለች በሚልግምት በሶቭየት ዩኒየን የመሣሪያ ድጋፍ፣ ህዝብያለቀበት ወረራ ፈጸመች፡፡ ለዚሁም ሽፋንያደረጉት የዚያድ ባሬ መንግሥት ያቋቋመውበራሱ ጄኔራሎች የሚመራው ይኽውየምዕራብ ሶማሊያ ነፃነት ንቅናቄ ግንባር(Western Somalia Libration front) በስሩየኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት አውጪ ግንባር(Ogaden National Libration Front) ኦብነግ እናከዚያም ደግሞ የሐረርጌን፣ የባሌና የሲዳሞንኦሮሞዎች ሶማሌ አቦ የሚሏቸውን እያደራጁ፣እያስታጠቁ ጦርነት ከፈቱ:: በተከታታይምኦጋዴን የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ናት እያሉበየኢንተርናሽናል  መድረክ ብዙ ፕሮፖጋንዳመንዛታቸው ይታወቃል፡፡ ዛሬ የምናየው ኦብነግ(ONLF) ይህ ነው፡፡ ክህደት በደም መሬትበሚለው መጽሐፌ ገጽ 49 ያለውንእጠቅሳለሁ፡፡

ኢብራሂም አብደላ የተባሉ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ተጠሪ በአንድ ወቅት ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል፡፡

“ድርጅታችን የሚከተሉት ዓላማዎች አሉት፡- የእስልምናን ልዕልና ማረጋገጥ፣ እስላማዊ ትምህርት በሕዝቡ ዘንድ ሰርጎ እንዲገባ ብርቱ ትግል ማድረግ፣ ኦጋዴንን ከኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ ነፃ በማውጣት ነፃ መንግሥት መመሥረትና የሕዝቡን ፍላጎትና ምኞት እውን ማድረግ፣ በእስልምናና በዲሞክራሲያዊ አመራር ሥር ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ነፃነቱ የተረጋገጠ እስላማዊ ኀብረተሰብ መገንባት፣ ከሶማሊያ ሕዝብ ጋር ያለውን የወንድማማችነትና የትግል አንድነት እንዲጠነክር፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከዓረቡ ዓለምና ከሙስሊሙ ጋር ያለንን ግንኙነት በጋራ ጥቅሞች ላይ ተመርኩዞ የሚያድግበትን መንገድ መሻት…”

የኢትዮጵያ የደህንነት ሥጋቶችና የኡጋዴንኢትዮጵያዊነት በሚሉ ርዕሶች ሰፊ ጥናትበመጽሐፌ ውስጥ እና ከዚያም በድረ ገጾች ላይአስመዝግቤአለሁ፡፡ በቅርቡም የኢህአዲግመንግሥት ኦብነግ (ONLF) ጋር ኬንያና ዱባይላይ ድርድር በጀመረበት ጊዜ ይህ የሚፈጥረውንአጠቃላይ ሁኔታ እኔ፣ / ዲማ ነገዎና /ጌታቸው በጋሻው ያለንን ስጋት የሚጠቁሙጽሁፍ በትነናል፡፡

የሱማሌ መንግሥት ብዙ ችግር ነበረበት፣Transitional Federal Government አባል የነበረውIsIamic Court የስልጣን ተቀናቃኝ በነበረበትጊዜ ONLF Islamic Court ጋር በቅርብ ይሠራእንደነበረ ታሪክ ውስጥ የተመዘገበ ነው፡፡lslamic Court በታላቋ ሶማሊያ ዓላማእንደሚያምን የታወቀ ነው:: በንግግሮቹም፣በጽሁፎቹም ላይ ይህንኑ ጠቁሟል፡፡ Islamic Court ከሥልጣን ሲባረር ወደ አልሻባብነትተለወጠ፡፡ አልሻባብን የመሰረቱት Islamic Court ኃላፊዎችና አባሎች ናቸው፡፡ አሁን ያለውየጠቅላይ ሚኒስትር ፎርማጆ መንግሥትከኢትዮጵያ ጋር መልካም ጉርብትና ስለሚፈልግኦብነግን አውግዟል፡፡ ከማውገዝም አልፎሽብርተኛ ነው ሲል ፈርጆታል፡፡

ኦብነግ (ONLF) ማን ምን እንደሆኑ ሥርመሰረታቸውን እንቅስቃሴአቸውን እናውቃለን፡፡ የኢትዮጵያ አንዱና ትልቁ የፀጥታ ሥጋትONLF ነው፡፡ የሶማሊያ መንግሥት ቢለወጥአቋማቸው እንደሚዋዥቅ ጥርጣሬ ሊኖርአይገባም፡፡ ዛሬ በዶ/ አብይ አመራር የአፍሪካቀንድ መሪዎች ሰላማዊ የሆነ አካባቢንስለፈጠሩ ONLF ዋና መስሪያ ቤቱ ያደረገባትኤርትራም ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ጉርብትናስለመረጠች፣ ሶማሊያ ውስጥም እንቅስቃሴማድረግ ስላልቻሉ ከዚህ አሰላለፍ ቢወጡInternational Community ሽብርተኛ ተብለውስለሚመዘገቡ፣ ስለሚወገዙ እና ጥቁር ሊስትውስጥ እንሚገቡ ስለሚያውቁት እንጂአጀንዳቸውን ለውጠዋል ማለት አይደለም፡፡

ሶማሊያን እንድትንኮታኮት ያደረጋት ይህፖሊስዋ ነው፡፡ ብዙ ሕይወት ከጠፋበት 1978 .. ወረራ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥትሶማሊያን ለማዳከምና ሽብር ውስጥ ለመክተትአማራጭ የሌለው ፖሊሲ ሆኖ አገኘው፡፡በሶማሌያ ውስጥ ያሉትን ተቃዋሚ ኃይሎችማስታጠቅና ማደራጀት ጀመረ:: ዛሬ የምናያትሱማሊያ የዚያው ውጤት ነች፤ አዲሱመንግሥትም፤ መልካም ጉርብትናን መርጧል፡፡ONLF እስከዛሬ የተናገረውን፣ የፃፈውን ሁሉቀልብሶ በኦጋዴን ኢትዮጵያዊነት የሚያምንበዚህ ውስጥ በህዝቦች መካከል የሚፈፀሙልዩነቶችን  በሰላማዊና በአንድነት መንፈስእንደሚፈፅም ለኢትዮጵያ ህዝብ መግለጽአለበት፡፡ 1978 .. ጦርነት ምክንያትበአስቸኳይ ዘመቻ ጥሪ ተደርጐ ምስራቅግንባር ከተሰማራ ሁለት መቶ ሠራዊትውስጥ አንድ ሶስተኛው እዚያው ኡጋዴንውስጥ አልቋል፡፡ የነበርን ሰዎች አንረሳውም::የአሁኑም ወጣቶች እና መሪዎች ሊረሱትአይገባም፡፡ ኦብነግ በጥንቃቄ መያዝ ያለበትድርጅት ነው፡፡ ስለዚህ ዛሬ ONLF ያንን በፕሮግራሙ የተቀመጠውን አቋም ሰርዞ፣  በኢትዮጵያዊነት አምኖ ለመስራት መዘጋጀቱንና ፕሮግራሙንም መለወጡን በስምምነት አፅድቆ ለህዝብ በግልፅ ማሳወቅ አለበት፡፡

አካባቢው

በካባቢያችን ያለው የኃይል አሰላለፍያስደነግጣል፡፡ የአሜሪካን የውጭ ፖሊሲበአፍሪካ ቀንድ ውስጥ በፀረ ሽብርተኝነትዘመቻ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ዛሬ ከዚህ ፖሊሲእየራቀ America First የሚለውን የአሜሪካጥቅም የሚያስጠብቅ አዲስ ፖሊሲ እየቀየሰነው፡፡ አንድ የአሜሪካ የመከላከያ ሀላፊእንደተናገሩት “Great power competition not terrorism is now primary focus of national interest” በአንድ ሀገር ውስጥ የሽብርተኛእንቅስቃሴ ኖረም አልኖረም አንድ መንግሥትራሱ ሽብርተኛ ሆኖ State Terorism ቢያካሂድም፣ቀዳሚነት የሚሰጠው የአሜሪካ የኢኮኖሚጥቅምን ነው፡፡ ይህም በቅርቡ በግልጽ በሳውዲጋዜጠኛው ጀማል ካሹጊ ላይ የተፈጸመውግድያና የአሜሪካ ዝምታ ብዙ መልዕክትያስተላልፋል፡፡ ይህንን በተመለከተ በቅርቡየፃፍኩት  “The Unholy Alliance Between the most Democratic and the most AutocraticWashington and Riad Should we be worriedየሚለውን ጽሁፍ ማንበብ ይቻላል፡፡

Global politics 09 Nov, 2018 G.C የወጣውጽሁፍ እንዲህ ይላል The new Cold War brewing in the Gulf has rapidly rewritten the geo political rule book in the Horn of Africa….Saudi Arabia and the UAE versus their bitter adversaries Qatar and Turkey are looking to forge closer connections with Ethiopia…..in the background you have Iran which is an enemy of Saudi and ally of the US. It is very complex background”

ዛሬ በጅቡቲ ላይ ያሉት የጦር ሰፈር ክምችቶችአፍሪካ ቀንድ የብዙ መንግሥታት ጥቅምመነኸሪያ መሆኑን ያመለክታል፡፡ አሜሪካ ቀድሞየፈረንሳይን ቤዝ ካምፕ አድሳ፣ አስፋፍታ ታላቅየጦር ሰፈር አድርጋዋለች፡፡ ፈረንሳዮችምእንዳሉ ናቸው፡፡

በተጨማሪም ለመጀመሪያ ጊዜ ጃፓን እና ቻይና በጂቡቱ ጦር ሰፈሮች ሰርተዋል፡፡ ህንድምበቅርቡ ትልቅ የጦር ሰፈር ጅቡቲ ላይእያቋቋመች ነው፡፡ ጣሊያንም እዚህ የሀያላንስብስብ ውስጥ ገብታለች፡፡ ዩናይትድ አረብኢሜሬትና ሳውዲ አረቢያ ትልቅ የጦር ሰፈርአቋቁመዋል፡፡ ባህረ ሰላጤውንምከመቆጣጠር ባሻገር የመን የሚያካሂዱትንውጊያ የሚያግዝ የሎጅስቲክስ ቤዝአድርገውታል፡፡ ኳታር በጅቡቲና በኤርትራመካከል በነበሩ የድንበር ግጭት ሰበብ ሰላምለማስጠበቅ ጦር ሰፈር ነበራት፡፡ በሳውዲናዩናይትድ አረብ ኢሜሬት ግፊት ከጅቡቲተባራለች፡፡

ሳውድ አሪቢያም በአሰብ ላይ ጦር ሰፈርእንዳላት የታወቀ ነው፡፡ የመን ከኤርትራ 30 ሎ ሜትር ርቀት ነው የሚለያያት:: የደቡብየመን ጦር ከኢትዪጵያ ጦር ጋር ተስልፌከኤርትራ ህዝብ እርነት ግንባር ጋር መዋጋቱንማስታወስ ይጠቅማል::

ጅቡቲ ያለችው በቀይ ባህርና በኤደን በህረሰላጤ በስዊዝ ካናል አገናኝ ሥፍራ ላይስለሆነች በባህር ላይ ለሚደረገው እንቅስቃሴታላቅ የሴኩሪቲ የኤኮኖሚ ሚና ትጫወታለች፡፡ዩናይትድ አረብ ኢሜሬት በሶማሌ ላንድ በርበራወደብ ላይ ጦር ሰፈር ከማቋቋም በላይ አዲስአይሮፕላን ማረፊያም እየስሩ ናቸው፡፡ ቱርክበሱማሊያ፣ ሩሲያም በሱዳን፣ ግብጽ በደቡብሱዳን፣ ቱርክን የሱዳን ደሴት የሆነችውንስዋኪን ላይ ጦር ሰፈር ለመመስረት መሞከሩይህንን የመሳሰሉ በየጊዜው በፈጣን ሁኔታየሚለዋወጠው ለኢትዮጵያም ለአፍሪካቀንድም በጥቅሉ አስጊ ነው::

ሁሉም ሀይሎች የየራሳቸው አጀንዳ አላቸው፤ኢትዮጵያ እዚሁ መካከል ነው ያለችው::

ለጊዜው ይህንን የአረቦች በአፍሪካ ንድ ላይየሚፈፅሙት ርብርቦሽ እንዲፈጠር ያደረገውየየመን ጦርነትና በባህረሰላጢው ባሉትብዛኛው የአረብ አግርችና በኢራ መካከልያለው ፍትጊያ ቢሆንም ከጥንት ጀምሮ አረቦችቀይ ባህርን የአረብ ሃይቅ ለማድረግ ካላቸውምኞትም ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ይህንንምበተመለከተ በቅርቡ በጣም ሰፋ ያለ ጥናትአቅርቤ አለሁ፡፡ ጊዜ ካላችሁ The Iran Saudi Rivalry and the Scramble for the Horn of Africa በሚል ርዕስ ያዘጋጀሁት ጽሁፍ The Africa Institute For Strategic and Security Studies(AISSS) ድረ ገጽ ላይ ይገኛል፡፡

ስዊዝ ካናል ከተከፈተበት 1869 .. ጀምሮአረብና አፍሪካ ቢቀራረቡም በግሎባላይዜሽንጊዜና ዓለም በሀይማኖትና በሌሎችምምክንያቶች የአረብ አንድነት እየተፍረከረከታላቅ የነበረው የአረብ (Nationalism) ብሔርተኛነት ሲፈርስ አሁን አዲስ ሃይሎችዩናይት አረብ ኢሜሬትና ሳውዲ የሚመሩትብቅ ብሎ Gulf Alliance በሚል አሜሪካየተወውን ባዶ ሥፍራ ለመሙላት አካባቢውንበገንዘብ ሃይል ለመቆጣጠር እየቻሉ ነው፡፡አሁን ቀይ ባህር የአውሮፓና የአሜሪካ ጉዳይሳይሆን የአፍሪካና የአረብ ሀገሮች ጉዳይ እየሆነመጥቷል፡፡ አካባቢው በጣም ተከፋፍሏል፡፡በዩናይትድ አረብ ኢሜሬትና በሳውዲ አረብያየሚመራው አሊያንስ፣ በአፍሪካ ቀንድ ውስጥያሉ ሀገሮችን ለመያዝ ለመቆጣጠርየሚፈፀመውን ሁለንተናዊ ዘመቻ ኢትዮጵያበጥንቃቄ ልትመለከተው ይገባል፡፡ በቅርቡ 30 Nov, 2018 The National Interest በሚባልonline ፅሁፍ አንድ የፖ ዲህይላል፡፡

“Somalia remains troubled largely by foreign agents who weaken its government, who divide its people and who threaten to reverse its gains”ይህም የተባለበት ምክንያት የአረብ ኤሜሬትስበሕ የሶማሊያ አካል በሆነችው ፑንትላንድናሶማሌ ላንድ ላይ እንቅስቃሴ በመጀመራቸውነው:: ንያም በበኩሏ በአካባቢው ያለውእንቅስቃሴ የሚያሳስብ መሆኑን አሰምታለች::

የመን ውስጥ የሚደረገው ጦርነት የየመንህዝብ ጦርነት አይደለም፡፡ ኢራን በአንድ ወገን፣ሳውዲ አረቢያ በሌላ በኩል በአሜሪካ ድጋፍየሚካሄድ የእጅ አዙር ጦርነት ነው፡፡ የመንውስጥ ሃያ ሚሊዮን ህዝብ በረሃብ ላይ ይገኛል፡፡አስራ አንድ ሚሊዮን ህፃናት በሞት እናበሕይወት አፋፍ ላይ ናቸው፡፡ የመን የምትባልሀገር ጠፍታለች፡፡ ስንት ሞቷል ስንት ቆስሏል፤ የእጅ አዙር ጦርነቶች እየተበራከቱሲሄ ኢትዮጵያ ከእያንዳንዱ ልትማር ይገባል፡፡ከሱዳን እና ከግብጽ ጋር ኢትዮጵያ ያላትየተፈጥሮ ቁርኝት ማለትም ኢትዮጵያ ለሁለቱሀገሮች የህልውና ጥያቄ ስለሆነች የኢትዮጵያንሁኔታ በቅርብ ይከታተላሉ፡፡ በሚታይምበማይታይም መንገድ ዘወትር በኢትዮጵያ ጉዳይጣልቃ ከመግባት አይቆጠቡም፡፡

ኤርትራና ኢትዮጵያ የውጭ ፖሊሲያቸውእንዳይጋጭ ከባድ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፡፡ኤርትራ በየመን ጦርነት ላይ አቋም ይዛለች፡፡በሌሎችም በአካባቢው ካሉ የአረብና የአፍሪካቀንድ ሀገሮች ጋር አቋም አላት፡፡ ኢትዮጵያምእንደዚሁ አቋም አላት፡፡ ይህ አቋማቸው ሁልጊዜ ተመሳሳይ ሊሆን አይችልም፡፡ እይገባምም:: ልዩነቶችን ማጥበብና ማጥፋትበማይቻልባቸው ሆኔታዎች አንዱ የአንዱንአቋም አክብሮ የመኖር ባሕል ሊገነቡ ይገባል፡፡

ከኤርትራ ብዙ ስደተኞች ነን የሚሉ ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ናቸው:: ከዚሁ ጋር ተያይዞብዙ የኤርትራ መንግሥ ተቃዋሚዎችኢትዮጵያ ምድር ገብተው በኤርትራ መንግሥትላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለማሰማት ቢሞክሩምንድነው የሚደረገው? ከኢትዮጵያ አኩርፈውወንጀል ፈጽመው ኤርትራ ለሚገቡ ምን አይነትአቋም ነው ኤርትራ የምትወስደው? በንግድም፣በሌሉችም ሁለቱን ህብረተሰቦች በሚያገናኙጉዳዮች ሁሉ አለመግባባት እንዳይፈጠርውይይት ተደርጎ ወረቀት ላይ የሰፈረ ስምምነትማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ በሁለቱም በኩል ሊኖርየሚገባው ግዴታና ኃላፊነት በዝርዝር መጠቀስ ይገባዋል::

በአጠቃላይ የውጭ ፖሊሲን በተመለከተ በዚህሙያ ልምድ ያላቸው የፃፉ፣ የተመራመሩአዋቂዎች ያሉበት እንደ አስፈላጊነቱየሚሰበስብ ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩቢያቋቁሙ ይረዳቸዋል ብዬ አምናለሁ፡፡

መደመደሚያ::

በመጨረሻም የሀገር ውድቀት የሚመጣውበአንድ ጊዜ አይደለም ቀስ በቀስ ነው፡፡በየጊዜው የሚከሰቱ ጉዳዮች ውጤት ነው፡፡ዛሬ ኢትዮጵያ ከባድ ሥጋት ላይ ነች ዛሬ ክልሎች ከኢትዮጵያ መንግሥት ቁጥጥር ውጭ እየሆኑ ከፌዴራሊዝም ያለፈ ስም የለሽ ሥርዓት ውስጥ ተሸጋግረዋል፡፡ አብረው የኖሩ በአንድነት ታሪክ የሰሩ፣ በእምነታቸው በባህላቸው ተሳስረው የኖሩ ተጋብተው ተዋልደው የኖሩ ቢጣሉም ልዩነታቸውን ሳያስቀድሙ ሀገርን ጠብቀው ሞቱን በአንድነት ሞተው ስቃዩን ችግሩን ተደጋግፈው አሳልፈው ኢትዮጵያን አንዳልገነቡ ሁሉ ዛሬ በመጣው የዘር ፖለቲካ ምክንያት ጋብቻ በዘርቆጠራ፣ ትምህርትቤት ጓደኝነት በዘር ቆጠራ፣ እየሆነ በመምጣቱ የሚያስተሳስሩን እሴቶች እየጠፋ ለመራራቅ አመቺ ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ የተደራጁ ተዋጊ ኃይሎች በግልፅ አይታዩም፡፡ አሁን ጸጥታውን የሚያደፈርሱት ትንንሽ ቡድኖችና የማይታዩ ሃይሎች ናቸው፡፡ የተደራጀ ኃይልን መቋቋም አያስቸግርም ግን የተበታተኑ ቡድኖች ግን አመጽና ወንጀል ለመቋቋም አስቸጋሪ ነው፡፡  ከሥር ጀምሮ ያሉየመንግሥት ተቋሞች እየፈረሱ ከማዕከላዊመንግሥት ቀርቶ ከክልላዊ አመራሮችምቁጥጥር ውጪ ሲሆኑ፣ የታጠቁ ግለሰቦችተከታይ እየመለመሉ አካባቢያቸውንመቆጣጠር ሲጀምሩ ሥልጣን እየጣማቸውየመንግሥት ሃይልን መቋቋም ሲጀምሩ ሊገቱየማይችሉ የሰፈር ጦር መሪዎች (War Lords) ይፈጠራሉ፡፡ ይህንን ክፍተት ያዩ ሌላ አጀንዳያላቸው፣ መሳሪያና ድጋፍ በገፍ ያቀርባሉ፡፡ክፍተቱ እና ጣልቃ ገብነቱ  እየሰፋ ሲሄድየራሳችው ውጊያ መሆኑ ቀርቶ የሌሎች ውስጣዊ ኃይሎችና የባዕዳን ጉዳይ ፈፃሚዎችይሆናሉ:: ጦርነቱ ኃይል መጠቀም ሲጀመርሰላማዊ ህዝብና አማፂያንን መለየትያስቸግራል፡፡ ቁጣውና ኩርፊያው ይበራከታል፤ጠላትም ይጠቀምበታል፤ የዚህንም ሂደት መተንበይ ያስቸግራል፡፡

እዚያ ሳንደርስ ሳይቃጠል በቅጠል የምንለውለዚህ ነው፡፡ መስረታዊ የስርአት ለውጥ ጊዜየሚስጠው ይደለም:: የዘመናት ትርምስ ዛሬወሳኝ ደረጃ ላይ ደርሶአል:: ህዝብ በቀጥታየተሳተፈበት ህገመንግስትን ማውጣት፣ በዘርላይ የተመሰረተ ፌዴራሊዝምን ማጥፋት፣ማዕከላዊ ግሥትን ማጠናከር፣በአካባቢያችንና ከዚያም ባሻገር ካሉ አገሮችጋር የተጠና ሚዛናዊ ወዳጅነት መፍጠር፣ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ተፈርተው፣ተከብረው የመልካም አስተዳደርና የአብሮነትኑሮ ምሳሌ ሆነው የጥቁር ህዝብ ተስፋና ኩራትእንደነበሩ ሁሉ ዛሬም እንደሚሆኑ ሊያረጋግጡ ይችላሉ፡፡

በዶ/ር አብይና በመንግሥታቸው የሚፈጸመውንና የታቀደውን ባለማወቅ ተሳስቼ ከሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ዓላማችን ለማገዝ፤ የተለየ ሐሳብን ለማቅረብና ለማንሸራሸር እንዲረዳ በዕድሜና በተሞክሮ ከበለፀግን፤ ስልጣንና መታየትን ከማንፈልግ ወገኖች በቅንነት የቀረቡ  ጥናቶችና ሐሳቦች ናቸው፡፡

አመሰግናለሁ፡፡