አዲስ አበባ ከተማ የግብር ከፋዮ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ኃብት ናት ( በሚሊዮን ዘአማኑኤል )

0

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOM

 ”በርሻ ዘዴ በግብርና፣

ነበር የሚገኝ ብልጽግና፣

ከእኛ ዘንድ የለም ተስፋ፣

ዘሩም እንደበቀለ ጠፋ “

የለገሃር የቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት፣ የቻይናውያኑ ስካይላይት ሆቴልና የአዲስ የወንዝ ዳር ዳርቻ ፕሮጀክት፣ አዲስ አበባ የማናት? ፍንፍኔ የማን ናት?

የመለስ ዜናዊ የፖለቲካ ሴራ ውርስ ቀጠለ። የህወሃግ/ኢህአዲግ መንግስት ከደርግ ወታደራዊ መንግስት የግል ባለሃብቶችን ንብረቶች የከተማና የገጠር መሬቶች ወርሶ ባገኘው የአባት ውርስ መሠረት እንደቀጠለበት ልብ ሊሉ ይገባል፡፡ በኢትዬጵያ የ1975 እኤአ በሶሻሊዝም ስም የተወረሱ የግል ባለሃብቶች ፋብሪኮች፣ ኢንደስትሪዎች፣ ትልልቅ እርሻዎች ንብረቶች ወደ መንግስታዊ ካፒታሊዝም ንብረትነት ተሸጋግረው የታየበት ስርዓት ነበር፡፡ የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት ኢፈርት፣ጥረት፣ዲንሾ፣ ወንዶና ሜድሮክ ካንፓኒዎች በመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ባለፈው 20 አመታት 365 መንግስታዊ ድርጅቶች ወደ ግል ዘርፍ ሲዘዋወሩ አብዛኛዎቹን ተቀራመቷቸው፡፡ የህወሓት/ኢህአዲግ የጦር አበጋዞች መንግሥት ወደ ኦዴፓ/ኢህአዴግ የጦር አበጋዞች መንግሥትነት የመቀየር አዝማሚያዎች ይታያሉ፡፡ አዲስ አበባ ከተማ የኦሮሚያ ክልል ናት፣ የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም በአዲስ አበባ፣ የሚለው የመለስ ማማለያ የኦሮሚያ ፖለቲከኞችን ልብ ያሸፈተ አዲስ አበባ ወተት የሚፈልቅባት፣ ማር የሚቆረጥባት የተስፋይቱ ምድር ለማድረግ የኦሮሞን ህዝብ ወደ ተስፋይቱ መሬት ቡልቡላን፣ ቀበና፣ ግንፍሌ፣ አቃቂ ወንዞችን አሻግረው ከወንድም እህቶቹ ደም ሊያቃቡት ይሻሉ፡፡

አዲስ አበባ ከተማ በውስጧ በሚኖሩት ህብረ ብሔር ኢትዮጵያውያን ግብር ከፋይ ህዝብ ኃብት ናት፡፡ አዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ ህብረት ሃገራት መቀመጫ መዲና ናት፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ልዩ ፅህፈት ቤቶች የሚገኙባት፣ እንዲሁም ብዙ ኢንባሲዎችና ለጋሲዎኖች የሚኖሩባት ዓለም አቀፍ ከተማ ናት፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ በመረጠው መሪ መተዳደር ዴሞክራሲያዊ መብቱ ነው፡፡ በዚህ  ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ተካፍሎ መወዳደር የሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች መብት ሲሆን በከተማው ህዝብ ነፃነት ላይ የሚደረግ የገዥና ሽያጭ፣ የእኛና የእናንተ የመለስ ዜናዊ ተረት ተረት ለአንዴና ለሁሌ እልባት አግኝቶ መቆጨት ይበጃል እንላለን፡፡  ህወሓት የፖለቲካ ጫና በደረሰበት ዘመን ሁሉ የአዲስ አበባን ከተማ ለኦህዴድ ለማስተላለፍ ሲዝት፣ ሲጠግብ ኦህዴድን አዳማ ሲያባርር በ27 ዓመታት ዘመኑ ተስተውሏል፡፡ ዛሬም ህወሓት/ኢህአዴግ መንበረ-ሥልጣኑን ለኦህዴድ/ኢህአዴግ አስተላልፎ በሪሞት ኮንትሮል አዲስ አበባ የማናት፤ ፍንፍኔ የማን ናት፤ ማብሪያና ማጥፍያውን በመነካካት ፖለቲካውን ይዘውረዋል፡፡ የምጣኔ ኃብት ተመራማሪ አጥኝዎች በዓለማችን እንደሚገኙ ከተሞች ሁሉ፣ አዲስ አበባ ከተማ በአንደኛ ደረጃ የባለጸጋ ኢትዮጵያዉያኖች ንብረት ናት፡፡ ቀጥሎ የዓለም አቀፍ ሃብታም ከበርቴዎች ንብረት ናት፡፡ ይሄን ሃብትና ንብረት በዝርዝር በጥናት አንድ በአንድ እየነቀስን በከተማዋ ውስጥ ያለውን የመሬት ሃብት፣ የህንፃዎች የንብረት ባለቤትነት፣ የገንዘብ ኃብት በጥናት በተከታታይ እናቀርባለን፡፡ በተለይ በማይንቀሳቀሰው ሃብትና ንብረት ላይ በማተኮር ሌላው ኢትዮጵያዊ ምን ንብረትና ሃብት እንዳለው እንዲሁም ብዙሃኑ ደሃ ህዝብ ከአዲስ አበባ ከተማ ሲሞት ሁለት ክንድ መሬት መካነ መቃብር ቦታ ያገኝ ይሆናል፡፡ በዚች ከተማ የመካነ መቃብር ቦታ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠፋ ጥርጥር የለንም፡፡ ዛሬ የመቀበሪያ ፉካ ከ30 እስከ 50 ሽህ ብር ይገዛል፡፡ ሙታኖች ፎቅ ተገንብቶላቸው ከጥቁሮ አፈር ከተለያዩ በህወሓት/ ኢህአዴግ ዘመን 27 ዓመታት ተቆጥሯል፡፡ ሁሉ ነገር ንግድ ሆኖል፡፡ በምጣኔ ሓብት ትምህርት የመቃብር ፉካ ይሄን ያህል ካወጣ በህይወት ያለው ደሃው ሰው በህይወቱ ይሄን ብር አግኝቶት አያውቅም፡፡ እውነት አዲስ አበባ የማናት? ፍንፍኔ የማን ናት? ዋሽንግተን ዲሲ የማናት? የዓለም ሃብት የማን ነው? ሃብታም እየበለፀገ፣ ደሃው እየደህየ የሚሄድበት ዓለም ውስጥ እንገኛለን፡፡

 • 50 በመቶ የዓለምን ኃብትና ንብረት የሚቆጣጠሩት 1 በመቶ የሚሆኑ ቢሊየነሮች ናቸው፡፡ 
 • 85 በመቶ የዓለምን ኃብትና ንብረት የሚቆጣጠሩት 10 በመቶ የሚሆኑ ሚሊየነሮች ናቸው፡፡  
 • 30 በመቶ የዓለምን ኃብትና ንብረት የሚቆጣጠሩት 97 በመቶ የሚሆኑ ህዝብ ናቸው፡፡                 

በዓለማችን ህዝብ ፍህታዊ ያልሆነ የሃብት ክፍፍል 2018 እኤአ ሪፖርት መሠረት፣ በአውሮፓ 10 በመቶ የሚሆኑ ቢሊየነሮችና ሚሊየነሮች 37 በመቶ የሚሆን ሃብትና ንብረት አላቸው፡፡ 10 በመቶ የሚሆኑ ኃብታሞች በቻይና 41 በመቶ ሃብትና ንብረት ይቆጣጠራሉ፣ 10 በመቶ የሚሆኑ ባለጸጎች በራሽያ 46 በመቶ ንብረት አላቸው፣ 10 በመቶ የሚሆኑ ቢሊየነሮችና ሚሊየነሮች በሰሜን አሜሪካ 47 በመቶ ኃብትን ይቆጣጠራሉ፣ 10 በመቶ የሚሆኑ ባለጸጎች ሳህራ በታች ባሉ አገራት 55 በመቶ ሃብትና ንብረት ይቆጣጠራሉ፡፡ (source:- world inequality report 2018 the poor keep getting poorer and the rich richer)             

በኢትዮጵያ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ከ2500 እስከ 3700 ሚሊየነሮች እንዲሁም አንድ 5 ቢሊየነሮች የሃገሪቱን 50 በመቶ የሚሆነውን ሃብትና ንብረት ይቆጣጠራሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ የኦዴፓ/ኢህአዴግ የፓርቲዎች የንግድ ድርጅቶች የህወሓት ኢፈርት፣ የብአዴን/አዴፓ ጥረት፣ የኦህዴድ/ኦዴፓ ዲንሾ፣ ደኢህዴን ወንዶ የፖለቲካ የንግድ ድርጅቶች 25 በመቶ የሚሆነውን ሃብትና ንብረት ይቆጣጠራሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የኢህአዴግ የፓርቲ ድርጅቶች ንግድ ውስጥ እንዳይገቡ እንኮን አለማሳሰባቸው አጃይብ ሆኖብናል፡፡  የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች 20 በመቶ የሚሆነውን ሃብትና ንብረት ይቆጣጠራሉ፡፡ ቀሪውን 97 በመቶ ህዝብ 15 በመቶ የሚሆነውን ሃብትና ንብረት ይቆጣጠራሉ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ እኔና አንተ ሁለት ክንድ የመካነ መቃብር ቦታ አለን! ስንዝሮ መሬት ካላለቀች፡፡ አዲስ አበባ የማን ናት? ፍንፍኔ የማን ናት? ህወኃት/ኦዴፓ ኢህአዴግ ደሃውን ህዝብ ለምን ያጋጫል!!! ለሥልጣን ሱስ፡፡ የጦር አበጋዞች የዘር አገዛዝ ከትግራይ ወደ ኦሮሞ እንዲቀጥል ከኦሮሞ ወደ አማራ፣ ሱማሌ፣ አፋር ወዘተ በዘር ተኮርነት በትረ ሥልጣኑ እንዲቀጥል በመለስ ዜና የጠነሰሰው የፖለቲካ ሴራ ነው፡፡ ድሬዳዋ የማ ናት? ሃዋሳ የማ ናት? አዳማ የማ ናት? ወዘተ ቀጣይ የፖለቲከኞች ሴራ ገና ይቀጥላል፡፡ ዛሬ አዲስ አበባ የማናት? ፍንፍኔ የማን ናት? የሚባለውን ጉንጭ አልፋ ክርክር በወፍ በረራ እንቃኛታለን፡፡

{1} ከ1928 ዓ/ም እስከ1933 ዓ/ም በጣልያን ወረራ ዘመን፣ ፋሽስት ጣልያን አዲስ አበባ ከተማን ፖፖላሬ፣ ካዛንቺስ፣ መርካቶ፣ ፒያሳ፣እያለ ዶቦ ሳይቆርስ ስም የጣልያን ስም አወጣላቸው፡፡

{2} ከ1967 እስከ 1983ዓ/ም ወታደራዊው መንግስት የገጠርና የከተማ መሬት ወረሰ፣ ትርፍ መኖሪያ ቤቶች ወረሰ፣ ፋብሪካዎች፣ የእርሻ ቦታዎች፣ ባንክና ኢንሹራንሶች በመንግስት ተወረሱ::

{3} ከ1983 እስከ 2011ዓ/ም ህወሓት/ኢህአዴግ የገጠርና የከተማ መሬት ወረሰ ቀጠለ፣ ትርፍ መኖሪያ ቤቶች ወረሰ ቀጠለ፣ ከመንግስት ዘርፍ ነቀላና ተከላ ከመንግስት ወደ ፓርቲ ንግድ ድርጅትነት ፋብሪካዎች፣ የእርሻ ቦታዎች፣ ባንክና ኢንሹራንሶች  በህወሓት ኢፈርት፣ ብአዴን/ አዴፓ  ጥረት፣ ኦህዴድ/ ኦዴፓ ዲንሾ፣ ደኢህዴን ወንዶ  ንብረትነት ተዘዋወሩ፣ የአላሙዲን ሜድሮክ ከፍተኛውን ሃብት ተቀራመተ፣ ወዘተ ወዘተርፈ

አዲስ አበባ የማን ናት? ፍንፍኔ የማን ናት?

በቀ.ኃ.ሥ ዘመን መንግሥት

 • ከፍተኛ የትምህርት ተቆማት ህንፃዎች፡- ዩኒቨርሲቲዎችና ትምህርት ቤቶች፣ አራት ኪሎ፣የሳይንስ ዩኒቨርሲቲ (ሚኒሊክ ት/ቤት፣ ትምህርት ሚኒስቴር)፣ አምስት ኪሎ የምህንድስና ዮኒቨርሲቲ፣ ስድስት ኪሎ የህግና የሶሻል ሳይንስ ዮኒቨርሲቲ፣ የግል ዩኒቨርሲቲዎችና ትምህርት ቤቶች በአመዛኙ የተያዘ መሬት ነው፡፡ ከአራት ኪሎ፣አምስት ኪሎ እስከ ስድስት ኪሎ የዮኒቨርሲቲ፣ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች(ሚኒሊክ፣ተፈሪ መኮንን)፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች (የሚኒሊክ ቤተመንግሥት፣ የኢሰፓ/ጊህአዴግ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ፣ ፓርላማ፣ የኢሠፓ/ ኢህአዴግ ፅህፈት ቤት ህንፃዎች፣ ወወክማ፣ ትምህርት ሚኒስቴር፣ የጳጳሱ መኖሪያ ህንፃ፣ የቤተክህነት ህንፃ ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ሥላሴ፣ ቅድስተ ማርያም፣  ምህካዬ ህዝናን፣ የአሜሪካ ኢንባሲ፣ መናፈሻ፣ 
 • የፋይናንስና የባንክ ዘርፍ ህንፃዎች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ንግድ ባንክ፣ 16ቱ የግል ባንኮች (ዳሽን፣ አዋሽ፣ ወጋገን፣ ህብረት፣አቢሲንያ፣ ወዘተ ) ቅርንጫፎቻቸው ከነልጅ ልጆቻቸው የተያዘ መሬት
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ማረፍያ፣ ሲቪል አቪየሽን፣ የተንጣለለ ሰፊ መሬት እስከ መስቀል አደባባይ ግራና ቀኝ የተሠሩ ህንጻዎች እንዲሁም ከለጋሃር ባቡር ጣቢያ በቸርችል ጎዳና እስከ ማዘጋጃ ቤት
 • የቤተ-ዕምነቶች ህንፃዎችና ሲሶ እርስት፣ የቤተክህነት፣ የመስጊድ፣ የፕሮቴስታንት፣ የቅዱስ ጊርጊስ ካቴድራል፣ የመንበረ ፀባዓት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን፣ ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን፣ የኢየሩሳሌም መታሰቢያ፣ የታላቁ አንዋር መስጊድ፣ የወሊ መሃመድ መስጊድ፣ የቢኒን ሰፈር መስጊድ፣ ግሪክ ኮሚኒቲ ህንፃ ወዘተ የመሬት ሃብትና ንብረት እንዲሁም የእኔና የአንተ ሁለት ክንድ የመካነ መቃብር ቦታዎች ብቻ ከቸሩን ከዛ ሥፍራ ሁላችንም የዘር ሃረግ ሳንጠቅስ፣ የፆታ ልዩነት ሳናደርግ፣ የቀለም ልዩነት ሳንሰብክ፣ የሃይማኖት ልዩነት ሳየኖረን፣ የፖለቲካ ጥላቻ ሳንሰብክ ወዘተ የምንኖርባት ስንዝር መሬት ናት፡፡
 • የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ርስተ ጉልት፡- ጀነራል ሙሉጌታ ቡሊ ጦር ሠፈር፣ መከላከያ ሚኒስቴር፣ ጦር ኃይሎች፣ ወታደር ፖሊስ፣ ፖሊስ ሆስፒታል፣ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል፣ የጦር ግምጃ ቤቶች፡- ጥይት ቤት፣ የመሣሪያ ግምጃ ቤት፣
 • የቀ.ኃ.ሥ ዘመን ህንፃዎች፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የኢትዮጵያ መብራት ሃይል፣ የውሃ ልማት፣ የቴሌኮምኒኬሽን፣ ፖስታ ቤት፣ ብርሃነ ሠላም ማተሚያ፣ ልዑል ራስ ዕምሩ፣ ብላታ አድማሱ፣ ኢብራሂም ሸኖ፣ ሃጂ ፈይሳ ደጋጋ፣ በድሉ ህንፃ፣ ተስፋዬ ቀጀላ ህንፃ፣ ፓፓሲኖስ፣ ዬርዳኖስ፣ ናዴል፣ ቪሊ ሳሪ፣ ቨርነሮ ህንጻ፣ ወዘተ
 • የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ቢሮዎች በየአፍሪካ ህብረት፣ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በአፍሪካ፣ ወዘተ
 • በመዲናዋ መሬት ላይ ፈረስ በሚያስገልብ ቦታ ላይ ተንጣለው የተሰሩ ኢንባሲዎች ብዛት፣ የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ፣ የጣሊያን፣ የእስራኤል፣ ካናዳ፣ ቡልጋሪያ፣ ጃፓን፣ ህንድ፣ ኢራቅ፣ ኢራን፣ ሳውዲ ዓረቢያ፣ ግብፅ፣ ኬንያ፣ ናይጀሪያ ኢምባሲ አረ ስንቱ!!!
 • በከተማዋ ውስጥ በተንጣለሉ ሰፋፊ ሥፍራዎች ላይ ታንጸው የተገነቡ ሌጋሲዬኖች ብዛት፣ ራሺያ፣ ዳች፣ ዩጎዝላቪያ፣ ቤልጅግ፣ ፈረንሳይ ለጋሲን አረ ስንቱ!
 • በከተማዋ የታነፁ ሆስፒታሎች፣ ዳግማዊ ሚኒሊክ፣ ዘውዲቱ፣ ቀ.ኃ.ሥ፣ ልዑል መኮንን፣ ልዕልት ፀሃይ፣ ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ፣ ፖሊስ ሆስፒታል፣ አማኑኤል ሆስፒታል አረስንቱ
 • ካሳንቺስ፣ ፒያሳና መርካቶ የተሰሩ የንግድ ቤቶች ሆቴሎች ወዘተርፈ
 • የአዲስ አበባ ሠፈሮች የተሰሩ ችምችም ያሉ የግል መኖሪያ ቤቶች፣ ልዑል ራስ ካሳ ሠፈር፣ ራስ ሙሉጌታ ቡሊ፣ ራስ ካሣ ሠፈር፣ ራስ ተሰማ፣ ራስ ስዩም፣ ደጃዝማች ውቤ፣ ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ፣ ደጃዝማች ገነሜ፣ ደጃዝማች ነሲቡ፣ ደጃዝማች ገብረስላሴ፣ ደጃዝማች ሃብተማሪም፣ ካሣ ገብሬ፣ ባሻ ወልዴ ችሎት፣ አባ ኩራን ሠፈር አረ ስንቱ አራዳ፣ ውቤ በርሃ፣ አዲስ ከተማ፣ አራት ኪሎ፣ ስድስት ኪሎ፣ ካዛንቺስ፣ ፖፖላሬ፣ አደሬ ሠፈር፣ አቦሬ፣ ቦሌ፣ ጉለሌ፣ ግንፍሌ፣ መካኒሳ፣ ገፈርሳ፣ ቂርቆስ፣ ቄራ፣ ሰንጋ ተራ፣ ሣር ተራ፣ እንጨት ተራ፣ ሱማሌ ተራ፣ ንፋስ ስልክ፣ እቴጌ መስክ፣ ጃን ሜዳ፣ ፍልውሃ ሜዳ፣ ሽሮ ሜዳ፣ ለገሃር፣ እንጦጦ፣ ቀጨኔ፣ ቀበና፣ ኮልፌ፣ ኡራኤል፣ ተክለሃይማኖት፣ የካ፣ ማይጨው፣ ቀራኒዎ፣ ጎፋ፣ ጎላ፣ ጌጃ፣ ልደታ፣ ካንጎ፣ ኮሪያ፣ ባንያን ሠፈር፣ እቃ ቤት፣ በቅሎ ቤት፣ አፍንጮ በር፣ ፊት በር፣ ሰራተኛ ሠፈር፣ ገዳም ሠፈር፣ ካህን ሠፈር፣ ነጋዴዎች ሠፈር፣ ነፍጠኛ ሠፈር፣ ወሎ ሠፈር፣ ጎጃም በረንዳ፣ አረ ስንቱ የአዲስ አበባ መንገዶች፣ አደባባች፣ ጎዳናዎችና ሠፈሮች እንደ ሸረሪት ድር ከላይ ታች፣ ሽቅብ ቁልቁል፣ በአራቱም ማዕዘናት አውቶሞቢሎች ኦፔል፣ ቮክስዋገን፣ ላንድሮቨር፣ ታኖስ፣ ዶጂ፣ ጂፕ፣ ሚሊቼንቶ፣ ሺሸንቶ፣ ፊያት፣ ቤቢ ፊያት፣ አንበሣ አውቶብስ፣ ሎንችና ኤንትሬ፣ ዶቅዶቄ፣ የፈረስ ጋሪ ቼ ፈረሴ፣ እልማ አለ ባቡሩ የሚዋቡባት ድንቅዬ ከተማ ነበረች፡፡ የአዱ ገነት አመሰራረት ዘር፣ ሃይማኖት፣ ፆታ፣ ቀለም ሳይለዩ በአብሮነት የኖሩባት የፍቅር ከተማ ነበረቺ፡፡

በህወሓት/ ኢህአዴግ ዘመን፣ በኢኮኖሚክስ የኃብት ክፍፍል ጥናት መሠረት፣ አዲስ አበባ የማናት? ፍንፍኔ የማን ናት? ለሚለው ጥናታዊ መልስ የጥቂት ከበርቴዎች ንብረት እንደሆነቺ መረዳት ይቻላል፡፡ ኢፍህታዊ የሃብት ክፍፍል በመዲናዋ፣ በወፍ በረራ እንቃኛታለን፡፡

 • የከተማና ቤቶች ሚኒስቴር፣ በመንግሥታና በቀበሌ የሚተዳደሩ 17 ሽህ የኪራይ ቤቶች ቤትና መሬት የመንግሥት ንብረት ናቸው፡፡
 • የ160 የግል ሪል ስቴት ከበርቴዎች መሬት፣ አያት ሪል ስቴት፣ የቻይና ፀሐይ ሪል እቴት ወዘተ
 • በፕራይቬታይዤሽን የተሸጡ ፋብሪካዎች፣
 • ኮንዶሚኒየም፣ አንድ መቶ አንድ የጀነራል መኮንኖች ኮንዶሚኒየም ህንፃዎች ስድስት ኪሎና ሲጊናል፣ እንዲሁም 10/90፣ 20/80፣ 40/60 ኮንዶሚኒየም ህንፃዎች መሬት  
 • የሼክ አላሙዲን ንብረት ሸራተን ሆቴል፣ እንድ ሽህ አንድ ድርጅቶቻቸው የተያዘ መሬትና ቅርብ ጊዜ የተነጠቁት የታጠሩ የትየለሌ ቦታዎች የሼኩ ነበሩ፡፡
 • የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት፣ 25 የክፍለ ከተማ ህንፃዎችና 100 ወረዳና ቀበሌ ቢሮዎች ፣ የመኪና ማቆሚያ ፓርኮች፣ቄራዎች፣ወዘተ
 • በህወሓት/ ኢህአዴግ ዘመን የተገነቡ የአዲስ አበባ ፎቆች የማናቸው ለናሙነት የተገለፁ ከ400 ፎቆች ውስጥ 42ቱ ብቻ አስተውሉ፣ 350 ፎቆች በህወሓት/ ኢህአዴግ የፓርቲ ድርጅቶች የህወሓት ኢፈርት ፣ የብአዴን ጥረት፣ የኦህዴድ ዲንሾ፣ የደኢህዴን ወንዶ የፓርቲዎቹ የንግድ ድርጅቶች ንብረትና ኃብት በብዛት እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

Buildings in Addis Ababa፡- The 42 buildings covered included the following: Dasset Building, Addis Fana PLC, Terfera Seyum Commercial, Kelifa Business Center, T.K International Building 1 & 2, Friendship, DH Geda, Dabi Complex, Saay building, Alem Building 1 & 2, Sevita Building, Salfaz Building, Mamitu Alamerw, Jambo Business Complex, Abyssinia Building, Daminaroff Building, TSBG International Trading, AHF International, Yoly building, Legesse Feleke, Aberus Complex, Dembel City Center, Menteweab, Mina, Tebaber Berta, Wongelawit Taddesse, Baleker Tower, Al Paulo Building, Alemu Woldetsadik Building, K-Kare Center, Adam’s Pavilon, Yezelalem Building, Geo-Traco building, Nur Building, ITMA S.C, St.Ledeta Health science College, TG building, Rebecca Building, Lex Plaza and Comet Building. Source:-www.ethioconstruction.net/

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ቅርምት በኢፈርትና ሜድሮክ  

በ1967 ዓም የኢትዬጵያ ወታደራዊ መንግስት (ደርግ) በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኙ በግል ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችን በአዋጅ ቁጥር 20/1974 ወደ መንግስት ሃብትነት በማዘዋወርና በመውረስ ፋብሪካዎች፣ባንኮችና ኢንሹራንሰ ኩባንያዋችን፣የከተማ ትርፍ ቤቶችን፣ የገጠር መሬትን፣ እርሻዎችን

ወዘተ በብሄራዊ ሃብትና እድገት ሚኒስትር( Ministry of National Resource Development) ስር የተወረሱትን ንብረቶች እንዲያስተዳድር ስልጣንና ሃላፊነት በአዋጅ ተሰጠው፡፡ በዚህም መሠረት፣የከተማ ትርፍ ቤቶችን አዋጅ ለማስፈፀም የመንግስት ኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ተቆቁሞ የወር ኪራያቸው ከመቶ ብር በታች የሆኑትን ቤቶች በቀበሌ አስተዳደር ስር እንዲተዳደሩ ተወሰነ፡፡ የወር ኪራያቸው ከመቶ ብር በላይ የሆኑትን ቤቶች በመንግስት ኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ እንዲተዳደሩ ተወሰነ፡፡

የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት፤ የከተማ መሬት በመሸጥ፤የገጠር መሬት በሊዝና ኮንትራት ከ60 እስከ 90 አመታት ለውጭ ሃገር ባለሃብቶች በመሸጥ የኢትዮጵያን ህዝብ የመንግስት ጭሰኛ ያደረገ በእውቀት የጨነገፈ የደደቢት ደደቦች መንግስት ነው፡፡ የኢትዮ ጵያን ህዝብ የግል ንብረት የማፍራት መብቱን ተነጥቆ በመሬቱ ላይ የመጠቀም መብት ብቻ እንዳለው በህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት ህገመንግስት ተደንግጎል፡፡ ከ1983 አ.ም የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት፤ በከተማ ልማት፤ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር፤ የመንግስት ኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ(የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ) በመቆጣጠር በአዲስ አበባና በሌሎች አገሪቱ ክልሎች የሚገኙ በድምሩ 17,549 ቤቶች ማስተዳደር ጀመረ፡፡ ከዚህ ውስጥ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ አስተዳደሮች በድምሩ 12,042 መኖሪያ ቤቶችና 5,507 የድርጅት ቤቶች መኖራቸውን የግል ኩባንያው በጥናቱ መረጃ ያረጋግጣል፡፡

የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት ከ1983 አ.ም ጀምሮ እስከአሁን እነዚህን መኖሪያ ቤቶች ለህወሃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደኢህዴን ወዘተ የጦር አበጋዞችና የፖለቲካ ካድሬዎች ከደርግ ሹማምንትና ካድሬዎችን ከቤታቸው እያስወጡ በነፃ ተቀራመቶቸው፡፡ የሚገርመው እነዚህ የክልል መንግስቶች በየክልላቸውና በአዲስ አበባ ውስጥ ሁለት የመኖሪያ ቤቶች እንደ ክረምትና በጋ ቤት ይዘው ይገኛሉ፡፡

በቤቶቹ ቅርምት የደደቢት ህወሃት የጦር አበጋዞችና የፖለቲካ ካድሬዎች የአንበሳውን ድርሻ ሲደርሳቸው ቀጥሎ የብአዴን፣ የኦህዴድ፣ደህዴድ ወዘተ ከቤቶቹ ቅርምት ኩርማን፣ሲሶና አስራት ቅርጫ ደርሶቸዋል፡፡ የህወሃት የጦር አበጋዞች አደዋ አደባባይ ሲግናልና ከተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ከፍ ብሎ ለ‹ኢትዬጵያ› መከላከያ ሰራዊት መኮንኖች መኖሪያነት ስም የተገነባውን ከ50 አስከ 100 የሚደርስ ምርጥ ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለህወሃት የጦር አበጋዞች መኖሪያነት ተሰጥቶል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማና በአጎራባች የኦሮሚያ ክልሎች የህወሃት የጦር አበጋዞች፤‹የህዝብ ደህንነት›ና የፖለቲካ ካድሬዎች ከአንድም ሁለት ሦስት መሬት እየተመሩና እየሸጡ የኢትዮጵያ ህዝብን ንብረት ለአለፉት 27 ዓመታት ዘርፈዋል፡፡

ይህ የተዘረፈ የኢትዮጵያ ደሃ ህዝብ ንብረት ከህወሓት/ ኢህአዴግ እጅ እስካሁን በኦዴፓ/ኢህአዴግ ሲመለስ አልታየም፡፡ እንዲያውም ኦህዴድ/ ኦዴፓ ከሱማሌ የኦሮሞ ተፈናቃዬችን አዲስ አበባ ሞጆና አዳማ ማስፈር የስብአዊ መብት ጥሰት ነው፡፡ ህዝብን ያለፍቃዱ በኃይል ማስፈር ማለትም የህዝብ አሰፋፈርን ለፖለቲካ ጥቅምና ለምርጫ ሲባል የሚደረግ ሴራ በኦህዴድ/ ኢዴፓ እየተከናወነ በመሆኑ ሰፋሪዎቹ ወደ መጡበት ቀያቸው እንዲሰፍሩ ማድረግ ያስፈልጋል እንላለን፡፡ የህወሃት የጦር አበጋዞችና ካድሬዎች የመሬት ቅርምትና የቤቶች ነጠቃ በኦህዴድ/ ኦዴፓ በዚህ ዓይነት የሙስና ስርዓት የመንግስት ኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ (የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ) አሠራር ከአሁኑ ማጋለጥ ያስፈልጋል እንላለን፡፡ ቤቶቹም ከመንግስት ወደግሉ ዘርፍ ሃብትነት ይሸጡ ይተላለፋ እንላለን፡፡ የመንግስት ሹማምንት ቤት፣ መሬትና መኪና የመሳሰሉትን ዓይነት ጥቅማ ጥቅሞችን ማግኘት ማስቀረት ያስፈልጋል፡፡ ህዝቡንም በቅንነትና በታማኝነት ያገለግላሉ፡፡

መለስ ዜናዊ መታሰቢያ የመሬት ቅርምት Meles Zenawi Foundation (MZF)

በመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ስም የመሬት ቅርምትና ነጠቃ በፌዴራል መንግስትና በሁሉም ክልሎች መንግስት ተጦጡፎ ነበር፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ መለስ ዜናዊ መታሰቢያ በሚል ካዛንችስ ወደ አቦሬ በሚወስደው መንገድ ላይ ከሚስስ ፎርድ መታሰቢያ ትምህርት ቤት ፊትለፊት  ሁለት ፎቅ ቤቶች በቢሮነት ተወስደዋል ፡፡ የሚያሳዝነው ብዙ የድሃ ልጆች የሚማሩበት በ ቀ.ኃ.ሥ ግዜ የተሰራው የሚስስ ፎርድ መታሰቢያ ትምህርት ቤት አርጅቶና ሊፈርስ ደርሶ እያለ ከፊት ለፊቱ ለስራ ፈቶቹ የተበረከተው ህንፃዎች ናቸው፡፡ የሚስስ ፎርድ(ፒዜድ) በመባል የሚታወቀው ትምህርት ቤት አፍሪካዉያንን ወደ ኢትዩጵያ ለመመለስ የተጠነሰሰ ውጥን ነበር፡፡ የሚስስ ፎርድ ልጆች ትምህርት ቤቱን ለማደስ አልተፈቀደላቸውም፡፡

 • በብዙ ሽህ ሄክታር የተያዘው ደን ፣የጉለሌ ቦታኒክ ጋርደን ወይም የጉለሌ የእዕዎት ማዕከል የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ተብሎ ተበርክቶል፡፡
 • የጆሲ ሂውማኒቴሪያን ፋውንዴሽን የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ፓርክ በሚል በጊንዶ ግንደበረት 1200 ሜትር ካሬ ቦታ ተወስዶል፡፡ በህዝባዊው ቁጣ የመለስ ዜናዊ ፓርክ ተቃጥሎል፡፡
 • በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለመለስ ዜናዊ መታሰቢያ 12000 ሄክታር መሬት ተወስዶል፡፡

አዲስ አበባ የማናት; ፍንፍኔ የማን ናት; ድሬዳዋ የማናት; አዳማ የማናት; ሃዋሳ የማናት; ወዘተርፈ የሚሉት የፖለቲከኞች ጨዋታ ደሃውን አማራ ከደሃው ኦሮሞ፣ ደሃውን  ወላይታ ከደሀው ሲዳማ፣  የማጋጨት የፖለቲካ ሴራ መሆኑን ወጣቱ ትውልድ ሊረዳ ይገባዋል፡፡ ደሃው ህዝብ የመቀበሪያ ቦታ እንኮን የለውም፡፡ የከተሞቹን ዙሪያ ገባውን አስተውል፣ ያ ህንፃ የማን ነው; ያ ቪላ ቤት የማን ነው;  ያ ሆቴል የማን ነው; ያ የንግድ ቦታ የማነው; ያ ፍብሪካ የማነው; ያ እርሻ ቦታ የማን ነው; የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ንብረት የቱ ነው; የአገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ኃብት የቱ ነው; እያልክ የምጣኔ ሃብት ይዞታን ሁኔታ ጠይቅ ተመራመር እንላለን፡፡  ኢኮኖሚክሱን ስታውቀው ፖለቲካው ይገባሃል እንላለን፡፡

የህግ ሉዓላዊነት ይከበር፣ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!!!

ኦዴፓ/ኢህአዴግ መንግሥት ለሌቦችና ሙሰኞች ከለላ አይስጥ!!!

ህገወጥ ቤቶችን ከማፍረሳችሁ በፊት የሙሰኛ ሌቦችና ነፍሰ ገዳዬችን ቤትና ምሽግ አፍርሱ!!!

በማሃይም የፖለቲካ ካድሬዎች ሴራ አትጋጭ!!! ገንቢ ሂስ ያብብ!!! ፖለቲካ የሽሮ መብያ አይሁን!