ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው ቅዱስ መሪ ቃል፣ አፍሮ አይገባ ( በ/ት ፂዮን ዘማርያም )

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

                                   1-የትግራይ ክልል፣     2- የአማራ ክልል፣     3-የኦሮሚያ ክልል፣     4- ደቡብ ክልል፣      “ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው ቅዱስ መሪ ቃል፣ አፍሮ አይገባ ለቡዳ ዘረኛ ፖለቲከኞች መድኃኒት ነው”

ኢትዮጵያዊያን የጦርነት፣ የርሃብ፣ የበሽታ፣ የዘመነ መሳፍንት ዘመንን የተሸገሩበት ‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!!! ቅዱስ መሪ ቃል ነው! የኢህአዴግ ዘር ተኮር ክልላዊ መንግሥቶችን ለመጣል፣ ከጥንት ከጠዋቱ፣ ከትውልድ ትውልድ ከአባቶች የተላለፈውን ልዩነት በብዙኃነት   የሚሰብከውን ‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!!!›› ቅዱስ መሪ ቃል ሥር የተሰባሰብን ህዝብ መሆናችንን እንረዳ፡፡ ‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!!! ቅዱስ መሪ ቃል፣ አፍሮ አይገባ!!! ›› ቅዱስ መሪ ቃል የ3 ሚሊዮን አመታት ታሪክ አለው፡፡ ‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!!! ቅዱስ መሪ ቃል፣ ለቡዳ ዘረኛ ፖለቲከኞች መድኃኒት ነው!!!›› በሚል የተደራጁ  የልማት ድርጅቶችን፣ በከተማና በገጠር  ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ማህበራት አስፈላጊ ናቸው እንላለን፡፡ ‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!›› የሚል የልማት ድርጅቶች በመመስረት ህብረተሰቡን ያለ አንዳች ልዩነት በዘር፣ በኃይማኖት፣ በቆንቆ፣ በክልል ወዘተ ሳይለያዮ ሃገርና ትውልድን ከዘመን ወደ ዘመን  ያስተላለፈ ቅዱስ መሪ ቃል ስር መሰባሰብና መደራጀት አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ ከተሞች ልዩ ልዩ በህዝብ የተመረጡ የልማት ድርጅቶች በታዋቂ ሰዎች በማቆቆም ለምሳሌ  ‹‹ አንድ ብር ለአንድ ወገን ›› የረድኤት ድርጅት ማህበራዊ ችግሮችን በተግባር ለመቅረፍ በየከተሞቹ ውስጥ አንድ ብር ለአንድ ወገን ከዳቦ ቤቶች ደጃፍ፣ከመስጊድ ና ቤተስኪያን ደጃፍ በማሰባሰብ ‹‹ዳቦ ለተራበው!››  ወገን በመመፅወት  የወገን ጥሪን በፍቅር መግለፅ የታማኝ የቤተ-እምነት ወጣቶች ነፃ የሥራ ማህበራዊ አገልግሎት ነው፡፡ ለጥቆም ‹‹ ኃይማኖት የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው››ማህበራቱ ሲጠናከሩ በህብረት የጤና፣ የትምህርት ቤት፣ የመንገድ፣ የመብራት፣ የውኃ፣ የስልክ፣ የቤተ-መፅሃፍት፣ የቴሌቪዝንና ሬዲዬ ማዳረስ፣ የጫማ፣ ሣሙና፣ ሞዴስ የማዳረስ፣ የእርሳስና ደብተር፣ ወዘተ ለህብረተሰቡ የሚያዳርሱ አንድ ሽህ አንድ የልማት ማህበራት በታዋቂ ሰዎች ማደራጀት ያስፈልጋል እንላለን፡፡ ‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!!! ቅዱስ መሪ ቃል፣ አፍሮ አይገባ!!! ›› የአባቶቻችን ቅዱስ መሪ ቃል ጥላቻን በፍቅር፣ ልዩነትን በአንድነት፣ ድንቁርናን በእውቀት የሚገልጥ ከአጋንት ፖለቲከኞች የሚሰውር ቅዱስ ቃልን እንጠቀምበት እንላለን፡፡

‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!›› መሪ ቃል በየከተሞቹ እስቲከር በመለጠፍ፣ በማውለብለብ፣ በማሰር አዲስ የከተማ ንቅናቄ ማስፋፋት ወደ ፍቅር መንገድ ያስጉዘናል፡፡ ‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!›› የእናቶች እዱስ መሪ ቃል  በአዲስ አበባ፣ ከ4 እስከ 5 ሚሊዮን የሚገምቱ ነዋሪዎች በየክፍለ ከተማቸው ህብረ ብሄር የልማት ማህበር ማቆቆም ፡፡ በተመሳሳይ በሃገሪቱ ውስጥ ከመቶ ሽህ በላይ ህዝብ በላይ ያላቸው ከተሞች ህብረ ብሄር ዜጎች እንደሚኖሩባቸው ለማንም ግልፅ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ ጎንደር (323,900)፣ መቀሌ (323,700)፣ ባህር ዳር (187,900)፣ ጂማ (177,900)፣ ጂግጂጋ (159,300)፣ ሻሸመኔ (147,800)፣ ሶዶ (153,322)፣ ብሸፍቱ/ ደብረዘይት (147,100)፣ አርባ ምንጭ (142,900)፣ ሶዶ (145,100)፣ ሆሳዕና (133,800)፣ ሀረር/ሀረሪ (129,000)፣ ዲላ (112,900፣ ነቀምት (110,640)፣ ደብረ ብርሃን (102,100)፣ ደብረ ማርቆስ (103,263)፣ አሰላ (103,522)፣ ከተሞች ውስጥ የሚጀመረው ‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!›› የልማት ማህበር የህብረተሰቡን ችግር የመፍታት የመንገድ፣ የትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል፣ የስልክ፣ የመኖሪያ ቤት (የሽንት ቤት ችግር)፣ የህጻናት መዋያ፣ የስፖርት ሜዳዎች፣ ቤተመጽሃፍት ማደራጀት፣ ወዘተ ተቆማትን በህብረ ብሄርነት በመገንባት በከተሞች ውስጥ የሚኖሩ የኢትዮጵያዊያን ዜጎች በምርጫ ራሳቸውን በእራሳቸው የማስተዳደር መብት ተጠቅመው የከተማ የልማት ማህበራት በመደራጀት የኢህአዴግ ዘር ተኮር ፓርቲዎችና ክልላዊ መንግሥቶችን መገርሰስ ቀጣዮ የወጣቶች ምዕራፍ ሁለት ትግል ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ማስቀጠልና አገር አቀፍ ‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!›› የልማት ማሕበራት ህብረት መመሥረት ያስፈልጋል እንላለን፡፡ ለኢህአዴግ ዘረኛ የልማት ማህበራት ድጋፍና እርዳታ አለማድረግና ህዝብ የሚፈልገውን ልማት በጋራ የመሥራት የቆየ ባህል ማጠናከር አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ ‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!›› መሪቃል አባቶቻችን ለዘመናት የመከሩበት  ለዘረኞች፣ ለጉጠኞች፣ ለጎሰኞች፣ ለትምህከተኞችና ለጠባብ ፖለቲከኞች ፍቱን የቡዳ መድኃኒት ነው እንላለን፡፡

የህወሓት/ ኢህአዴግ ዘር ተኮር የፖለቲካ ንግድ ድርጅቶችና ክልላዊ መንግሥቶች ለመጣል፣ በየክልሉ ‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!›› መሪ ቃል የልማት ድርጅቶችን መደራጀት ፍህታወና ወቅታዊ አጀንዳ ነው እንላለን፡፡ ህዝቡ ላለፈው 27 አመታት በክልላዊ መንግስት ተጠቃሚ አልሆነም፡፡ ተጠቃሚዎቹ የክልሎቹ ርዕሰ ከተሞች ጠሆኑት  መቐለ፣ ባህርዳር፣ አዳማ፣ ሃዋሳ ከተማዎች ባቻ ናቸው፡፡ ሰፊው ህዝብ በእነዚህ ከተሞች እየሄደ መገበር እንዳስመረረው ጥናቶች በመረጃ ዘግበዋል፡፡ ክልላዊ አስተዳደሮች በዘር መታወቂያ ስም በትግራይ በአማራ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ክልል ያልሠለጠነና  ያልዘመነ አስተዳደር በማደራጀት የክልሎቹ ህዝቡ መቐለ፣ ባህርዳር፣ አዳማ፣ ሃዋሳ ድረስ እየተጎዘ አስተዳደራዊ ጥያቄ፣ ኢንቨስትመንት ፍቃድ፣ ፍትህ ዳኝነት፣ ወዘተ ጥያቄዎች ለማቅረብ ለብዙ አመታት የተሰቃየበት ኢዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ስለተጫነበት ነው፡፡ ህዝብ ባልመረጣቸው የፖለቲካ ካድሬዎች ሲገዛ ቆይቶል፣ ቀጣዩ የህዝብ አመፅና እንቢተኝነት ለፍህታዊ የልማት ሥርጭት፣ ለተገቢው ቦታ እውቀት ያላቸው ሙያተኞች መመደቡ፣ የወንዜ ልጅነት ዘር ተኮር ቡድን መቀሌነት፣ ጎጃሜነት፣ ወለጌነት፣ ሲዳማነት ከእንግዴህ በዚህ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን የህወሓት/ ኢህአዴግ የፖለቲካ ካድሬዎች ቆማር ጨዋታና የሥልጣን ጥማት ከእንግዲህ አይሠራም እንላለን፡፡ ቀጥሎም የመለስ ኢህአዴግ እንደ መንግሥቱ ኢሠፓ ከኢትዮጵያ ምድር ይወገዳል እንላለን፡፡ የክልል መንግሥቶች ፍህታዊ የፖለቲካ አሥተዳደር፣ የምጣኔ ኃብት ፍህታዊ ድርሻ እና የማህበራዊ ልማት አድሎዊ ያልሆነ ሥርጭት ባለፉት 28 አመታት ተግባራዊ አልነበሩም፡፡ የኢህአዴግ ፖለቲካ ካድሬዎች በክልላዊ ዘር ተኮር ሥም የራሳቸውን ኃብትና ንብረት ሲዘርፉና ሲያሸሹ ተስተውለዋል፡፡በክልሎቹ ህዝብ ሥም የተቆቆሙት የፖለቲካ ንግድ ድርጅቶችና የልማት ማህበራት፣ የፋይናንስ ባንክና የማይክሮ ፋይናንስ ተቆማቶች እንደተዘረፉ የኢፈርት፣ ሜቴክ፣ ጥረት፣ ዲንሾና ወንዶ የፖለቲካ ካድሬዎችና ቤተሰቦች ንብረት ሆነው እንደተዘረፉ በአደባባይ ለህዝብ በማስረጃ ቀርቦል፡፡ መፍትሄውም እነዚህ ድርጅቶች ከኢህአዴግ ፓርቲዎች ንብረትነት አላቆ ለግሉ ዘርፍ ባለኃብቶችና ለህዝብ በአክሲዬን  መሸጥ አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው፡፡         

በኢትዮጵያ የክልላዊ መንግስቶች፣ የዘር አደረጃጀት ለህዝቡ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳዬች ችግር መፍታት ባለመቻላቸው፣ የፖለቲካ ሥልጣን ጥያቄ፣ የኢኮኖሚ የዶቦ ድርሻ ጥያቄና የሥራ አጥነት ችግር መፍታት አልቻሉም፡፡ በኢትዮጵያ የክልላዊ መንግስቶች፣ ኢፍህታዊ የፖለቲካ አሰራር በተለይ በሰው ኃይል ልማት በአውራጃዊነትና በወንዜ ልጅነት ላይ ያጠነጠነ እውቀትንና ችሎታን ያላገናዘበ የፖለቲካ ካድሮዎች የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የነበሩ የሚኒስትርነት፣ የዲፕሎማትነትና የጀነራል መኮንንነት ማዕረግ ያለእውቀት በመስራት ሃገሪቱን ለውድቀት ዳርጎታል፡፡  በኢኮኖሚም ዘርፍ ፍህታዊ ያልሆነ የኃብት ክፍፍል በክልላዊ መንግሥቶች ውስጥ የኢህአዴግ የፖለቲካ ድርጅቶች የህወሓት/ኢፈርት፣ የብአዴን ጥረት፣ የኦህዴድ/ዲንሾ እንዲሁም የደኢህዴን ወንዶ የልማት ግንባታ ማጠንጠኛቸው በወንዜ ልጅነትና አድሎዊ አሰራር ላይ ያተኮሩ ለመሆኑ ምስክር የሚሆነው ህዝብ ሊጠየቅ ይገባል፡፡ እንዲሁም በማህበራዊ የጤና፣ የትምህርት ቤት፣ የመንገድ፣ የመብራት፣ የውኃ፣ የስልክ ወዘተ ፍህታዊ የልማት ሽፋን ድርሻ አለመኖሩ ህዝባዊ ጥያቄ ተበራክቶ የክልላዊ መንግሥቶች ወደ አውራጃዊነት መንግሥትነት መፈረካከስ ይከተላል፡፡ በኢትዮጵያ የክልላዊ መንግስቶች፣ የዘር አደረጃጀት ለህዝቡ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳዬች ችግር መፍታት ባለመቻላቸው፣ ቀጣዩ ህዝባዊ ትግልና አመፅ ለክልላዊ መንግሥት ባለመገበር ‹‹ ኃይማኖት የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው›› በሚል መሪ ቃል የልማት ማህበርነት መደራጀት ይከሰታል፣‹‹ ኃይማኖት የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው›› የአባቶች ብሂል መሠረትም፡-

{1} በትግራይ ክልል ውስጥ፣ መቐለ፣ ሽሬ፣ አዲግራት፣ አክሱም፣ እንድርታ ወዘተ አውራጃዊ የልማት ማህበርነት ህብረ ብሄራዊ ሆኖ ይደራጃል፡፡

{2} በአማራ ክልል ውስጥ፣ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎና በሸዋ አውራጃዊ የልማት ማህበርነት ህብረ ብሄራዊ ሆኖ ይደራጃል፡፡

{3} በኦሮሚያ ክልል ውስጥ፣ ወለጋ፣ ጂማ፣ ቦረና፣ ሃረር፣ ባሌ፣ አርሲ ወዘተ የልማት ማህበርነት ህብረ ብሄራዊ ሆኖ መደራጀት ይጀመራል፡፡ 

{4} በደቡብ ክልል ውስጥ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ሃዲያ፣ ጌዲዬ፣ ጉራጌ፣ከፋ፣ጋሞ፣ ወዘተ የልማት ማህበርነት ህብረ ብሄራዊ ሆኖ ይደራጃል፡፡

{5} በአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሀረሪ ክልሎች ውስጥ፣አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ ወዘተ ህብረ ብሄራዊ ሆኖ ‹‹ ኃይማኖት የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው›› መሪ ቃል ለልማት መደራጀት ይጀመራል፡፡ በኢትዮጵያ የክልላዊ መንግስቶች፣ የዘር አደረጃጀት ለህዝቡ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳዬች ችግር መፍታት ባለመቻላቸው፣  ቀስ በቀስ ኃይላቸው እየቀዘቀዘ፣ ዘር ተኮር የፖለቲካ አገዛዛቸው ሽሮ የማያበላና በእውቀት ላይ ያልተመሠረተ የፖለቲካ ካድሬ ሥልጣን እያከተመ ህብረ ብሄራዊ ሆኖ በእውቀትና ብቃት ላይ ያተኮረ በሰው ኃይል ይተካል፣ የመንግሥት መር ኢኮኖሚ እየከሰመ በግል ዘርፍ ኢኮኖሚ እየለመለመ ይመጣል፡፡ እንዲሁም የግሉ ዘርፍ በማህበራዊ ጉዳይ በጤና፣ በትምህርት ቤት፣ በመንገድ፣ በመብራት፣ በውኃ፣ በስልክ ወዘተ ፍህታዊ የልማት ሽፋን ድርሻ በኃላፊነትና ተጠያቂነት መሳተፍ  በኢትዮጵያ የክልላዊ መንግስቶች፣ የዘር አደረጃጀት ህዝቡን ‹እንጀራ የማያበላ› የፖለቲካ ነቀርሳ በሽታ ለአንዴና ለሁሌ በሂደት እየከስመ ይሄዳል እንላለን፡፡ በመላ ኢትዮጵያ ውስጥ ቤተክርስቲያንና መስጊድ ሲገነባ ክርስቲያኑም ሙስሌሙም በህብረትና በፍቅር ገንዘብ አዋጥቶ እንደሚገነባ ሁሉ በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሀረሪ የሚገነቡ ልማታዊ ሥራዎች በመላ ኢትዮጵያ ህዝብ የሚገነቡ ሥራዎች ይሆናሉ፡፡  ኢህአዴግ ፓርቲዎች የፖለቲካ ንግድ ድርጅቶች ዘር ተኮር ክልላዊ መንግሥቶች ለመጣል፣ ‹‹ ኃይማኖት የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው›› የልማት ማህበር መደራጀት ቀጣዩ የህዝብ ጥያቄ በማድረግ በምሁራን ተሳትፎ መጠናከር አለበት እንላለን፡፡ በመላ ሃገሪቱ ‹‹ ኃይማኖት የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው›› ብሄራዊ የልማት ድርጅቶች ህብረት ይፈጠራል፡፡ ‹‹ ኃይማኖት የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው›› ብሄራዊ የልማት ድርጅቶች ህብረት ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት ተደራጅተዉ በምርጫ ተወዳዳሪ ይሆናሉ፡፡ ‹‹ ኃይማኖት የግል ነው፣ ሃገር የጋራ ነው›› አዲሱ ህዝባዊ አጀንዳችን ይዘን ከዶክተር አብይ አህመድ የመደመር መሪቃል ጋር እናዋህደው፡፡

ለአለፉት 28 ዓመታት የህወሓት፣ የብአዴን፣ የኦህዴድና የደኢህዴን/ኢህአዴግ  የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ክልላዊ መንግሥት፣ መንግሥት መር የኢኮኖሚ ጣልቃ ገብነት የተነሳ 30  ቢሊዮን ዶላር በህዝብና ልማት ሥም ተዘርፎ ከአገር ኮብልሎል፣ እነደ ሜቴክ የተጀመሩ አንድ ሽህ አንድ መቶ ፕሮጀክቶች በሙስና ሌብነት ሳይጠናቀቁ ተመዝብረዋል፡፡ በ21ኛው ክፍለ ዘመን፣ የኢትዮጵያ ህዝብ፣  ትምህርት ቤት፣ መንገድ፣ መብራት፣ ውኃ፣ ስልክ፣ የመኖሪያ ቤት ሽንት ቤት  አገልግሎቶችን ህብረተሰቡ አላገኘም፡፡ ጭራቁ ህወሓት/ ኢህአዴግ በልማታዊ መንግስት ሥም፣ በአብዬታዊ መንግሥት ሥም፣ የህዝቡን ኃብትና ንብረት የዘረፈ መንግሥት በህግ ሊጠየቅ ይገባዋል እንላለን፡፡ በኢትዮጵያ ህዝብ የተፈፀመ የስብዓዊ መብት ጥሰት በኢሠመጉ በዝርዝር ቀርቦ ተጠያቂዎች ለፍርድ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ዛሬም በየክልሎቹ የተፈናቀሉ ህዝቦች ወደ ቀያቸው በአፋጣኝ እንዲመለሱና መከላከያ ሠራዊቱ ሰላም የማስጠበቅ ኃላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል እንላለን፡፡   

{1}የህወሓት ኢፈርት የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች፣ መሶቦ ሲሚንቶ፣አልመዳ፣ሸባ፣ ትራንስ ኢትዮጵያ፣ መስፍን ኢንጅነሪንግ፣ሱር ኮንስትራክሽን፣  ወዘተ ለኢትዮጵያ የግል ዘርፍ በአክሲዮን በመሸጥ ኃብትና ንብረቱን የመላ ሃገሪቱ ዜጎች ሃብት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

{2}የብአዴን ጥረት የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች፣ለኢትዮጵያ የግል ዘርፍ በአክሲዮን በመሸጥ ኃብትና ንብረቱን የመላ ሃገሪቱ ዜጎች ሃብት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

{3}የኦህዴድ ዲንሾ የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች፣ለኢትዮጵያ የግል ዘርፍ በአክሲዮን በመሸጥ ኃብትና ንብረቱን የመላ ሃገሪቱ ዜጎች ሃብት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

{4}የደኢህዴን ወንዶ የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች፣ለኢትዮጵያ የግል ዘርፍ በአክሲዮን በመሸጥ ኃብትና ንብረቱን የመላ ሃገሪቱ ዜጎች ሃብት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

{5}የኢህአዴግ የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች፣ የግል ባንኮችና ኢንሹራንሶች ለኢትዮጵያ የግል ዘርፍ በአክሲዮን በመሸጥ ኃብትና ንብረቱን የመላ ሃገሪቱ ዜጎች ሃብት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

{6} የኢህአዴግ የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች፣ የማይክሮ ፋይናንስ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ የግል ዘርፍ በአክሲዮን በመሸጥ ኃብትና ንብረቱን የመላ ሃገሪቱ ዜጎች ሃብት ማድረግ ያስፈልጋል እንላለን፡፡

ህወሓት /ኢህአዴግ መንግሥት የፖለቲካ የንግድ ድርጅቶች ለአለፉት 28 አመታት ህወሓት ኢፈርት፣ብአዴን ጥረት፣ ኦህዴድ ዲንሾ፣ አና ደኢህዴን ወንዶ በሚል ክልላዊ መንግሥት ተኮር የንግድ ድርጅቶች በማቆቆም የሀገሪቱንና የክልሉን ሃብትና ንብረት ሲዘርፉ ቆይተዋል እንላለን፡፡ የዶክተር አብይ አህመድ መንግስት እንደ ህወሓት /ኢህአዴግ መንግሥት የኢፈርት የፖለቲካ የንግድ ድርጅቶች ዓይነት

(ሀ) ኦህዴድ/ ኢህአዴግ ይሄንንው ፋሽን በመከተል በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት  ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት›› እነዲሁም (ለ) በአማራ ክልላዊ መንግሥት ‹‹ዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት››፣(ሐ)በደቡብ ክልል የወንዶ  የፖለቲካ የንግድ ድርጅቶች ሥራ በማስቀጠል የክልል መንግሥት መር ኢኮኖሚ በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡

{ሀ} የኦሮሚያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ዲንሾ የፓርቲ የንግድ ድርጅት ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት››

በዶክተር አብይ አስተዳደር ዘመን የወያኔ በክልል መንግሥታትና ተቆማት ላይ የፖለቲካ ተፅዕኖ ማሳደር ብቃቱ በመሸርሸር ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህም ማስረጃ በፊዴራል መንግሥት ለኢንቨስተሮች ሰጥቶ የነበረውን የተለያዩ ማዕድናት ማውጫዎች በኦሮሚያ፣በጋምቤል ክልላዊ መንግሥት መወረስ በናሙናነት ይጠቀሳል፡፡‹‹የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ለኢንቨስተሮች ሰጥቶ የነበረውን የተለያዩ ማዕድናት ማውጫዎች መንጠቅ ጀመረ፡፡ የክልሉ መንግሥት የሚነጥቃቸውን የማዕድናት ማውጫዎች ለተደራጁ ሥራ አጥ ወጣቶች ለመስጠት አዲስ ዕቅድ አውጥቶ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ቀይ አሸዋ፣ አሸዋ፣ ካባ ድንጋይ፣ፑሚስና ታንታለም ማውጫ ሥፍራዎችን የስራ አጥነት መቅረፍያ ለማድረግ ታስባFል፡፡ አሁን የተጀመረው በምሥራቅ ሸዋ ዞን ሲሆን በዚህ ሥፍራ የሚገኙ የማዕድናት ማውጫዎችን በመውሰድ ለ300 ሽህ ወጣቶች ሥራ ለመፍጠር ታቅዶል፡፡ ወጣቶቹ ያመረቶቸውን ማዕድናት ለኢንቨስተሮቹ ይሸጣሉ፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በክልሉ የሚገኙ ኢንቨስተሮች ያለሙትን የማእድን መሬት በመንጠቅ ለወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር እቅድ ነድፎ ተግባራዊ ማድረግ ጀምሮል፡፡ በአዲስአባባ ዙሪ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ በዱኮምና በገላን ከተሞች የሚገኙ 42 ጠጠር አምራቶች፣በመንጠቅ ለወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠሩን አውጆ ነበር፡፡ በምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ለሲሚንቶ ማምረቻ ዋነኛ ጥሬ ዕቃ የሆነውን ፑሚስ የሚያመርቱት ግዙፎቹ ኩባንያዎች ደርባን ሚድሮክ ሲሚንቶ፣ዳንጎቴ ሲሚንቶና፣ሙገር ሲሚንቶ የፑሚስ ማዕድናት ማውጫቸው በመነጠቁ ማምረት ባለመቻላቸው የምርት መስተጎጎል ተከስቶ ነበር፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ማዕድናት ማውጫ ሥፍራዎች የመውረስ ስትራቴጂ ሌሎች የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ባሉባቸው ክልሎች ተግባራዊ የማይደረግ ከሆነ በሃገሪቱ የገበያ ውድድር መዛባት ፈጥሮ ነበር፡፡ ይህ ስትራቴጂ በፌዴራል ደረጃ ካልተተገበረ በሃገሪቱ የሲሚንቶ ገበያ ዋጋንና ውድድሩንም ፍታሀዊ አያደርገውም፡፡ ጥራት ያለው ማቴሪያል ከማምረት አንፃርም ሊመዘን ይገባዋል፡፡ ወያኔ እነዚህን የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ከገበያ ተወዳዳሪነት በማስወጣት መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካን ምርት በመላ ሃገሪቱ ለመሸጥ የነደፈው ሴራ ካልሆነ ኢንቨስተሮች ንብረትንና ኃብትን መውረስ በአንድ ክልል ሊተገበር አይችልም፡፡ ከሆነም በፊዴራል መንግሥት ደረጃ በሃገር አቀፍ ደረጃ የማዕድናት ማውጫዎችን መውረስ አለበት በማለት ኢንቨስተሮች ተቃውመው ነበር፡፡ የኦሮሚያ ክልል የተንሰራፋውን ሥራ አጥነት ለመቅረፍ በዚህ በጀት ዓመት የ6.6 ቢሊዩን ብር በጀት በመመደብ፣ 1.2 ሚሊዩን ሥራ አጥ ወጣቶችን ሥራ ለማስያዝ ዕቅድ አውጥቶ ነበር፡፡›› ለ1.2 ሚሊዩን ሥራ አጥ ወጣቶችን የነፍስ ወከፍ ብድር ምጣኔ 5500 ብር እንደሆነ ማስላት ይቻላል፡፡ የአዲሱ የኦሮሚያ ካቢኔ ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት››በሚል መርህ በኦሮሚያ  የኢኮኖሚ አብዩት በፍጥነት ወደ ተግባር ለማስገባት፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና የኦሮሞ ባለሃብቶች ጥምረት ምክር ቤት መሥርቶል፡፡ ይህ ተግባራቸው ከወያኔ ፊዴራል መንግሥት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጋር ይጋጫል፡፡

የኦሮሚያ ኢኮኖሚ አብዬት መሠረት ኦዳ ኢንቲግሬትድ ትራንስፖርት አክሲዩን ማህበር/ኩባንያ አጠቃላይ ካፒታሉ በ1.6 ቢሊዩን ብር ሲሆን የክልሉ መንግሥት ለዚህ አክሲዩን ማህበር መመሥረቻ 500 ሚሊዩን ብር የመደበ ሲሆን ቀሪው ከአክሲዩን ሽያጭና ከባንክ ብድር መሆኑ ታውቆል፡፡

ኬኛ ቤቬሬጅ (ኬኛ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ) አክሲዩን ለመመስረት ታቅዶል፡፡ እንዲሁም የኦሮሞ ኮንስትራክሽን አክሲዩን ማህበርና አምቦ ፕመር የተባለ የማዕድንና የግብርና ማኑፋክቸሪንግ አክሲዩን ማህበር እንደሚመሠረት ተገልፆል፡፡ የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ለማ መገርሳ ለኦህዴድ ወጣቶች ሊግ ባደረጉት ንግግር ‹‹በኢኮኖሚ ያልዳበረ ማሕበረሰብ ተላላኪ ነው፡፡ ቁጥር ብቻ ነው፡፡ የትም መድረስ አይችልም፡፡ ገንዘብ ያለው ወይም ሃብት ያለው ፣በኢኮኖሚ ጠንካራ የሆነው ወደ ፈለገበት ይነዳዋል፡፡ ስለዚህ መሥራት ነው ያለብን፡፡ የዓለምን ጥሩ የፖለቲካ ርዕዩት ብናወራ ዋጋ የለውም፡፡ ስለኪራይ ሰብሳቢነት ለ20 ዓመታት ስናወራ ነበር፡፡ ይህ ጎተራችንን የማይሞላ ከሆነ ምን ይጠቅማል; ከአሁን በኃላ መንቃት አለብን፡፡ ያለፈውን ታሪክ እንቀይር፡፡›› የሚል ቀስቃሽ ንግግር አድርገው ነበር፡፡ የኦሮሚያ ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት››የኦዳ ትራንስፖርት ኩባንያ በግማሽ ቀን በተካሄደ የአክሲዩን ሽያጭ 617 ሚሊዩን ብር የሚያወጡ አክሲዩኖች መሸጣቸው ታውቆል፡፡የኦዳ ትራንስፖርት የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት የተሸከርካሪዎች ግዥ በመፈፀም እንደሚጀምርና ከወጣቶች ጋር በጋራ የሚያስተዳድራቸው የነዳጅ ማደያዎችና የነዳጅ ዲፖዎች እንደሚኖሩት ተገልፆል፡፡ እንዲሁም ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት›› የኦህዴድ ዲንሾ የፓርቲ የንግድ ድርጅት የአሰላ የብቅል ፋብሪካ በመግዛት ሥራውን ጀምሮል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ፍህታዊ የኢኮኖሚ ስርጭት የለም፣ አድሎዊ የኢንዱስትሪ ግንባታ፣ አድሎዊ የወንዜ ልጅነት የሥልጣን ክፍፍል፣ ኢፍህታዊ የባጀት ክፍፍል ለአለፉት 27 አመታት ተንሰራፍቶ መቆየቱን በማስረጃ መሞገት እንችላለን፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ ባንዳ የኦህዴድ የፖለቲካ ሰዎች ህዝብ የማያውቅ መስሎቸው በዚህ ኢዴሞክራሲያዊ አሠራራቸው በስመ ኦሮሞነት በመደለል ለመቀጠል እንደማይችሉና ወለጋ፣ ጂማ፣ ቦረና፣ ሃረር፣ ባሌ፣ አርሲ የእራሱን ልማት በማህበር ተደራጅቶ መቀጠሉ አይቀርም እንላለን፡፡ በተዛባ የኦዴፓ ወያኔዊ የሹንባሾች አሥተዳደር የኦሮሞ ህዝብ ወለጋ፣ ጂማ፣ ቦረና፣ ሃረር፣ ባሌ፣ አርሲ እስከ አዳማ ድረስ እየሄደ መገበር የለበትም እንላለን፡፡ ኦዴፓ በህዝብ ተመርጦ የኦሮሞን ርዕሰ መስተዳደር መወሰን፣ መሪውን መምረጥ፣ በክልሉ ኃብትና ንብረት መወሰን፣ የክልሉን በጀት ድልድል የመወሰን፣ የመብራት ፣ ውኃ፣ ትምህርት ቤት፣ ሆስቲታል አገልግሎት ወዘተ ፍህታዊ ድርሻና ሥርጭት መረጃ በግልፅነትና በተጠያቂነት ኦዴፓ በይፋ ለህዝብ አሳውቆና ለውይይት ቀርቦ ልማቱ እንዴት እንደሚዳረስ በእቅድ ተነድፎ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መቀጠል አለበት እንላለን፡፡  የኦህዴድ /ኢህአዴግ መንግሥት ልክ እንደ ህወሓት መንግሥት በዘር ተኮር የሥልጣን ፈረቃ ለናሙናነት ለመጥቀስ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ካሉት 58 የቢሮ ሃላፊዎች ውስጥ 31 ኦሮሞ፣ 11 ደቡብ፣ 9 ትግራዋይ 7 አማራ ናቸው፡፡ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ50 የባንክ ሹማምንቶች ውስጥ 31 የኦህዴድ አባላት መሆናቸው ታውቆ፡፡

{ለ} የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ጥረት የፓርቲ የንግድ ድርጅት ‹‹ዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት›› በብአዴን ጥረት ተጠቃሚ የሆነው የአማራ ህዝብ ማን ነበር!!! ፍህታዊ የልማት ሥርጭት ነበር ወይ!!! ባለፈው 28 አመታት በጥረት የተሰራው በመረጃ ሊቀርብ ይገባል እንላለን፡፡ ዛሬም በብአዴን/ አዴፓ አድሎዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ኢፍታህዊነት ሰፍኖል እንላለን፡፡   

‹‹ዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት››፣ በአማራ ክልል መንግሥት፣ በክልሉ ባሉ 516 የልማት ድርጅቶችና የግል ባለሃብቶች አማካኝነት አባይ ኢንዱስትሪ ልማት አክሲዩን ማሕበር ስር ከ20 በላይ ኩባንያዎች ተቆቁመዋል፡፡ የአማራ ክልል መንግሥት 25 በመቶ የአክሲዩን ድርሻ ሲኖረው፣ የልማት ድርጅቶችና የግል ባለሃብቶች 75 በመቶ የአክሲዩን ድርሻ እንዳላቸው ተገልፆል፡፡ የአክሲዩን  ማሕበሩ 22 ፕሮጀክቶችን መካከል የብረታ ብረት ፋብሪካ፣ የሲሚንቶ፣ የማዳበሪ፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ፋብሪካ፣ የሰፋፊ እርሻ ልማት ሥራዎችና ሌሎች ይገኙበታል፡፡

በባህር ዳር የብረት ብረት ፋብሪካ፣ በምስራቅ ጎጃም የሲሚንቶ ፋብሪካ፣ በደብረብርሃንና ወልዲያ ከተሞች የሚገነቡ የእንጨት ሥራ ፋብሪካዎች እንደሚገነቡ ታቅዶል፡፡ የሦስቱ ፋብሪካዎች የግንባታ ወጪ 10.5 ቢሊዩን ብር ውስጥ፣ አንድ ቢሊዩን ብር የተከፈለ ካፒታል ሥራውን ለማስጀመር ታቅዶል፡፡ በአጠቃላይ የአክሲዩን ማህበሩን ጠቅላላ ካፒታል፣የተሸጠውን የአክሲዩን ብዛትና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዩች ወደፊት ለህዝብ ይገለፃል ተብሎል፡፡ በአማራ ክልል ፍህታዊ የኢኮኖሚ ስርጭት የለም፣ አድሎዊ የኢንዱስትሪ ግንባታ፣ አድሎዊ የወንዜ ልጅነት የሥልጣን ክፍፍል፣ ኢፍህታዊ የባጀት ክፍፍል ለአለፉት 27 አመታት ተንሰራፍቶ መቆየቱን በማስረጃ መሞገት እንችላለን፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ ባንዳ የብአዴን የፖለቲካ ሰዎች ህዝብ የማያውቅ መስሎቸው በዚህ ኢዴሞክራሲያዊ አሠራራቸው በሥመ አማራነት በመደለል ለመቀጠል እንደማይችሉና ጎንደር፣ ወሎና ሸዋም የእራሱን ልማት በማህበር ተደራጅቶ መቀጠሉ አይቀርም እንላለን፡፡ በተዛባ የአዴፓ ወያኔዊ የሹንባሾች አሥተዳደር የአማራ ህዝብ ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ እስከ ባህር ዳር ድረስ እየሄደ መገበር የለበትም እንላለን፡፡ አዴፓ በህዝብ ተመርጦ የአማራን ርዕሰ መስተዳደር መወሰን፣ መሪውን መምረጥ፣ በክልሉ ኃብትና ንብረት መወሰን፣ የክልሉን በጀት ድልድል የመወሰን፣ የመብራት ፣ ውኃ፣ ትምህርት ቤት፣ ሆስቲታል አገልግሎት ወዘተ ፍህታዊ ድርሻና ሥርጭት መረጃ በግልፅነትና በተጠያቂነት አዴፓ በይፋ ለህዝብ አሳውቆና ለውይይት ቀርቦ ልማቱ እንዴት እንደሚዳረስ በእቅድ ተነድፎ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መቀጠል አለበት እንላለን፡፡ የአማራ ክልላዊ መንግሥትን ከሚያስተዳድረው ብአዴን ትስስር ያለው ጥረት ኮርፖሬት፣የባህር ዳርና የኮንቦልቻ ጨርቃጨርቅ አክስዩን ማህበራትን 765 ሚሊዩን ብር ለመግዛት ከመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ተወስኖል፡፡ ጥረት ኮርፖሬት በ1987 ዓ/ም ከብአዴንና ከ25 መሥራች አባላት በተገኘ 26.1 ሚሊዩን ብር የተመሠረተ ነው፡፡በአሁኑ ግዜ በሥሩ ዳሽን ቢራን ጨምሮ 18 ኩባንያዎች ይገኛሉ፡፡ ጥረት በ2008ዓ/ም ሰባት ቢሊዩን ብር የሚጠጋ ሽያጭ ማከናወኑንና የተጣራ ትርፍ 443 ሚሊዩን ብር ትርፍ ማግኘቱን የትረት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ ካሳ ገልፀዎል፡፡ የህወሓት ኢፈርት፣ የብአዴን ጥረት፣የኦሮሚያ ዲንሾ፣የደቡብ ወንዶ በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ የፖለቲካ ድርጅቶች በመላ ኢትዩጵያ ዘረፋ የሚፈፅሙ የማፍያ ድርጅቶች ናቸው፡፡

  • ከወልዲያ-ወረታ- ፍኖተ ሰላም እንዲሁም ክረታ መተማ- ሱዳን ለመዘርጋት የታቀዱ የባቡር መሥመር ፕሮጀክቶች ግንባታ
  • በባህር ዳር የሚገነው የአባይ ድልድይ በ1.4 ቢሊዮን ብር ሊገነባ ነው፣ በደጀን የሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ሥራ ተጀምሮል፡፡
  • የወረታ ደረቅ ወደበና ተርሚናል ግንባታ በ20 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን፣ ለመጀመሪያ ምዕራፍ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ይደረጋል፡፡ እንዲሁም ጥረት ኮርፖሬሽን በክልሉ ለሚገኙ የዳስ ትምህርት ቤቶች የሚውል 17.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፣ የድልድሉ ድርሻ በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎና በሸዋ ይገለጽ!!! እንዲሁም የጤና ሚኒስትር 13 የኦክሲጅን ማምረቻና ማከፋፈያ ማዕከል በባህር ዳር ከተማ የገነባ ሲሆን  የፕሮጀክቱ ዝርዝር ይገለፅ!!!

ኢህዴን፣ ብአዴን፣ አዴፓ ከ1973 እስከ 2011አ/ም ከህወሃት/ኢህአዴግ ቅጥረኛ በመሆን ለወያኔ ያገለገለ ድርጅት በአመዛኙ ከጎጃም፣ጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋ አማራዎች የተሰባሰበ ሲሆን የአማራ ክልልን ርዕሰ ከተማ ባህር ዳር በማድረግ ጎንደር፣ ወሎና የሸዋ ህዝብ ባህር ዳር ድረስ እየሄደ አስተዳደራዊ ሥራ የፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዩች ለማስፈፀም በግፍ ሲንከራተት 28 ዓመታት ተቆጥሮል፡፡ የብአዴን ባንዳዎች የጎንደርን፣ የወሎንና ሸዋን ህዝብ ሲያስገድሉ፣ ሲያሳስሩና ከወያኔ ጋር ሲሞዳሞዱ የነበሩ የአማራ ተብዬ አመራሮች በአድርባይነትና በሙስና በአስተዳደራዊ በደልና በኢፍህታዊ የልማት አድሎዊ ፀረ -ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርና የአማራ ክልላዊ መንግሥት ሹማምንትና ሓላፊነት ቦታዎች በጎጃምነት፣ በጎንደሬነት፣ በወሌነትና በሸዌነት ላይ ያጠነጠነ በመሆኑ የሰው ኃይል ምደባው የትምህርት ደረጀን ያላገናዘበ፣ የመደነኛ፣የካፒታል፣ የክልል ድጎማ በጀት አጠቃቀም ለአለፉት 28 ዓመታት አድሎዊና በጉጥ ዘረኛነት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ መሠረታዊ ለውጥ ካልተደረገና ፍህታዊ የፖለቲካና የኢኮኖሚ እድገት በአማራ ክልል ካልመጣ የአማራ ክልል ወደ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎና ሸዋ ግዛታዊ መንግሥትነት መሸንሸኑ አይቀሬ ጉዳይ ነው እንላለን፡፡

  • ለዓመታት የቆየው የመልካም አስተዳደር ችግር ርዕሰ መስተዳደሩ መፍትሄ እንዲሠጣቸው የደብረ ብርሃን ነዋሪዎች ጠይቀዋል፡፡ የብእዴን ባንዳዎች ህወሓት/ኢህአዴግን መንገድ እየመሩ ያስገቡ ወንጀለኞች በሸዋ ህዝብ በአማራው በኦሮሞው፣ በጉራጌው ወዘተ ላይ ባደረሱት ግፍና መከራ መጠየቅ ይገባቸዋል፣ የደብረብርሃን፣ የደሴና የጎንደር ህዝብ ባህር ዳር ከተማ ድረስ እየሄደ እንደ ዘመነ መሳፍንት መገበር የለበትም፡፡ በዚህ ሃያ አንደኛው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክፍለ ዘመን በጎጃሜነት፣ በጎንደሬነት፣ በወለዬነትና በሸዌነት ድንበር አጥሮ መቦደን ለሃገር አይጠቅምም እንላለን፡፡ ከክልሉ ህዝብ የሚሰበሰበው ታክስና ግብር ፍህታዊ በሆነ መንገድ ድልድል ተደርጎ ሁሉም ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን ባለፉት 28 ዓመታት የተሠሩት አድሎዊ ሥራዎች በፖለቲካ ሹመት፣ በኢኮኖሚ የሃብት ክፍፍል፣ የትምህርት ቤት፣ የሆስፒታል፣ የመንገድ ፣ የመብራት፣ የውኃ ወዘተ ሥርጭት ለውይይት መቅረብና በቀጣይነት መሰራት ያለበት እቅድ መነደፍ ይኖርበታል እንላለን፡፡
  • የደሴ ከተማ ከንቲባ በአማራ ክልል አሥተዳደር በኢህአዴግ ዘመን በወሎ ውስጥ ምንም የኢኮኖሚ የልማትና የመሠረተልማት ግንባታ አለመደረጉን አስረግጠው አሳውቀዋል፡፡

{4}የደኢህዴን ወንዶ የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች፡-

በደቡብ ክልል ፍህታዊ የኢኮኖሚ ስርጭት የለም፣ አድሎዊ የኢንዱስትሪ ግንባታ፣ አድሎዊ የወንዜ ልጅነት የሥልጣን ክፍፍል፣ ኢፍህታዊ የባጀት ክፍፍል ለአለፉት 27 አመታት ተንሰራፍቶ መቆየቱን በማስረጃ መሞገት እንችላለን፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ ባንዳ የደኢህዴን የፖለቲካ ሰዎች ህዝብ የማያውቅ መስሎቸው በዚህ ኢዴሞክራሲያዊ አሠራራቸው በስመ ደቡብነት በመደለል ለመቀጠል እንደማይችሉና ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ሃዲያ፣ ጌዲዬ፣ ጉራጌ፣ከፋ፣ጋሞ፣  የእራሱን ልማት በማህበር ተደራጅቶ መቀጠሉ አይቀርም እንላለን፡፡ በተዛባ የደኢህዴን ወያኔዊ የሹንባሾች አሥተዳደር የደቡብ  ህዝብ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ሃዲያ፣ ጌዲዬ፣ ጉራጌ፣ከፋ፣ጋሞ፣ እስከ አዋሣ ድረስ እየሄደ መገበር የለበትም እንላለን፡፡ ደኢህዴን በህዝብ ተመርጦ የደቡብ  ርዕሰ መስተዳደር ከተማን መወሰን፣ መሪውን መምረጥ፣ በክልሉ ኃብትና ንብረት መወሰን፣ የክልሉን በጀት ድልድል የመወሰን፣ የመብራት ፣ ውኃ፣ ትምህርት ቤት፣ ሆስቲታል አገልግሎት ወዘተ ፍህታዊ ድርሻና ሥርጭት መረጃ በግልፅነትና በተጠያቂነት ደኢህዴን በይፋ ለህዝብ አሳውቆና ለውይይት ቀርቦ ልማቱ እንዴት እንደሚዳረስ በእቅድ ተነድፎ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መቀጠል አለበት እንላለን፡፡     

  • ኢትዮጵያዊያን የጦርነት፣ የርሃብ፣ የበሽታ፣ የዘመነ መሳፍንት ዘመንን የተሸገሩበት ‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!!!›› ቅዱስ መሪ ቃል ነው!‹‹ኃይማኖት የግል፣ ሀገር የጋራ!!!›› ቅዱስ መሪ ቃል ከዘር፣ ከኃይማኖት፣ ከቆንቆ፣ ከክልል ልየነት የፀዳ ሰው ሰው የሸተተ ብሂል ነው፡፡‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!!!››  የኢትዮጵያዊያን ጥንታዊ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ነው፣ ‹‹ፖለቲካ የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!!!›› ወዘተ    
  • ‹‹ኃይማኖት የግል፣ ሀገር የጋራ!!!›› መሪ ቃል ህዝብን በማስተባበር ‹‹አፍሮ አይገባ›› ይባል ነበር፡፡ ጠላቶቻችን አረንጎዴ፣ ቢጫ ፣ ቀይ ስንደቅ ዓላማችንን ሲያዩ ቅስማቸው ይሰበራል፣ ከሃዲነታቸው ያንፀባርቃል፡፡ ራስ ተፈሪያኖች በእምነት ባንዲራችንን አንግበው ይዘው ኖረወል፡፡  
  • ‹‹ኃይማኖት የግልነው፣ ሀገርየጋራ ነው!!!›› የአባቶች ጥንታዊ ቅዱስ መሪ ቃል፣ አፍሮ አይገባ!!!›› ሁሉም ድረ-ገፆች፣ የቴሌቪዝን የሬዲዬ ሚዲያዎች፣ የተነጠቅንውን ቅዱስ መሪ ቃል በማስመለስ አጀንዳ እንስጣቸው፡፡ ካመንበት ቅዱስ መሪ ቃል ኃይሉ ፍቱን ነው!!! በፋሽስት ወረራ ዘመን ፋሽስቱን፣ ሰላቶ፣ ሹምባሹን፣ ያርበደበደ፤ አርበኛውን በቅዱሱ መሪ ቃል አንድ ያደረገ ነው፡፡ ለሁሉም እናካፍለው፣ እናሰራጨው፣ እንደ ሰንደቅ እናውለብልበው የእምዬ ኢትየዮጵያ ዘረኛ ፖለቲከኞ ጠላቶቻችን ዓይተው ይርዳሉ፣ ሰምተው ይደነቁራሉ፣ ዳሰው ይቀሰፋሉ፣ ቀምሰው ያስታውካሉ፣ አሽተው ይተናሉ፣ አፍሮ አይገባ ነውና!!! የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶች በዴሞክራሲ ጠበል አይፈወሱም፣ በፖለቲካ ዲስኩር አይነጹም፣ በባህር ማዶ የፈረንጅ ትምህርት አይድኑም፣ ምሳቸው የሃገረሰብ መድኃኒት የጥንት የጠዋቱ ‹‹ኃይማኖት የግል ነው፣ ሀገር የጋራ ነው!!!›› የአባቶች ጥንታዊ ቅዱስ መሪ ቃል፣ አፍሮ አይገባ!!!›› ክታባችን ስናደርግ ብቻ ነው፡፡ ከእጃችን እንደ መሃረብ፣ከጣታችን እንደ ቀለበት፣ ከራሳችን እንደ ኮፍያ፣ ክታብ አርገን አስረን ቡዳ የዘር ፖለቲከኞችን ከምድረ ገፅ እንዳይጠፉ በንስሃ እንፈውሳቸዋለን፡፡ የሃገራችን ሴረኛ የዘር ፖለቲከኞች ላይስማሙ ተስማምተዋል፡፡ ስለዚህ ይህን የአባላሽኝ ክፉ ዘመን ‹‹ኃይማኖት የግል፣ ሀገር የጋራ!!!›› የአባቶች ጥንታዊ ቅዱስ መሪ ቃል፣ አፍሮ አይገባ!!!›› ሃገራችንና ህዝብ በሠላምና በፍቅር ይሸጋገራል፡፡ ሁሉም ያልፋል፣ ሻለቃ መንግሥቱም አልፎል፣ መለስ ዜናዊም አልፎል፣ ኃይለማርያም አልፎል፡፡  መሪዎች ያልፋሉ ይመጣሉ ይሄዳሉ፣ ሃገር ግን አታልፍም፣ ዘላለማዊ ናትና! ‹‹ኃይማኖት የግል፣ ሀገር የጋራ!!!›› የአባቶች ጥንታዊ ቅዱስ መሪ ቃል፣ አፍሮ አይገባ!!!›› ከአጥናፍ አጥናፍ እናስተጋባ፣ ፈውሱ ፍቱን ነውና!  

ምን አለ፣ ምን አለ ህዝቡ በተራ!

ኃይማኖት የግል፣ ሀገር የጋራ!

ምን አለ፣ ምን አለ ህዝበ በረራ!

ፖለቲካ የግል ሀገር የጋራ!

ምን አለ፣ ምን አለ ህዝበ ሃረሪ!

ወላጅህ የግል ሃገር የጋራ!

ምን አለ፣ ምን አለ ህዝበ መቐለ!

መሬትህ የግል ሃገር የጋራ!!!

ምን አለ፣ ምን አለ ህዝበ አዳማ!

ከብቶችህ የግል፣ ሃገር የጋራ!

 ምን አለ፣ ምን አለ ህዝበ ሠመራ!

ግመልህ የግል፣ ሃገር የጋራ!