img-dbe60706f1d683b9ef804154c7fb7b48-v2141756150_6dd6f90ca7_b

ልቀቅ አዲስ አበባን ተው ያራዳን ልጅ

ልመናም አይደለም አይበጅህም እንጂ ።

አራዳው ሲጫወት ካልተመቸህ ላንተ

ላሽ ብለህ እለፈው አይገባህም አንተ ።

ቁም ነገሩ ጣፋጭ ልቡ ግልፅ የሆነ

አንተ ሳትነቃ እሱ የባነነ ።

መጀን የአዲስ ልጅ ቂምን የማያውቀው

በጅሎች ጨዋታ አንተ ብታበሽቀው ።

እሱ አይጣላህም ትሁት ነው አራዳ

ለገባልህ ቃሉ እማያወላዳ ።

ብቻ ግን ብትሞክር ልትሸውድ አሱንimg-dbe60706f1d683b9ef804154c7fb7b48-v

ልታቆስል ብትሞክር ያመነህን ልቡን ።

አያድርገኝ አንተን ከርፋፋው ባተሌ

ያለብስሃል እሱ ቁምጣህ ላይ ቦላሌ ።

በፍቅር አማኝ ነው አይጨክን አንጀቱ

ያንተ ክላሽ ብርት አረ የት አባቱ።

ከፍቶህም ብትመጣ ወይም ወፈፍ አርጎህ

ይሸኛል አራዳው እራቁትክን አርጎህ ።

ስቶክሆልም ጃንዋሪ 2019