ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

“ለተገፋ ሁሉ ፍርድ እንዳይታጣ፣

ድመት ሌሊት አይሂድ፣ አይጥም  ቀን አይምጣ፡፡”

ኢሣት በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዬች ያላሰለሰ የመረጃ ምንጭ በመሆን ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ በመሆን ሲያገለግል አመታት አስቆጥሯል፡፡  ሆኖም ኢት-ኢኮኖሚ/ /ET-ECONOMY መጣጥፎች ከአገር ውስጥ የምጣኔ ኃብት ሙያተኞች በተለያዩ ድረ-ገፆች ማለትም በሳተናው፣ አባይ፣ ዘሃበሻ፣ ኢትዮጵያ ኤክስፕሎለር፣ አትዮሚዲያ ወዘተ ድረገፆች ለብዙ አመታት ሽፋን አግኝቷል፡፡ ከማንም በላይ ብዙ አንባቢዎች ለማግኘቱ የድረ- ገፆቹ ባለቤቶች ምስክርነታቸውን ሊሰጡ ይገባል እንላለን፡፡ ኢት-ኢኮኖሚ/ /ET- ECONOMY ለኢሣት ጋዜጠኞች ለአበበ ገላውና ሃብታሙ አያሌው እንዲያሳትመው በመፍቀድ፣ በዛ ክፉ ዘመን የደረሰ ጥናታዊ መጽሃፍት ሲሆን በኢሣት ፕሮግራሞች አልቀረበም፡፡ የኢት- ኢኮኖሚ ፁሁፎችና መጽሃፍቶች  በብዙ ድረ-ገፆች ሽፋን ያገኙ ሲሆን በኢሣት አለመቅረባቸው የመረጃዎቹ አስተማኝ ስላልሆኑ ታስቦ ከሆነ  መልስ ሊሰጥበት ይገባል እንላለን፡፡ የኢት-ኢኮኖሚ ዋነኛ ዓለማ በኢኮኖሚው ዘርፍ ለሃገርና ለወገን በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ጥናታዊ ፁሑፍ በማቅረብ በተለያዩ ድረ-ገፆች ተደራሽነት በማግኘታችን ደስተኛ ከመሆን ሌላ እስከመቃብር እውቅና የማንሻ በብዕር ስም ብቻ የምንታወቅ ስንሆን ከአመታት በፊት፣ ከለውጡ በፊት፣ ኢሣት በምጣኔ ኃብት የቀረቡ መጣጥፎችን ባለማስተናገዱ፣ የተጎዳው የሃገራችን ህዝብና ምሁራን ሲሆኑ አበበ ገላውና ሃብታሙ አያሌው እጅ የሚገኘው መፅኃፍት ጥናታዊ ሥራ  ዛሬ  በተለያዩ ድረ-ገፆች ተለቀው በመነበብ ላይ ሲሆኑ፣ የጋዜጠኝነት ሥራችሁን ባለመወጣታችሁ ገንቢ ሂስ ለማቅረብ በማሰብ ከዓይናችሁ ጉድፍ ለማውጣት የታለመ ነው፡፡ በጋዜጠኝነት ሥራና ሙያዊ ሥነ-ምግባር፣  ግልፅነት፣ ታማኝነትና ተጠያቂነት ዋነኛዎቹ መገለጫዎች ናቸው እንላለን፡፡ ኢሣት መረጃ ከውስጥ ላበረከቱ ጸሃፊዎች ምስጋና ቢቀር እንደ ነፃ ሚዲያ የማቅረብና የመዘገብ ሥራ ልክ እንደ የኢትዩጵያ የመረጃና መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (INSA) ከሃገር ውስጥ የተላከ መረጃ ኢሣት ያለ በቂና ሚዛናዊነት በጊዜው አለመዘገቡ በጋዜጠኛ አበበ ገላው የቀረበው ትንተና አሳማኝ ሆኖ አላገኘንውም፡፡ ከሰባት አመታት በፊት በኢሣት ጋዜጠኞች መረጃው ይቅረብ አይቅረብ የነበረ ክርክር ይፋ ቢደረግ ታላቅነታችሁን ያበስርላችኋል እንላለን፡፡ የኢት-ኢኮኖሚ/ /ET- ECONOMY ሥራዎችን በኢሣት በፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው እና በኢሳት የቀድሞ የሠራዊቱ ድምፅ ስለ ኢፈርትና ሜቴክ በተከታታይ ጹሁፋችን እንደቀረበ ለማመስገን እንወዳለን፡፡  ኢሣት በነዚህ መረጃ አቅራቢዎችን ለምን እንዳላስተናገዱና የመረጃ ምንጩ አስተማማኝ ይሁን አይሁን የሚለው የማምለጫ አብዶ መለኪያው  ምን እንደሆነ በግልፅ ካልተቀመጠ  ከሃገር ቤት መረጃ የማግኘት ገመዳችሁ ይቆረጣል እንላለን፡፡ ኢሣት አገርቤት ገብቶል፡፡

  • የኢትዮጵያ ሣተላይት ቴሌቪዥን ፣የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ወዘተ ህዝባዊ መገናኛ ብዙኃን በመሆን ላበረከቱት አስተዋፆኦ እያመሰገንን፣ አገር ውስጥ ከገባችሁ በኋላ እንደ ማንኛውም የሚዲያ መገኛኛ ብዙኃን የግሉ ዘርፍ፣ በግል፣ ቡድን በአክሲዬን የቴሌቪዝን/ የሬዲዬ ጣቢያ ሆናችሁ መቀጠል እንጂ ህዝብን ገንዘብ አምጡ፣ ነጋ ጠባ መኒ! መኒ! አምጡ ማለት ህዝቡ ለተፈናቃዬች ይርዳ ለእናንተ አስቡበት እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ የፌዴራልና፣ የክልል፣ የመንግሥትና የግል የመገናኛ ብዙሃን በምን መልክ መቀጠል ይገባቸዋል ለሚለው ፅንሰ ሃሳብ በተለያዩ ጊዜት ጥናታዊ ዘገባ በማቅረብ በማስረጃ ዘግበናል፡፡ ለዛሬ አጥኝዎች ግብዓት ይሆናል ብለን መጣጥፎቹን ዳግም እናቀርባለን፡፡     
  • በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን እጣ ፈንታ የክልል ዘር ተኮር መንግስቶች ህወኃት/ ብአዴን/ ኦህዴድ/ ደኢህዴን የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ በክልላቸው ውስጥ ስውር ሥራዎች በማደራጀትና አንዱ አንዱን በመክሰስ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻውን አጦጡፈውታል፡፡ የየክልሎቹ መገናኛ ብዙኃን የቴሌቪዝንና ሬዲዬ ሥርጭት የጦርነት መጎሰሚያ ሆነዋል፡፡ህወሓት፣ ኦህዴድ፣ ብአዴንና ደኢህዴድ ባለፈው ጊዜ በየግላቸው አንዳንድ መግለጫዎችን አውጥተዋል። እንዲሁም በደቡብ ክልል የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የጉራጌ ወዘተ የክልል ጥያቄ በአጠቃላይ በመላ ሃገሪቱ ያስነሳው የድንበርና የወሰን ግጭትና ጦርነት እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ጥያቄ ወዘተ በፅንፈኛ ሚዲያ እየሞቀ እየፈላ መምጣቱ አይቀርም እንላለን፡፡
  • በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን፣ የማንነት ጥያቄ ሠለባዎች፣ ባለፉት 27 አመታት ወያኔ ባጸደቀው በዘርና ልሳን በተከለለ ፌዴራላዊ ክልላዊ አስተዳደር የተነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁም ስቅሉን በማየት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም የተነሳ በወያኔ ከፋፍለህ ግዛው የአባላህኝ ዘመን ከክልላቸችን ውጡ፣ ቅስቀሳ የተነሳ የሃገራችን ዜጎች በሁሉም የሃገሪቱ ግዛት ውስጥ ተዘዋውሮ የመስራት መብቱንና ክብሩን አጥቶል፡፡ በዚህም የተነሳ ከአንድ ሚሊዩን 500 ሽህ ህዝብ በላይ የኦሮሞና ሱማሌ ህዝብ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በጉጂ ኦሮሞዎችና በሲዳማ ጊዴኦ የዘር ግጭት የተፈናቀሉ ከ750 ሽህ እስከ አንድ ሚሊዮን ወገኞቻችን ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በሲዳማና ወላይታ በተከሰተው የዘር ግጭት ከ20 እስከ 30 ሽህ ህዝብ ሲፈናቀል በተመሳሳይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ  8510 የትግራይ ተወላጆች የዘር ግጭትን በመፍራት ወደ ትግራይ ክልል ተመልሰዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ የትግራይ ርዕስ መስተዳደር ዶክተር ደብረፂዬን በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ተደረገ በማለት ከመቐለ በማቅራራት ላይ ይገኛሉ፡፡ እናቱ የማተችበትም፣ ወንዝ ውሃ ለመቅዳት የወረደችበትም ህፃን እኩል ያለቅሳል እንደሚባለው ዓይነት የኢትዮጵያን ህዝብ በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ፡፡     
  • በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ‹‹በፈቃድ ከመጣ ባርነት የበለጠ የሚያሳፍር የለም!!!›› (‘No slavery is more disgraceful than that which is self-imposed’Seneca) ይሄ አባባል ለእኛ ‹‹በፈቃድ ከመጣ የልሂቃን ባርነት የበለጠ የሚያሳፍር የለም!!!›› ቢባል ያስኬዳል፡፡ የኢትዮጵያ ልሂቃን ከባህር ማዶ የቀሰሙትን ትምህርት ከሃገራቸው ተጨባች ሁኔታ ጋር ባለማዛመድ እንዳለ በመቅዳትና በመተርጎም ከስልጣኔ ማማና ከምሁራን ጎራ ቢደመሩም ለሃገራቸው የፖለቲካ፣ ምጣኔ ኃብትና ምህበራዊ ጉዳዮች የሰጡት መፍትሄ አጠያያቂ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በቀኃሥ፣ በደርግና በኢህአዴግ ዘመነ መንግሥት ህገ- መንግሥት ከተለያዩ ሃገራት የተገለበጠ ህገመንግሥት፣ የፖለቲካ ርዕዮት፣ የኢኮኖሚ እቅድ፣ የማህበራዊ ጉዳይ ችግር አፈታት በአጠቃላይ የመንግሥታዊ አስተዳደርና ሥርዓተ መንግሥታዊ መዋቅሮች የተኮረጁና በህዝብ ላይ በግድ የተጫኑ ለመሆናቸው ሾተላይ ሰላይ መሆን አይጠበቅብንም፡፡ በወያኔ ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ  የዘር ፌዴራሊዝም ፖለቲካ ከተጫነብን 27 አመታት ተቆጠረ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ህዝቡን በልሳን ከፋፍሎ ለሞት፣ እስራት፣ ስደትና መፈናቀል ዳረገው፡፡ በኦሮሞና ሱማሌ፣ በአማራና ትግራይ፣ በሲዳማና ወላይታ፣ ወዘተ በተከሰተው የዘር ግጭት የሃገር ውስጥ ተፈናቃዬች ቁጥር ከሁለት እስከ ሦስት ሚሊዮን አሻቅቦል፡፡ የህወሃት አመራር በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ተካሄደበት፣ በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተፈፀመብን  ‹ኢንተር ሃሞይ!› ብለው እንደጮሁት ዛሬም ድራማ እየሰሩ ናቸው ታዲያ እነዚህን ቦዘኔ ሌባ የወያኔ አመራሮች ‹‹በፈቃድ ከመጣ የወያኔ አመራር ባርነት የበለጠ የሚያሳፍር የለም!!!›› ልንላቸው ይገባል፡፡ ማንም ሰው ከህግ በላይ መሆን ስለማይችል በወልቃይት በራያ ህዝብ ላይ መቐለ የመሸገው ፀረ-ዴሞክራቲክ ኃይል ሚፈፅመው ወንጀል ይዋለወ ይደር እንጂ ለፍርድ መቅረብ አይቀርም እንላለን፡፡ ህወሓት የፈፀመውን ወንጀል፣ አዲስ ወንጀል በማስፈፀም ሊያረሳሳ የሚሞክረው  ከንቱ ውዳሴ እንጂ በዚህ በዲጂታል ዘመን የተመዘገበ ማስረጃ አንድ ቀን ፀሃይ ዮሞቀዋል እንላለን፡፡  የ1998ዓ/ም ምርጫ ያጣሩት አንበሶች፣ ዛሬም በዶክተር አብይ መንግሥት ተቀባይነት አጥተው ከሃገር ያለመግባታቸው ሚሥጢር ረቂቅ ነው፡፡   ለዳኛ ፍሬህይወትና ለዳኛ ወልደሚካኤል ዘብ እንደቆሙልን ዘብ ልንቆምላቸው ይገባል እንላለን፡፡

‹‹ከጥንት ጀምሮ እኛ የምናውቀው፣

 ሲነድ ሲቃጠል የሚስቅ እሳት ነው፡፡ ባለቅኔ ኃይሉ ገብረህይወት /ገሞራው

  • PART I – የኢትዩጵያ ገበሬዎች ትራክተር ከሚገዛ፣ ክላሸን ኮቨ በመቶ ሽህ ብር ይገዛል!!! እንደ መግቢያ
  • PART II- ኢትዩ-ቴሌኮምና ቻይናዊያን ሾተላይ ሰላዬች! (ክፍል ሁለት) ፊርማው የማን ይሆን!!! የኢትዩጵያ የመረጃና መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ Information Network Security Agency (INSA)  ቪላድሜር ፑቲንም ኬጂቢ ነበሩ!!! በጥሞና አንብቡት!!! PDF
  • PART III-  Human Rights Watch “ They Know Everything we do” telecom and internet surveillance in Ethiopia PDF

‹‹የህወሓት/ ኦህዴድ የኢንሣ ጡሩምባ፣ መሬት ቀዶ ገባ!!!››

የኢንሣ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!!

የህወሓት/ኢህአዴግ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!!

ጅብ ከሚበላህ ጅቡን ብላውና ተቀደስ!!!