ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY        

የአዲስ አበባ ስታዲየሞች በፎቶ Addis Ababa Stadiums የአዲስ አበባ ስታዲየሞች፣ የኢትዮጵያዊያን ዜጎች ኃብት ናቸው!

አዲስ አበባ የማን ናት! ፊንፍኔ የማናት! የግብር ከፋዬች ኢትዮጵያዊያንና የአትሌቶቻችን ኃብት ናት፡፡ ለጀግኖቹ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶቻችን መታሰቢ ትሁን!

አዲስ አበባ ‹‹ ፊንፊኔን ከኛ!!! በረራ የእኛ!!!››

የትግራይ መንግስት ህግ ጥሷል፣ የኦሮሚያ መንግሥትም ህግ ጥሷል፣ የፌዴራል መንግሥቱ የህግ ሉዓላዊነትን ማስከበር ለአስር ወራቶች ውስጥ ተስኖታል፡፡ ህግ በሌለበት ሃገር የህዝብ የመኖር ዋስትና አጠያያቂ ነው፣ የህግ የበላይነት በኢትዮጵያ ይከበር እንላለን፡፡ ህወሓት/ ኢህአዴግ የ27 ዓመታት የዘር ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ መሠረቱ የተጣለው፣ አዲስ አበባ የማናት; ፍንፍኔ የማን ናት; ድሬዳዋ የማናት; አዳማ የማናት; ሃዋሳ የማናት; ወዘተርፈ የሚሉት የፖለቲከኞች ጨዋታ ደሃውን አማራ ከደሃው ኦሮሞ፣ ደሃውን  ወላይታ ከደሀው ሲዳማ፣ ኦሮሞውን ከሃረሪው፣ ሱማሌውን ከኦሮሞው ወዘተ የማጋጨት የፖለቲካ ሴራ መሆኑን ወጣቱ ትውልድ ሊረዳ ይገባዋል፡፡ በእነዚህ ከተማዎች ውስጥ በሰላም ተፋቅሮ የሚኖረው ህዝብን በዘር በማጋጨት የተካነው ህወሓት/ኦህዴድ ኢህአዴግ ሴራ ማክሸፍ ካልቻልን ስቃያችንን እናበዛዋለን፡፡  በኢትዮጵያ በክልል መንግሥቶች መኃል ህወሓት/ ኢህአዴግ በከለለው ድንበርና ወሰን ምክንያት 3 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝቡ ተፈናቅሎ እንደሚገኝ ልብ ይበሉ እንላለን፡፡         

የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን፣  ስታዲሞች (የአዲስ አበባ ስታዲየም፣ የአበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ አደይ ስታዲየም ወዘተ)፣ ስታዲየሞች፣የኢትዮጵያዊያን ዜጎች ኃብት ናቸው፣ብርቅዬና ድንቅዬ አትሌቶቻችን በዓለም የሃገራችንን ስም ያስጠሩባቸው በእነዚህ ስታዲየሞች እንዲሁም በጃልሜዳ፣ አብዬት አደባባይ፣ ሰልጥነው ጥሩ ውጤት ያመጡት፡ የእግር ኮስ ተጨዋቾቻችን ጊዩርጊስ፣ ቡና፣ ፋሲል፣ ደደቢት፣ ወዘተ ከነዚህ ስታዲሞችና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የተገኙ ስፖርተኞች ናቸው፡፡ ማንም ወጣት ችሎታ ይኑረው እንጂ በዘር፣ በብሄር፣ በፆታ፣ በቆንቋ፣ በቀለም ልዩነት ሳይደረግባቸው ኢትዮጵያን ያስጠሩ፣ ስንደቅ ዓለማችን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲውለበለብ ያደረጉ ጀግኖቻችን ናቸው፡፡ የማራቶን ንጉስ አበበ ቢቂላ፣ ማሞ ወልዴ፣ ምሩጽ ይፍጠር፣ በላይነህ ዲንሳሞ፣ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ገንዘቤ ዲባባ፣ መሠረት ደፋር፣ ወዘተ ለዚህ ኢትጵያዊነት ምሳሌት ናቸው፡፡ ኢትዮጵያን ወክለው እንጂ ዘራቸውንና ክልላቸውን ወክለው አልሄዱም፡፡ ባገኙትም የወርቅ ዋንጫና ሽልማት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ብዙዎቹ ምርጥና ድንቅ ሆቴሎች ገንብተው፣ ለወገናቸው ሥራ ፈጥረውና ከፍተኛ ግብር ከፍለው፣ ለሃገራቸውና ለወገናቸው አለይኝታ መሆን ችለዋል፡፡ የእኛ አገር ፖለቲከኞች ሯጮች ባይሆኑም ሰማይ ጠቀስ የወሬ ፎቅ ከመገንባት ሌላ ለሃገርና ለወገን ያተረፉት እልቂትና መፈናቀል እንደሆነ ህዝብ ያውቃል፡፡  ቀጣዮ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ከዚህ በመማር ለሃገርና ለወገን በመቆም፣ ብሎም ለአህጉራዊነት ለፓን አፍሪካኒዝም ህብረት መታገልና ዘልቆም ለዓለም አቀፋዊነት የሰው ልጆች ፍቅር መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ET 302 በቦይንግ አይሮፕላን 157 ሰዎች ሞተዋል፣ የ35 ሃገራት ዙጎች፣ የተለያዩ የሃይማኖት ዕምነት ተከታዮች፣ የተለያዩ ቀለምና ፆታ ያላቸው ሰዎች በአንድ ላይ የሞቱባት አሰቃቂ አደጋ የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የዓለም አቀፋዊነት ትስስር ዘመን እንጂ በዘር የተደራጁ የጦር አበጋዞች ዘመንና የጠባብ ጎሰኝነትና መንደርተኛነት የማህይማን ዘመን በሙዚም  እንጂ በእውን ዓለም የለም፡፡ ነፍስ ይማር!!! አትሌቶቻችን እንደ ጆርጅ ዊሃ የላይቬሪያ ፕሬዜዳንት እንደሆነው፣ በአገራቸው ፖለቲካ በመሳተፍና በመወዳደር ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን መወጣት ይጠበቅባችኋል፡፡ 

የስታዲየም ግንባታ፣ በአዲስ አበባ ከተማ በ2.47 ቢሊዩን ብር ብሄራዊ ስታዲየም በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ በባህር ዳር፣ በሃዋሳ፣ መቀሌ፣ ነቀምት፣ አሶሳ፣ ወልዲያ፣ ድሬ ዳዋና፣ ጋምቤላ ከተማዎች ውስጥ ብሄራዊና አለምአቀፋዊ ጨዋታዎች የሚያስተናግዱ ስታዲየሞች በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡ የቻይና መንግስታዊ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (State Egineering Corporation chainese company) በመገንባት ሥራ፣ የቻይና ኤግዚም ባንክ በማበደር ስራ፣ ኤም ኤች ኮንሰልቲንግ ኢንጅነሪንግ በአማካሪነት ሥራ የኢትዮጵያ ስታዲሞች በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በ2009እኤአ የሰመራ ስታዲየም በ727 ሚሊዩን ብር የግንባታ ወጪ ተጀምሯል፡፡

Reported የኢትዮጵያ ስታዲሞች (Ethiopian Stadiums)

No Ethiopian Stadiums seat capacity construction costs area sqm
1 Adama 80,000 1.7 billion Birr 82million USD
2 Bahir Dar 60,000 1.2 billion Birr (estimation)
3 Gambella 30,000 375 million Birr(18million USD)
4 Mekelle 35,000 331 million birr (22million USD)
5 Awassa 40,000 350 million birr (estimation)
6 Nekemte 20,000 80 million birr
7 Dire Dawa 70,000 1.5 billion Birr (estimation)
8 Woldiya 25,000 331 million birr (22million USD)
9 Adey Addis Ababa 60,000 2.4 billion Birr
10 Semera 30,000 727 million birr
11 Assosa 30,000 300 million birr
Total 10.014 billion Birr
No Addis Ababa Stadiums seat capacity construction costs
1 Yeka (at Ferensai Legasion) 25,000 566,666,666.66 (27.3million USD) 31,000sqm
2 Nifas silk ( at Lafto) 30,000 375 million Birr(18million USD) 113,000sqm
3 Bole (at CMC) 30,000 375 million Birr(18million USD) 113,000sqm
4 Gullele(at Semene Hotel) 25,000 566,666,666.66 (27.3million USD) 31,000sqm
5 Arada (at Bell Air) 25,000 566,666,666.66 (27.3million USD) 31,000sqm
Total 2.45 billion Birr(118 million USD)

በ2009 የወጣ መረጃ መሠረት ከዓለም የእግር የእግር ኮስ ደረጃ ሠንጠረዥ የኢትዩጵያ የእግር ኮስ ደረጃ 124ኛ እንደሆነ ይፋ ተደርጎ ነበር፡፡ የኃይለሥላሴ ስታዲየም በኃላ ስሙን ቀይሮ አዲስ አበባ ስታዲም የተባለው በ1940 ዓ/ም ተገነባ፡፡ ስታዲየሙ 35 ሽህ ህዝብ ማስቀመጥ ይችልል፡፡ ከዚህ ሌላ የይድነቃቸው ተሰማና የአበበ ቢቂላ ትንሽ ስታዲየሞች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ግዜ በኢትዩጵያ ውስጥ አስራአንድ  ስታዲየሞች በመገንባት ላይ ይገኛሉ፣ የግንባታ ወጪያቸውም በግምት 10 ቢሊዩን ብር በላይ ይገመታል፡፡ እንዲሁም አምስት ስታዲሞች በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ውስጥ በ2.45 ቢሊዩን ብር ወጪ ለመገንባት በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡ የአዲስ አበባና የአዳማ ስታዲየም ግንባታ በቻይናው (State Egineering Corporation chainese company) እንደሚገነባ ታውቆል፡፡

በኢትዮጵያ የከተማ ንዋሪዎች ከመቶ ሃያ እጅ ሲይዝ የገጠሩ ንዋሪ ደግሞ ሰማንያ በመቶ እጅ ይይዛል፡፡ ከተሞች የኢትዮጵያውያን ግብር ከፋዬች ኃብት ናቸው!!! ከተሞች የህብረ ብሔሮች ኢትዮጵያዊያን መቅለጫ መዲኖች ናቸው፡፡ የተለያዩ  ዘሮች፣ የተለያዩ ሀገር ሰዎች፣ የተለያዩ የዕምነት፣የፆታና የአስተሳሰብ ተቀይጠውና ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ህዝብ  የሚኖሩባቸው ከተሞች ውስጥ  አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ሃዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ጅማ፣ ባህርዳር፣ ደሴ፣ ደብረብርሃን፣ ጅግጅጋ፣ ጋምቤላ፣ ጎንደር፣ መቐለ፣ ወዘተ የከተማው ህዝብ እራሱን በእራሱ የማስተዳደር፣ ከንቲባውን የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብት አለው እንላለን፡፡  የሠለጠኑ ከተሞች የሃገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮችን በመሳብ ከተሞቻቸው ውስጥ ምዕዋለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በማድረግ ለስራ አጥ ወገኖቻቸው የሥራ እድል በመፍጠር ለመንግሥት ግብር በማሳደግ  የከተማው ህዝብና ኢኮኖሚ እድገትና ብልፅግና የሚያጎናፅፉ የተማሩ ከንቲቦች ያስፈልጎቸዋል፡፡ ከተሞቹን ለሃገር ውስጥና ለባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ሆስፒታል፣ ስታዲየም፣ የመንገድ ፣ የባቡር ግንባታ እንዲያደርጉ በመሳብ ከተማቸውን ያዘምናሉ፣ ለደሃው የከተማ ህዝብ የመኖሪያ ቤቶች በመገንባት ተጠቃሚና ፍህታዊ የኃብት ክፍፍል እንዲኖር የሚያደርግ እውቀት ያላቸው ሰዎች በህዝብ ተመርጠው፣ ከንቲባ ሆነው  በመምራት ከተማዋን ህዝብ ባፀደቀው የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ጉዳይ ፍኖተ ካርታ በመመራት ከተማዋን በተጠያቂነት፣ በሃላፊነት፣ የሚመሩ መሪዎች ያስፈልጎቸዋል እንላለን፡፡ 

ቀነኒሳ ሆቴል አዲስ አበባ፣  ኃይሌ ሆቴል ሃዋሳና አርባ ምንጭ፣ ደራርቱ ሆቴል አሰላ፣አትሌቶቻችንን የየከተሞቻችን የበላይ ጠባቂ  ብናረጋቸው በኢንቨስትመንት ሥራ በመፍጠር ራሳቸውን ጠቅመው ደሃውን ህዝብ ይረዳሉ፡፡ለሃገር ወዳዶቹ፣ ለጀግና አትሌቶቻችንን ክብር እንስጣቸው፡፡

Source:-

{1}Top of Form

  • Bottom of Form

Addis Ababa Stadium – Wikipedia/ https://en.wikipedia.org/wiki/Addis_Ababa_Stadium/ Addis Ababa Stadium is a multi-purpose stadium in Addis Ababa, Ethiopia. It is used mostly for football matches although it also has athletics facilities./ Capacity‎: ‎35,000 Location‎: ‎Addis Ababa, Ethiopia Former names‎: ‎Haile Selassie Stadium Opened‎: ‎1940

{2}Bahir Dar Stadium – Wikipedia/ https://en.wikipedia.org/wiki/Bahir_Dar_Stadium/ Bahir Dar Stadium(Amharic: ባህር ዳር ስታዲየም) is a multi-purpose stadium in Bahir Dar, Ethiopia. It is used mostly for football matches although it also has …/World Stadiums – Stadiums in Ethiopia/www.worldstadiums.com › Africa/A 3, Tenant/use, City, Stadium, Capacity, Built, Seats. ETH, National Stadium, Multi-use, Bahir Dar, Bahir Dar Int’l Stadium, 60 000, 2015, -. ETH, Ethiopian … Missing: numbers

{3}Adama to build a new 80,000-seat Stadium – Ethiosports/ www.ethiosports.com › Latest News › Sports Facilities › Stadiums/ 23 Jul 2015 – Adama, Ethiopia – The city of Adama is planning to build a new 80,000-seat stadium at a cost of 1.7 billion Birr ($82 million US), reported …

{4}Modern Stadium in Ethiopia – Saint George Football Club/ www.saintgeorgefc.com › News / Chinese company builds modern stadium in Ethiopia … The company has also carried out a number of projects in different countries including Namibia, …

{5}Ethiopia: Number of Premier League Clubs Reaches 16 – allAfrica.com/ allafrica.com/stories/201608090785.html/ 9 Aug 2016 – The number of the country’s elite league, the Ethiopian Premier League football club … Woldiya City will have their modern stadium in Woldiya.

{6}Ethiopia: Construction to start on new national stadium in Addis Ababa …/ stadiumdb.com › News › 2016 › January/ 7 Jan 2016 – Yesterday central authorities finally signed the long-anticipated deal for new national stadium in Ethiopia. Chinese contractors should begin …  Missing: numbers

{7}Ethiopian Sport – 40,000 seat Modern Stadium under Construction in … https://www.diretube.com/ethiopian-sport-40000-seat-modern-stadium-under-constru…/ 24 Oct 2013 – 40000 seat Modern Stadium under Construction in Ethiopia [Hawassa]Ethiopian Sport…

{8}Stadiums in ethiopia | Ongoing – Page 6 – SkyscraperCity/ www.skyscrapercity.com/showthread.php?t=1650257&page=6/ 19 Jul 2015 – 20 posts – ‎12 authors

Page 6- Stadiums in ethiopia | Ongoing General Ethiopia. … Can you just imagine, how many football clubs can be created based in these …

{9}Hawassa International Stadium to host Ethiopia’s last AFCON Qualifier/ www.soka25east.com/hawassa-international-stadium-host-ethiopias-last-afcon-qualifier/

26 Jul 2016 – It adds to three the number of approved stadiums in the country after Addis and Bahirdar Stadiums. Bahirdar hosted Walia’s 2-1 win over …

Searches related to Numbers of stadium in ethiopia

{10}addis ababa stadium new design/mekelle stadium 2015/woldia stadium ethiopia/awassa new stadium/adey abeba stadium/mekelle new stadium/hawassa stadium/nekemte stadium