ሚኒማ ያሟሉ የህወሓት/ ኦህዴድ/ ብአዴን/ደኢህዴን ኢህአዴግ ሌቦች ዙሩን አከረሩት! በሚሊዮን ዘአማኑኤል )

0

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

 በኢትዮጵያ የፋይናንሻል ባንኮች ዘርፍ የሙስናና የሌብነት ሃጢዓት ቅጣት፣ ከውኃ አጥማቂው በኋላ፣የእሳት አጥማቂው ይመጣል!!!

 የ50 እና የ100 ብር ኖቶች በአፋጣኝ መቀየር የገንዘብ ዝውውሩን ኡደት ያጠፋዋል፡፡

 • ኢትዮጵያ በዓለም የሕግ የበላይነት መለኪያ ከ126 አገሮች 118ኛ ደረጃን በመያዝ የመጨረሻውን ሚኒማ ማላት ተሳናት፡፡ ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉ 30 አገሮች 27ኛ ደረጃን ስትቆናጠጥ፣ ከ20 አነስተኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ደግሞ 18ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡ በጥናቱ መሠረት ከፍተኛ ባለፉት ሁለት ዓመታት በዓለም አገሮች የሕግ የበላይነት አለመሻሻልና የመቀነስ አዝማሚያ የሕግ የበላይነት በኢትዮጵያ እንደሌለ በዴሞክራሲ ስም ሙሰኞችና ሌቦች በ5 ሚሊዮን ብር ሰዓት በመግዛት የኦዴፓ ሚኒሚ ማላታቸው ከበሰበሰው ህወሓት ኢህአዴግ ወደ ኦዴፓ ኢህአዴግ ዘመ
 • ‹‹በእርሻ ዘዴ ግብርና፣
 • ነበር የሚገኝ ብልጽግና፣
 • ከኔ ዘንድ የለም ተስፋ፣
 • ዘሩም እንደበቀለ ጠፋ ›› ህዝቡ እያለ ሃገሪቱ በስምንቱ የጥናት ዘርፎች በመንግሥት ሥልጣን ላይ ባለ ገደብ ከ126 አገሮች116ኛ፣ በሙስና አለመኖር 64ኛ፣ በመንግስት ግልፅነት 123ኛ፣ በመሠረታዊ መብቶች 124ኛ፣ በሕግ፣ሥርዓትና ደኅንነት 93ኛ፣ በሕግ ማስፈጻም 120ኛ፣ በፍትሀብሔር ፍትህ11ኛ፣ እንዲሁም በወንጀለኛ ፍትሕ 104ኛ ደረጃን መያዞ በጥናቱ ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ የፍርድ ቤት ውሎ ትያትር‹‹ በየ14ቀን ሜቴክ ዘረፋ ….ከማለት ውጪ መቐለ የመሸገው ማክሲማውን ያሞሉ ሌቦችን ዝንባቸውን እሽ ሲል አልተስተዋለም፡፡  በአገራችን በህግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል አይደለም፡፡ ከወርቁ የዘገነና ያልዘገነ እኩል የሚያዝንበት ሥርዓት ሁሉን እርሳው ጤና ካለህ ሰርተህ ታገኛለህ ይልሃል፡፡   ለገጣፎና ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር አ12000 እንዲፈርሱ መወሰኑና  ከሽህ በላይ ቤቶች ማፍረሳቸው በዜናው ናኝቷል፡፡ በሌላ በኩል የፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል እንደሻው ጣሰው የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው ያልተያዙ ግለሰቦች ወንጀለኞቹን የሚደብቁ፣የሚሸሽጉና አካባቢዬ ላይ ተጠርጣሪው የለም ብሎ የሚያብር ክልል እንዳለና በዚህ ወቅት ለሰላም ስትል አትታኮስም፣ የተጀመረው ለውጥ የሚያናጋና የሚያበላሽ እንዲሁም የወንጀል መከላከል ሥራ ላይም ጥላ የሚያጠላ ጉዳይ ስለሆነ  በሚታረምበት መንገድ ይታረማል ብለዋል፡፡ ድሮም ‹‹የአህያ ባል ጅብ አያስጥልም!!!››   እስካሁን የህዝብ ልጆች በአደባባይ ገድሎ ለፍርድ የቀረበ አንድ ተጠያቂ አላየንም!!! በቅርቡ መቐለ የመሸጉት ሙስኛ ሌባ ሹማምንት በ 5 ሚሊዮን ብር ድጎማ አዲስ አበባ እንደሚደመሩ ጥርጥር የለንም፡፡
 • በቅርቡ በአፍሪካ ህብረት ሪፖርት ከኢትዮጵያ ባለፈው ዘጠኝ አመታት ውስጥ 20 ቢሊዮን ዶላር መኮብለሉን ተጋልጦል፡፡ ሚኒማ ያሞሉ ሌቦች ዙሩን አከረሩት! አንድ ሰው 5 ሚሊዩን ብር (180 ሽህ ዶላር) መዋጮ የተጠየቀበት 5 ቢሊዩን ብር አሰባስቦ የአዲስ አበባ ዳር ዳርቻ ፕሮጀክት 56 ሄክታር የሚሸፍን ልማት 29 ቢሊዮን ብር ለማላት ሚኒማ ያሞሉ ሙሰኛ ሌቦች ዙሩን እያከረሩት ይገኛሉ፡፡ ፍንፍኔ የማን ናት! ታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ የጣና ሃይቅ እምቦጭ፣ የስኳር፣ የመስኖ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ሳያልቁ ሌላ እንደማይጀመር ቃል በተገባ በሳምንቱ ሚኒማ ለሚያሞሉ ሌቦች ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡
 • ባለፉት ስድስት ወራቶች ውስጥ 89 ሚሊዮን 538 ሺህ 962 ብር የተለያዩ ሀገራት ገንዘብ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር መያዙን የፌዴራል የገቢዎች ሚኒቴር ለአማራ ብዙሃን ድርጅት ገልጿል፡፡ሶማሌ፣አፋርእና ሎሎች የሃገሪቱ ጠረፋማ አካባቢዎች ህገወጥ ገንዘብ በማዘዋወር የተበላሹ መድሃኒቶች፣የጦር መሣሪያ፣ ምግቦች ሃሽሽ አየር መንገድ ሠራተኞች ወደ ሀገር ውስጥ ሲያስገቡ ተይዘዋል፡፡በሶማሌ ክልል 60 ሚሊዮን ብር 13 የውጭ ሀገራት ገንዞቦች፣እና 7 ኪሎ ግራም ወርቅ ተይዘዋል፡፡ የ50 እና የ100 ብር ኖቶች በአፋጣኝ መቀየር የገንዘብ ዝውውሩን ኡደት ያጠፋዋል፡፡
 • በኦሮሚያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ 20 ሚሊዩን ብር ገቢ አሰባሰበ፣ በዛ ዝግጅት ላይ የኢሊሌ ሆቴል ባለቤት ገምሹ በአምስት ሚሊዮን ብር የዶክተር አብይ ሰዓትን በጨረታ አሸንፈዋል፡፡ ገምሹ በሙስና ሊያዝ ሲል ወደ አሜሪካ ኮብልሎ የነበረ ኢንቨስተር ሲሆን በተደረገላቸው ጥሪ የሙስና ሚኒማ በማሞላታቸው ወደ ሃገር የገቡ ገምሹ መሆናቸውን ልብ ይበሉ፡፡
 • የካቲት 13 ቀን 2011ዓ/ም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ልማት ባንክ ለግብርና ያበደረው 6.3 ቢሊዮን ብር በላይ እንደማይመለስ፣ ይህም የሆነው በተደራጀና በተቀነባበረ ኔትወርክ ስውር መንገድ ብድሩ በመሰጠቱ ነው ብለዋል፡፡ ይናገር ደሴ በፖሊስ ሥራ በጸረ-ሙስና ስራ ምን ጥልቅ አረገው!!! ቀን ያወጣዋል በሙያው የሰለጠኑ ስንት የሀገር ልጆች የሚያሰራቸው አጥተው እንጅ ተራ የሌባ ሥራን ማካበዱ ምን አመጣው፡፡ ‹አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ› በእናንተ የሥልጣን ዘመን ነው ገንዘቡ የተበላው  አቶ ተክለወልድ አጥናፉ፤  አቶ ዮሐንስ አያሌው፤ አቶ ሶፍያን አህመድ፣ የኢህአዴግ ካድሬዎች ባንኩን እንዳረከሱት ረስተውታል፡፡ ላሜራ ብረት እንደ ወርቅ ባር የተቀበለ ባንክ፣ የለገደንቢና ኢዛና ወርቅ ከብሄራዊ ባንክ ውጪ እንዲሄድ ያደረገ ሙያተኛ፣ ከአስመጪና ላኪዎች ጋር በመመሳጠር  ሃገር ያዘረፈ ባንክ ገዥዎች ተሾሙ  እንጂ ተጠያቂ ሲሆኑ አልታየም፡፡ ይሄን የፋይናንሻል ባንክ ዘርፍ ይዞ ልማት መጠበቅ ሚኒማውን ያላሟላ ለውጥ መጨረሻው  ለውድቀት ነው እንላለን፡፡  የሁለተኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ወይም ማስፈጸሚያ በአምስት አመት ፕሮግራም ውስጥ 2.4 ትሪሊዩን ብር ይጠይቃል፡፡ 2.4 ትሪሊዩን ብር ወጪ ለመሸፈን በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ላይ የሚኖረው የአገር ውስጥ የገቢ አቅም 2.03 ትሪሊዩን ብር ነው፡፡ በመሆኑም የበጀት ጉድለቱ ዕርዳታን ጨምሮ 341.2 ቢሊዩን ብር ይሆናል የሚል ታሳቢ በረቂቅ እቅዱ ተይዞል፡፡ ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚፈለገው የውጭ ምንዛሪ 119.5 ቢሊዩን ዶላር ይሆናል ብሎ የሚገምት የብሄራዊ ባንክ ሙያተኛች የኢህአዴግ ካድሬዎች የሃገሪቱን ኢኮኖሚ መቀመቅ ከተውታል፡፡  የገቢዎች ሚኒስትሮ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ‹‹በፖለቲካ አለመረጋጋት ሳቢያ ግብር የማይከፍሉ በርካታ ግብር ከፋዮች መኖራቸውን ገልጠዋል፡፡ በህቡዕ የሚደረግ የጨለማ ኢኮኖሚ  እንቅስቃሴ መንሰራፋቱን፣ በአገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን፣ የግብር ገቢ መሰወርና የንግድ ፍትሐዊነትን ማዛባቱ፣ ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ገልፀዋል፡፡››
 • በመንግሥት ላይ 71.6 ሚሊዮን ብር ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ የሜቴክ ስድስት ሠርተኞችና አንድ ነጋዴ ተከሠሡ፡፡ የሜቴክ ክንፈ ዳኘውና ኢሳያስ ዳኘው ኢዲኤም ከተባለ የአሜሪካአማራሬ ድርጅት ጋር በሙስና ተጠረጠሩ ወዘተርፈ… ለ14 ቀን …ወዘተ ህግ መቀለጃ የሆነባት ሃገር በዴሞክራሲ ስም የህግ ሉዓላዊነት የተጣሰባት ሀገር በመሆኗ 118 ደረጃ ሲበዛባት ነው እንላለን፡፡
 • 240 አስመጪና ላኪዎች ኩባንያዎች ውጭ ምንዛሪ በማሸሽ ከተጠረጠሩት መኃል ሰሊጥ ላኪው ዋርካ ትሬዲንግ ኩባንያ፣ ቡና ላኪው አብዱል ሰመድ ኩባንያ ወደ ውጭ ምርቶቻቸውን በላኩ ቁጥር በትንሹ አንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ከሃገር ያሸሹ ነበር፡፡ ብረትና የተለያዩ ምርቶችን በተለያየ ጊዜ ከውጭ ለማምጣት ምንዛሪ ተፈቅዶላቸው ነገር ግን ምርቶቹን ሳያመጡና እንደገና የውጭ ምንዛሪ ተጠቃሚ የሆኑ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ፣ መሰቦ ቢውልዲንግ ማቴሪያል፣አሰገዶም አብርሃና ኤዜድ ፒኤልሲ እንዲሁም ጎላጎል ትሬዲንግ ኩባንያዎች እንዲሁም ሑለት የጨርቃ ጨርቅ ኩባንያዎች፣ አይካ አዲስና ኢቱር ጥሬ እቃ ሰሲያስመጡና ምርት ሲልኩም የውጭ ምንዛሪ በማሸሽ 240 ድርጅቶች በብዙ ቢሊዮን ዶላር ያሸሹ ብሄራዊ ባንክ የሌብነቱን መረጃ ይፋ ሲያደርግ የባንኩ ተባባሪ ሌቦች ሹመትና እድገት አግኝተውበታል፡፡  ባለሃበቶቹ ከባንኩ ሙያተኞች ጋር በመመሳጠር ሃገሪቱን እንዳዘረፉ የአደባባይ ሚስጢር ሲሆን በህግ ማንም አልተጠየቀ፡፡ ከውኃ አጥማቂው በኋላ፣ የእሳት አጥማቂው ይመጣል!!!
 • ግብር በመሰወር መንግሥትን 14 ቢሊዮን ብር ያሳጡ 134 የንግድ ድርጅቶች የ65 ቱን ስም ዝርዝር የገቢዎች ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡ ከአምራቶች መኃል ኢስት አፍሪካንትሬዲንግ ሐውስ፣ ጀሳምቢን ትሬዲንግ፣ዋኔት ትሬዲንግ፣ኢትዮ ኢንተርናሽናልፋት ዌር ክላስተር እንዲሁም ምስራቅ ሃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር፣ የደንበል፣ የጎተራና አጎና ቅርንጫፍች ይገኙበታል፡፡የጅምላ አከፋፋዬች ውስጥ ይዛድ ጠቅላላ ንግድ አስመጪና ላኪ ድርጅት፣ ሶልቲና ጠቅላላ ንግድ፣ አርጂኬ የህንጻናየኤሌትሪክ እቃዎች ትሬዲንግ፣ ሮተርዳም ጀነራል ትሬዲንግና ፈሙ ኤሌክትሪካል ወርክስ ግብር ሰውረዋል ከተባሉት ጅምላ አከፋፋዬች መኃል ይገኙበታል፡፡ በዚህ ወንጀል እርምጃ የተወሰደባቸው ሆቴሎች መሃል ደግሞ ላሊ ሆቴል፣ሻፍረሪን ሆቴል፣ አሰብ ሆቴልና ሸንዲሆቴል ጥቂቶቹ ናቸው፡፡   ለገጣፎ የግብር ከፋይ የደሃ ቤቶች ይፈርሳል!!! ከውኃ አጥማቂው በኋላ፣ የእሳት አጥማቂው ይመጣል!!!
 • የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የፓልም ዘይት ወደ አገር ውስጥ እንዲያስገቡ ከተፈቀደላቸው ኩባንያዎች በግዜው ሚኒማውን ያሞሉት አምስት ኩባንያዎች በላይነህ ክንዴ አስመጭና ላኪ፣ሆራይዘን ኢትጵያ፣ ኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ፣ አልሳም ትሬዲንግና ኤኤችኤፍኤ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም የኤህአዴግ የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች የበአዴን/ አዴፓ አምባሰል ኢንተርፕራይዝ፣ የህወሓት ጉና ትሬዲንግ፣ የደኢህዴን ወንዶ ኢንተርፕራይዝ፣ የኦህዴድ ቢፍቱ ትሬዲንግ እንዲሁም አለ በጅምላ  የተባሉ ‹‹የኢንዶመንት ኩባንያዎች›› ፓልም የምግብ ዘይትን እንዲያስመጡና እንዲዘርፉ በሕግ ተፈቅዶላቸው ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡ አገሪቱ በየአመቱ ከ700 ሽህ ቶን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት የምታስገባ ሲሆን ባለፈው በጀት ዓመት ብቻ 734 ሽህ ቶን ዘይት ወደ አገር ውስጥ ገብቶል፡፡ ዘይቱ በህዝቡ ጤንነት ላይ ጉዳት በማድረስ ለውፍረት በመዳረግ ለበሽታ እንደሚዳርግ በጤና ባለሞሎች ይታወቃል፡፡
 • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስብአዊ ጉዳዬች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የካቲት 26 ቀን 2011 ዓ/ም 8.3 ሚሊዮን በላይ ወገች በአማራና በደቡብ ለሚገኙ ተፈናቃዮች አስቸኮይ ዕርዳታ እንደሚስፈልጋቸው ተመድ አስታውቆል፡፡ ተመድ እንዳስታወቀው በአማራ ክልል 90 ሽህ ፣ በደቡብ ክልል በጌዲኦ ዞንና ቢንች ማጂ ዞኖች፣ በኦሮሚ ክልል በቡኖ በደሌ፣በቄለም ወለጋ፣ በነቀምትና በጅማ፣ በቤኒሻንጉል ክልል ጉሙዝ ከማሺ፣ በአፋር፣ በሶማሌ ክልሎች ባለፉት ሁለት አመታት ጀምሮ በተከሰተው ግጭት በመቶ ሺዎች ሚቆጠሩ ተፈናቃች አስቸይ ዕርዳታ እንደሚስፈልጋቸው ተመድ አስታውቆል፡፡
 • “በርሻ ዘዴ በግብርና፣ነበር የሚገኝ ብልጽግና፣ከእኛ ዘንድ የለም ተስፋ፣ዘሩም እንደበቀለ ጠፋ

የህግ ሉዓላዊነት ይከበር፣ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!!!

ኦዴፓ/ኢህአዴግ መንግሥት ለሌቦችና ሙሰኞች ከለላ አይስጥ!

ህገወጥ ቤቶችን ከማፍረሳችሁ በፊት የሙሰኛ ሌቦችና ነፍሰገዳዬችን ቤትና ምሽግ አፍርሱ!!!

ሌባ በነገሠባት አገር፣ ህገወጥ ብሎ ቤት ማፍረስ ያስቀስፋል!!!

ከውኃ አጥማቂው በኋላ፣የእሳት አጥማቂው ይመጣልና!!!