ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

በኢትዩጵያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የአካል  ጉዳተኞች ይኖራሉ፡፡ የትግራይና የአማራ ምሁራን የወልቃይትና የራያን ህዝብ ጥያቄ በምንም መንገድ ወደ ማያባራ ጦርነት መግባት አይኖርባቸውም እንላለን፡፡ የወልቃይት ህዝብ ብዛት 55100 እንዲሁም የራያ ህዝብ ብዛት 87638  እንደሚደርስ ከ1994 ዓ/ም የስታሰቲክስ ቢሮ መረጃ ያሳያል፡፡ የትግራይና አማራ ክልላዊ መንግሥቶች በማኃላቸው የሳሉትን ሰው ሰራሺ የድንበርና ወሰን አስወግደው፣ የጥላቻ ፖለቲካን አስወግደው፣ በሁለቱ በሚነሳ ጦርነት ከውድቀት ሌላ የሚፈይዱት እድገት ስለማይኖር የዲጂታል ዘመን ወጣቶች ወደፊት ለሚጠብቃቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዬች የጋራ ውርስ በመማር ጦርነትንና የጥላቻ ፖለቲካ ቅስቀሳን በማስወገድ የወልቃይትና ራያን ጉዳይ በሽማግሌዎች መፍታት ይጠበቅባችኋል፡፡ የሁለቱ ክልል መንግሥቶች የወልቃይታና ራያን ህዝብ በኢኮኖሚ በመገንባት፣ የመኖሪያ ቤቶች በመገንባት፣ የገበያ ቦታዎች በመገንባት፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ከ150 እስከ 200 ሽህ ለሚደርሰው ህዝብ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በባህል በማቀራረብ የጥንቱን ፍቅራቸውን በማስፈን ወንጀል ከመፈፀም መቆጠብ የሰለጠኑ  ሰዎች መፍትሄ ይሆናል እንላለን፡፡ የኢትዬጵያ ህዝብም አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የተፈናቀሉትን ሰዎች ወደ ቀድሞ ስፍራቸው ማስፈር ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በኢትዩጵያና በኤርትራ የባደማ ፆረና ጦርነት ከሰባ እስከ መቶ ሽህ ዜጎች ከሁለቱም አገራት እንደሞቱ፣ ምን ያህል ሠራዊት እንደቆሰለና የአካል ጉዳተኞች እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ ሁለቱ ክልሎች በወልቃይትና ራያ  ጦርነት መግባት አይጠቅምም እንላለን፡፡  ትግራይም፣ አማራም፣ ወልቃይትም፣ ራያም ኢትዮጵያዊያን ናቸውና!!!

በ1994 ዓ/ም በኢትዩጵያ በተካሄደ የህዝብ ቆጠራ 988,853 የአካል  ጉዳተኞች መኖራቸው ታውቋል፡፡ በዛን ግዜ 53,073,322 ሚሊዩን ህዝብ ብዛት ውስጥ 1.9 በመቶ ዜጎች የአካል ጉዳተኞች ነበሩ፡፡ የአካል ጉዳተኞች፣በደረሰባቸው የአካልና የስነ-ልቦና ጭንቀት ምክንያት ጤነኛ ሰዎች ሊሰሩት የሚችሉትን ሥራ መሥራት ይሳናቸዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ገቢ የሚያስገኝ ሥራና የማህበራዊ ኑሮ ህይወት መምራት አይቻላቸውም፡፡ ከሠንጠረጅ ላይ በኢትዩጵያ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የሚገኙ የአካል  ጉዳተኞች ብዛትና የመቶኛ ንፅፅር እንቃኝ፡፡

Table 2-B: – prevalence of disability by regional states of Ethiopia (1994 census)

No ተ/ቁ              Region   

    ክልል

All persons             የህዝብ ብዛት PWD’s           የአካል ጉዳተኞች Ratio     ንፅፅር በመቶኛ
1 Oromiya 18,465,449 333,653 1.80%
2 Amhara 13,828,909 281,291 2.03%
3 SNNP 10,368,449 174,941 1.69%
4 Tigray 3,134,470 90,742 2.80%
5 Addis Ababa 2,100,031 45,936 2.18%
6 Somali 3,382,702 34,156 1.00%
7 Afar 1,097,067 14,140 1.29%
8 Benshangul & Gumuz 460,325 7,341 1.59%
9 Dirdawa 248,549 4,226 1.70%
10 Harari 130,691 2,909 2.23%
11 Gambella 162,271 2,581 1.59%
Total                         53,379,035 991,916 1.85%

PWD (People With Disabilities)

Baseline Study on the Status of Persons with Disabilities and the Influence of the African Decade Pronouncement in Ethiopia may, 2010

የጦርነት አዙሪት፣ኢትዩጵያ ከጦርነት አዙሪት ውስጥ ወጥታ አታውቅም ለአርባና ሃምሳ ዓመታት በተደረገ ውጊያ ብዙ ዜጎቻችን የአካል ጉዳተኞች ሆነዋል፡፡ የጦርነት ሰለባ የሆኑ፣ አካል ጉዳተኞች በሃገሪቱ ትክክለኛ ማስረጃ ለማግኘት ባይቻልም፣በአንደኛ ደረጃ በኦሮሚያ ክልል 333,653፣በሁለተኛ ደረጃ  በአማራ ክልል 281,291፣ በሦስተኛ ደረጃ በደቡብ ክልል 174,941፣በአራተኛ ደረጃ በትግራይ ክልል ከ90,742 ሽህ አካል ጉዳተኞች እንዳሉ የኢትዩጵያ ስታትስቲክስ ፅ/ቤት መረጃ ይገልፃል፡፡ ጦርነት የሚያካሂድ አገር በኢኮኖሚ ሊበለፅግ አይችልም፡፡ ደርግና ህወሓት አንባገነኖች በጦርነትና በኃይል የሚያምኑ በመሆናቸው ሃገር በኢኮኖሚ ሊበለፅግና ህዝብ ከድህነት አረንቆ ሊወጣ አልቻለም፡፡ የፖለቲካ ልዩነታችንን፣በጠረጴዛ ዙሪያና በሰለጠነ መንገድ በውይይት ችግሮቻችንን መፍታት እስካልቻልን ድረሰ ዓለም ከደረሰበት ስልጣኔ መድረስ ቀርቶ ዜጎቻችን ከርሃብ፣ ከድንቁርና፣ ከስደት፣ ከአካል ጉዳተኞች፣ከሥነ-ልቦና ጠባሳ ለመውጣት አይቻልም፡፡ በጦርነት የሚዳክሩ ሃገራት ምርታቸው የግብርና ምርት፣ የኢንዱስትሪ ሸቀጣ ሸቀጦች ሳይሆን የሃገር ገንቢ ዜጎቻቸው ሞትና የአካል ጉዳተኛ ምርት ሲያጭዱ ነው የሚኖሩት፡፡ ኢትዩጵያ በጦርነት አዙሪት ውስጥ ተዘፍቃለች፡፡ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በጦርነት ኢኮኖሚ መቅኒው ድረስ ተበልቶል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ በተደጋጋሚ የአስቸኮይ ግዜ አዋጅ ስበብ ብዙ ወጣቶች ገሏል፣አካለ ስንኩል አድርል፡፡ በየእስር ቤቱ በኢሰበአዊ ግርፋት ብሁ ዜጎች እግርና እጃቸው ሽባ ሆኖል፣ ሥነ- ልቦናቸው ተናግቷል፡፡ ሃገሪቱን በጦርነት ኢኮኖሚ  ዘፍቋል፣‹‹ሁሉ ነገር ወደ ጦር ግንባር!›› እንደ ደርግ ካለ ሠነበተ፡፡ በሰው ሠራሽ፣ ፀረ-ሰው ፈንጅ፣ ፀረ ታንክ ፈንጅ፣ የእጅ ቦንቦች የጦር መሣሪያዎች የሚሞተውና የሚቆስለው ወገኖቻችን ቤቱ ይቁጠራቸው!!! ለዚህ ነው ‹‹የሰው አንገት ከመሠየፍህ በፊት አስብ፣ ምክንያቱም መልሰህ አተክለውምና!!!››የሚሉት የቻይና አበወች ምክር ማስታወስ የሚገባው፡፡ በ2010 እኤአ የህዝብ ቆጠራ በኢትዩጵያ 805,492 የአካል ጉዳተኞች መኖራቸው ታውቆል፡፡ ከኢትዩጵያ 73,750,932 ሚሊዩን ህዝብ ብዛት  1.1 በመቶ ዜጎች የአካል ጉዳተኞች ነበሩ፡፡ በኢትዩጵያ የአካል ጉዳተኞች ቁጥር ከ1994 እኤአ እስከ 2010 እኤአ መቀነስ ዋና ምክንያት  የህዝብና የቤቶች ቆጠራ ወቅት፣ አባወራዎችና እማወራዎች በጎጂ የባህል ተፅዕኖ ምክንያት በቤተስቡ ውስጥ የሚገኝ አካል ጉዳተኛን ባለማስመዝገባቸው ነበር፡፡ በኢትዩጵያ ጠቅላላ የአካል ጉዳተኞች በክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች፣ የህዝብ ብዛት፣የአካል ጉዳተኞች ቁጥርና፣ በፆታ ያለው ንፅፅርን ከሠንጠረጅ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡

በኢትዩጵያ ጠቅላላ የአካል ጉዳተኞች ብዛት፣ በፆታ በ2010 እኤአ

ተ/ቁ ክልልና ከተማ ማስተዳደሮች የህዝብ

ብዛት

ጠቅላላ የአካል ጉዳተኛ ወንድ

የአካል

ጉዳተኛ

ሴት

የአካል  ጉዳተኛ

1 ኦሮሚያ 26,993,933 282,544 153,231 129,313
2 አማራ 17,221,976 198,694 101,522 97,172
3 ደቡብ 14,929,548 170,113 90,461 79,652
4 ትግራይ 4,316,988 69,017 35,802 33,215
5 አዲስ አበባ 2,739,551 32,630 17,931 14,699
6 ሶማሌ 4,445,219 24,223 14,206 10,017
7 አፋር 1,390,273 9,950 5,887 4,063
8 ቤኒ-ሻንጉል 784,345 8,486 4,621 3,865
9 ድሬዳዋ 341,834 3,778 2,069 1,709
10 ጋምቤላ 307,096 3,549 1,936 1,613
11 ሃራሪ 183,415 1,790 952 838
12 ልዩ ቆጠራ ቦታዎች 96,754 718 386 332
በኢትዩጵያ አጠቃላይ ድምር 73,750,932 805,492 429,004 376,488

ምንጭ‹-  የኢትዩጵያ ፊዴራል ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ማዕከላዊ ስታስቲክስ ፅህፈት ቤት፣  ኦግስት 2010፣ አዲስ አበባ ገፅ 134-138

በኢትዩጵያ የአካል ጉዳተኞች ትልቁ ችግር ሰው ሠራሽ የአካል ክፍል (Prosthetics)፣ ተሸከርካሪ ወንበሮች፣ምርኩዝ (Crutch)፣ወዘተ የመሳሰሉት መገልገያዎች እጦት የተነሳ አስታዋሽ አጥተው ይሰቃያሉ፡፡ 

የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት የትግራይ ክልል ህዝብን በጦርነት አዙሪት ውስጥ አስገብተውታል፡፡የትግራይን ህዝብ ከኤርትራ ህዝብ፣ ከጎንደር ህዝብ፣ ከአፋር ህዝብ፣ ከወሎ ህዝብ መሬት በመዝረፍ፣ ታላቆን ትግራይ በመሬት ቅርምትና ዘረፋ ለማሳደግ በሚያደርጉት ጥረት ሃገሪቱንና የትግራይ ህዝብን ወደ ማያባራ ጦርነት ውስጥ ከተዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በትግራይ ክልል ከ90 ሽህ አካል ጉዳተኞች እንዳሉና ወደፊትም በዚህ የጦርነት አዙሪትና የማያባራ ጦርነት፣ ይህ አሃዝ እንደሚጨምር ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ህወሓት በትግራይ ክልል መሽጎ ወንጀለኞችን አሳልፎ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ ህወሓት በትግራይ ክልል ልዩ ፖሊስ፣ ልዩ ኃይልና ህዝባዊ ሚሊሽያ 1.2 ሚሊዮን ታጣቂ በማደራጀት፣ በዘረፉትን የጦር መሣሪያ ታንኮችና የጦር አውሮፕላኖች  በመመካት አጎራባች የአማራ ክልሎች አካባቢ ሠፈራ በማድረግ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ የአማራም ክልል በተመሳሳይ  ልዩ ፖሊስ፣ ልዩ ኃይልና ህዝባዊ ሚሊሽያ በማደራጀት ህዝብ በማስታጠቅ ላይ ይገኛል፡፡ በመላ ሃገሪቱ የመሳሪያ ዝውውርና የገንዘብ ዝውውር በአስደንጋጭ መልኩ ሲሽለከለክ ሠንብቶል፡፡ ያለፈው አልበቃ ብሎ ወንድም ወንድሙን ለመግደል በዘር ተከፋፍሎ ዶልቶል፣ ማንም አሸነፈ ማንም የሁላችንም ምርት የወጣቶች እልቂትና የአካል ጉዳተኞች ምርት ከመጨመር ሌላ የወልቃይት፣ ራያና አፋር ወዘተ የመሬት ጥያቄ በሽማግሌዎች ያለምንም ደም መፋሰስ መፍትሄ ማግኘት ይችላል፡፡ ወደ ህሊናችን እንመለስ ለሚቀጥለው ትውልድ ፍቅር እናውርሰው፣ ጥላቻን አናውርሰው፡፡ የአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሃዋሳ ወዘተ የከተማው ህዝብ፣ በህዝብ የተመረጠ ከንቲባ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት በፌዴራል መንግሥት የከተማ አስተዳደር ፖሊሲ በህዝብ ውይይት በማድረግ ተግባራዊ መሆን አለበት እንላለን፡፡ በውይይት ሁሉም ነገር ይፈታል፡፡ ካለፈው ታሪካችን እንማር፡-   

 • በኢትዩጵያና በኤርትራ ጦርነት ከሰባ እስከ መቶ ሽህ ዜጎች ከሁለቱም አገራት እንደሞቱ፣ ምን ያህል ሠራዊት እንደቆሰለና የአካል ጉዳተኞች እንደሆኑ መረጃ አልተገኘም፡፡
 • በ1997ዓ/ም ምርጫ ወቅት ከ200 ሰዎች በላይ ተገድለዋል፣ ከ5000 ሽህ ሰዎች በላይ በጥይት ቁስለኛ ሆነው የአካል ጉዳተኞች ሆነዋል፡፡ በ2007/8 ዓ/ም በኦሮሚያ ህዝባዊ እንቢተኛነትና የአማራ ተጋድሎ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስ ሠራዊት፣ የአጋዚ ጦር ከ1500 ሠላማዊ ሠልፍ የወጡ ዜጎቻችንን ገድለዋል፣ ብዙ ሽህ ሰዎች በጥይት ቆስለው የአካል ጉዳተኞች ሆነዋል፡፡ በጋምቤላ ከ400 ሰዎች ተገድለዋል፣በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል፡፡ በሲዳማ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ዜጎች በግፍ ተረሽነዋልና ቆስለዋል፡፡ በአረካ ብዙ ሰዎች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፡፡ ከለውጡ በኃላ ለእነዚህ ሠማዕታት መታሰቢያ እንኮን አልቆመላቸውም፣ የመለስ መታሰቢያ ለነዚህ ሠማዕታት መታሰቢያ መሆን ይገባዋል እንላለን፡፡     
 • በ1994 የህዝብ ቆጠራ በኢትዩጵያ 988,853 የአካል ጉዳተኞች መኖራቸው ታውቆል፡፡ ከኢትዩጵያ 53,073,322 ሚሊዩን ህዝብ ብዛት 1.9 በመቶ ዜጎች የአካል ጉዳተኞች ነበሩ፡፡ በ2008 ዓ/ም ምን ያህል የአካል  ጉዳተኞች ይኖራሉ;
 • በኢትዩጵያ ውስጥ 4.6 ሚሊዩን ህፃናቶች ከወላጆቻቸው አንዱን በሞት የተነጠቁ ናቸው፡፡ በዚህም የተነሳ ሃገሪቱ ከዓለማችን የሙት ልጆች መኖሪያ ለመሆን በቅታለች፡፡
 • በኢትዩጵያ ውስጥ 1.2 ሚሊዩን ህዝብ በኤችአይ ቪ/ኤድስ በሽታ ጋር አብሮ ይኖራል፡፡ 800 ሽህ ህጻናት ከዚህ በሽታ ጋር በተያያዘ ወላጃቸውን አጥተዋል፡፡
 • በኢትዩጵያ በዓመት ከአንድ ሽህ ዜጎች መካከል ዘጠኙ ወደ ሌሎች አገራት ይሰደዳሉ፡፡ በ2015 እኤአ በኢትዩጵያ የሥነ-ህዝብ ቁጥር  99,465,819 ሚሊዩን ውስጥ 795,726 ሽህ ህዝብ በዓመት እንደሚሰደዱ ተገልፆል፡፡
 • በ2011 ዓ/ም 8.3 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኮይ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል እንደተባበሩት መንግሥት መረጃ መሠረት፡፡ በመላ ሃገሪቱ እስከ 3 ሚሊዮን ህዝብ ከቀየው ተፈናቅሎ በርሃብ አለንጋ እየተገረፈ ይገኛል፡፡ የዲያስፖራው ዜጋችን በታማኝ በየነ ስብዓዊ የድጋፍ ጥሪ 30 ሚሊዮን ብር በማሰባሰብ ለወገን ያለቸውን ፈጣን እርዳታ ዲያስፖራው ዛሬም ሲሶ መንግሥትነታቸውን አስመስክረዋል እንላለን፡፡

ምንጭ፡-Source:

 1. Baseline Study on the Status of Persons with Disabilities and the Influence of the African Decade Pronouncement in Ethiopia may, 2010
 2. የኢትዩጵያ ፊዴራል ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የ1994ዓ/ም፣ የህዝብና የቤቶች ቆጠራ በኢትዩጵያ፣ ማዕከላዊ ስታስቲክስ ፅህፈት ቤት፣ ጁን 1999፣ አዲስ አበባ ገፅ 60-62
 3. የኢትዩጵያ ፊዴራል ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ማዕከላዊ ስታስቲክስ ፅህፈት ቤት፣ ኦግስት 2010፣ አዲስ አበባ ገፅ 134-138
 4. Mekelle University College of Business and Economics Department of Cooperative Studies, The Role of Cooperatives In Unlocking Potentials of People with Disability: The Case of Tigray War Veterans in Mekelle, By Tesfahunegn Hailemariam Degefu/ September, 2011

ሃገሪቱ የግብርና ምርት እንጂ የአካል ጉዳተኛ ምርት አያስፈልጋትም!!! 

ችግራችንን በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት እንፍታ!!!

በጦር መሣሪያና በኃይል የህዝብ ችግር አይፈታም!!!

ህወሓት/ ብአዴን/ ኦህዴድና ደኢህዴን/ ኢህገዴግ የጦር አበጋዞች መንግሥት ምላጭ በመሳብ አረጁ፣ ዘመኑ የሚሻው ህሊናን መሳል ነው!!!