ተከሳሽ አዲሱ ከባ በዳሶ የ29 ዓመት ወጣትና የአይቲ ባለሙያ ነው፡፡ ግለሰቡ ሙያውን በመጠቀም በሀገርና በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል በማለት ፖሊስ በግለሰቡ ላይ ክስ መስርቷል፡፡

ተከሳሽ ለቴሌኮም አገልግሎት ብቻ የተፈቀዱ መሳሪያዎችን ከኢትዮ-ቴሌኮም እውቅና ውጪ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት መቀመጫውን አሜርካ ካደረገው ዮ.ፒ.ኤም የቴክኖሎጂ ተቋም ሰራተኛ ከሆነው እና ለግዜው በቁጥጥር ስር ሊውል ካልቻለው ግብረ አበሩ ሚኪ ዳን ጋር በመቀናጀት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ አራት ክፍለ ከተሞች ሰባት የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችን በተለያየ ግለሰብ ስሞች በመከራት የአለም አቀፍ ጥሪዎችን መጥለፍ ሚችሉ የቴሌኮም መሳሪያዎችን በማስቀመጥ የኢትዮ-ቴሌኮም ከአለም አቀፍ ጥሪዎች ማግኘት የሚገባውን ገቢ በማሳጣት በተቋሙ ላይ 47,530,244 ብር ኪሳራ እንዲደርስበት አድርጓል ያለው መርማሪ ፖሊስ ነው፡፡

ግለሰቡ በተከራያቸው ቤቶች ውስጥ ባስቀመጣቸው ህገ-ወጥ የቴሌኮም መሳሪያዎች አማካይነት 11,268,435 ደቂቃ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች ጥሪዎችን አስተናግዷል፡፡

ተከሳሽ በኢትዬ ቴሌኮም ላይ በፈፀመው ከፍተኛ የማጭበርበር ድርጊት እና በህገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ በመጠቀሙ በሁለት ወንጀሎች የተከሰሰ ሲሆን ግለሰቡ በፈፀመው ከባድ የማጭበርበር ወንጀል ተጠይቆ፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ታህሳስ 3 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ግለሰቡ በፈፀመው ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑን በሰው፣ በሰነድና በኤግዝቢት በተያዙ ማስረጃዎች በማረጋገጡ ጥፋቱን ይመጥናል ሌሎችም ከዚህ
ይማራሉ ብሎ በማሰብ ተከሳሹን በ13 ዓመት ፅኑ እስራትና በ500 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ተወስኖበታል ፡፡

ethiotelecom