” በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ይጣራ HR 128 ይቅረብ Let International Criminal Court (ICC) investigates ethnic cleansing in Ethiopia. ( ሚሊዮን ዘአማኑኤል “

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

“ በዘር መደራጀት አይደለም ዘርን መጠየቅ ወንጀል ነው!!!” ዶክተር አብይ አህመድ ንግግር ከሩዋንዳ መልስ

ዓለም አቀፍ ትብብር በኢትዮጵያ መብት፣ (ግሎባል አልያንስ) “የኢትዮጵያን የዘር ፍጅትና መፈናቀል፣ በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንዲጣራና ኤችአር 128 እንዲቀጥል ይታገል እንላለን!!!” H.Res.128, supporting respect for human rights and encouraging inclusive governance in Ethiopia መቐለ ለመሸገው የስብዓዊ መብት ረገጣ ወንጀለኞች ዜጎችን ያለ ፍርድ በመግደል፣ በማሰቃየት (ቶርቸር በማድረግ) ወንጀል የፈፀሙ ‹‹ በአለም አቀፍ የማግኒትስኪ የስብዓዊ መብቶች ተጠያቂነት ሕግ›› መሠረት ማዕቀብ እንዲጣልባቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እንዲተገብር የአሜሪካ እንደራሴዎች ምክርቤት ጥሪ አድርጎ ነበር›› ዓለም አቀፍ ትብብር በኢትዮጵያ መብት ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችንና ዲያስፖራውን አስተባብረው አይሲሲ እና ኤችአር 128 እንዲቀጥል በገለልተኛ ተቆማት ፍርድ እንዲሰጥ ማድረግ የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው እንላለን፡፡

በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤትና ኤችአር 128 በኢትዮጵያ ያ ወርቃማ ጊዜ ጨለመ!!! ተቃዎሚ ፓርቲዎች ይሄን አስፈፅመው ቢሆን ኖሮ የህወኃት ወንጀለኞች በዓለም አቀፍ ፍርድ ባገኙ ነበር፡፡ ይህ ባለመሆኑ 3 ሚሊዮን ደሃ ህዝብ ከቀየው የመፈናቀል እጣ ፈንታው ሆኖል!!! ኦህዴድ/ ኦዴፓ የህወሓት ወንጀልን በመደበቅ፣ ለፍርድ እንዳይቀርብ በማድረግ አንድም በማረሳሳት ሚና ሲጫወት ህወኃት ደግሞ በኦነግ በኩል የውክልና ጦርነት በኢትዮጵያ ውስጥ በማድረግ ከህወሓት ወንጀል የባሳ ወንጀል በመፈፀምና በመቀመም ጉዳዩን ማዘናጋትና ትኩረት ማስቀየር ችለዋል፡፡

ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዬርጊስ መጣጥፋቸው ‹‹የከሸፈ ሀገር የሚያጠቃልላቸው ነጥቦች፡- ነፃ የፖለቲካ ተሳትፎ አለመኖር፣ የሃገር ዳር ድንበር መቆጣጠር አለመቻል፣ የግዙፍ መፈናቅሎች መኖር፣ ማህበራዊ አገልግሎቶችን (ምግብ፣ ጤና፣ ቤት.. ወዘተ) ማቅረብ አለመቻል፣ ከፍተኛ የሙስና መጨን፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ከሃገር ለመውጣት የሚፈልጉ ስደተኞች መኖር፣ ምንም ወይም ደካማ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ከላይ የተጠቀሱትን ሁሉንም ታሞላለች፡፡ ‹‹ A failed state includes: {1} Lack of control over armed forces, militias, etc. Within the country {2} Lack of free participation in politics {3} Lack of control over territory within national border {4} Massive displacements {5} Failure to provide public services food, health, shelter etc… {6} High level of corruption {7} High numbers of refugees seeking to leave {8} No or poorly functioning economy.››

ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እስከዛሬ 44 ግለሰቦችን መመርመሩ ሲታወስ ከነዚሀም ውስጥ የአፍሪካ አህጉር ሰዎች ውስጥ የኡጋንዳው ጆሴፍ ኮኒ፣ የሱዳኑ ፕሬዜዳንት የነበሩት ኦማር አል በሽር፣ የኬኒያፕሬዤዳንት ኡሁሩ ኬንያት፣ የሊቢያ መሪ የነበሩት ሙአመር ጋዳፊ፣ የአይቮሪያን ፕሬዤዳንት ሎሬት ጋባግቦ፣ እንዲሁም የዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ምክትል ፕሬዜዳንት ጂን ፔሬ ብምባ ይገኙበታል፡፡ International Criminal Court (ICC) investigates and, where warranted, tries individuals charged with the gravest crimes of concern to the international community: genocide, war crimes, crimes against humanity and the crime of aggression. The Court is participating in a global fight to end impunity, and through international criminal justice, the Court aims to hold those responsible accountable for their crimes and to help prevent these crimes from happening again. The Court cannot reach these goals alone. As a court of last resort, it seeks to complement, not replace, national Courts. Governed by an international treaty called the Rome Statute, the ICC is the world’s first permanent international criminal court.  (WikipediA)

ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዬርጊስ ፖለቲካዊ ትንተና መሬት ጠብ የማይል ሲሆን የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ውድቀት የወደፊት ዕጣ ፈንታ በሚቀጥለው መጣጥፋችን በምጣኔ ኃብት ላይ በማተኮር ቀጥለን እናቀርባለን፡፡ የኢኮኖሚ ውድቀት (Economic crisis) ይቀጥላል፡፡

ዶክተር አብይ አህመድ በእሳቸው የአንድ አመት ዘመን (ከመጋቢት 24 ቀን 2010 እስከ መጋቢት 24 ቀን 2011ዓ/ም) 13 ቢሊዮን ዶላር በዓመት እንደተገኘ ሲናገሩ በጭብጨባ አዳራሹ ቀልጦ ነበር፡፡  13 ቢሊዮን ዶላር የተገኘው  ከውጭ ንግድ ገቢ፣ ከኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ገቢ፣ ከሆቴልና ቱሪዝም የተገኘ ገቢ፣ ከውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵዊያን ዲያስፖራ ወገናችን የተገኘ የሃዋላ ገቢ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ የአራቱ ወራት ገቢ የ2010 ዓ/ም የተገኘ ገቢ ሲሆን የ8 ወራ ገቢ የ2011 ዓ/ም የተገኘ ነበር፡፡ በእርግጥ ዶክተር አብይ ከተባበሩት አረብ ኢሚሬት 1 ቢሊየን ዶላር እርዳታ፣ 1.7 ቢሊየን ዶላር ብድር፣ ከሳውዲ ግማሽ ቢሊየን እርዳታ፣ከተባበሩት መንግሥታት ይፋዊ የልማት ድጋፍ (ኦዲኤ) 1.6 ቢሊየን ዶላር እንዲሁም ውጪ ከሚኖሩ ዲያስፖራ 5 ቢሊየነረ ዶላር የሃዋላ ገቢ በአንድ ዓመት ውስጥ ተገኝቶል፡፡  በአጠቃላይ ከውጭ ንግድ ገቢ 1.64 ቢሊን ዶላር ሲሆን የገቢ ንግድ ወጪ 10.5 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የሀገሪቱ የኣለም አቀፍ ንግድ ሚዛን 8.86 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ይታያል፡፡ የውጭ ንግድ ገቢ ባለፈው 8 ወራት ውስጥ ቀንሶል (Lack of export goods and services)፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት (Lack of foreign exchange) ቀትሎል፡፡ እንዲሁም የሃገሪቱ ብድርና የብድር ጫና (Burden of loan payment) በውጥረት ላይ ይገኛል፡፡

ህገሪቱ ኢኮኖሚ ከገባበት መቀመቅ ለተወሰነ ወራቶች እያገገመ ከመጣ በኃላ በህወሓት የኦነግ ውክልና ጦርነት ኢኮኖሚው ወደ አዘቅት በወንፊት ላይ ውኃ ቢሞሉበት ወንፊት፣ ዳግም ቢሞሉበት ወንፊት ሆኖል፡፡ ከህወሓት መንግሥት መር ኢኮኖሚ ወደ ኦህዴድ መንግሥት መር ኢኮኖሚ ቀጥሎል፡፡  የህወሓት በመቐለ በፈጠረው፣ ‹‹ በመንግሥት ውስጥ መንግሥት›› (A state within a state) የህወሃት ከኤርትራ ቀጥሎ ከኢትዮጵያ ግዛት ራሱን የገነጠለ መንግሥት ሲሆን የፌዴራል መንግሥቱ ኦህዴድ/ኢህአዴግ በተሰጠው በትረ ሥልጣን የህወሓትን ጥቅም በማስጠበቅ ታማኝነቱን አስመስክሮል እንላለን፡፡

የዓለማችን የመጀመሪያው የሰው ጭንቅላት ነቀላና ተከላ ሁኔታ ተከናውኖል በእንንሰሳት በአይጥና ውሻ የጭንቅላትና አንገት ኦፕሬሽን የተሳካ ሆኖል፣ የሚል ዜና ከወደ ቻይና ጀነዋሪ 23 ቀን 2019 እኤአ ተሰምቶል፡፡ አወዛራቢው ኢጣሊያዊው ዶክተር ስርጂዋ ካናቤሮ ህክምናው የሁለት ሰዎችን  (አንዱ ጤነኛ አንዱ በሽተኛ) የሆነ ጭንቅላት ነቅሎ ወደ ሌላው ሰው አካላት ላይ ተከለ ማድረግ ነው፡፡  የህክምና ሳይንስ ዘመናዊ የአንገት ነቀላና ተከላ ክብደትና ውስብስብነት፣ የእያንዳንዱ የህብለ ሠረሠር አከርካሬዎች መግጠም፣ እያንዳንዱ የደም ሥር ጅማቶች ተገጣጥመው በአግባቡ መስራትና ዋናው የደም ቦንቦ፣ ጅረት ቦንቦ ዝርጋታና ስርጭትን ማሳካትን እንዲሁም የአንጎልና የሰውነት የነርቨ ሥርዓተ ዑደት ረቂቅነትን ያጠቃልላል፡፡ በሌሎች ሳይንቲስቶች ሙከራ ያልተሳካ አድረገው ፈርጀውታል፡፡ ከድረ-ገፁ (Dr. Sergio Canavero) ገብተው ያንብቡት፡፡ የህወሓት ጭንቅላት በኦህዴድ አከላት ላይ ነቀላና ተከላ ከተከናወነ ድፍን ዓመት ሞላው፡፡ በቀላሉ ለመግለፅ የዶክተር አብይ አህመድ ጭንቅላትና አንገትን በአረጀው የአቦይ ስብሃት ነጋ መለመላ አከላት ላይ በነቀላና ተከላ ከተከናወነ ድፍን ዓመት ተቆጠረ፡፡  የአብይ ህሊና ምን ያስባል፣ የአባይ ስብሃት  ገላ ምን ይሻል የሚለውን ጥያቄ ማሰላሰል ነው ፍልስፍና ዓለም አስቡት፡፡ ኦህዴድ የህወሓት ትምህርት ቀስሞ የፖለቲካ ሥልጣኑን በኦህዴድ ሹማምንቶች የመተካት ሥራ፣ የሚኒስትሮች ዲፕሎማቶች፣ መከላከያ ሠራዊትና ሲቪል፣ የኢንሳ ወዘተ ቢሮክራሲውን በኦሮዎች በአመዛኙ የማስያዝ ሁኔታ ይቀጥላል፡፡ ኦህዴድ/ ኦዴፓ ሀገሪቱን ኢኮኖሚው በኦህዴድ ዲንሾ የፓርቲ የንግድ ድርጅት ለመቆጣጠር  ተግቶ እየሠራ ይገኛል፡፡ 

 • የህወሓት አይነኬ ህግጋት በኢትዮጵያ፡- ህገ-መንግሥት ማሻሻል፣ በተለይ አንቀፅ 39፣ ልማታዊ መንግስት፣ አብዬታዊ ዴሞክራሲ፣ የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ወልቃይት፣ ራያ ድንበር ጥያቄ፣ የክልላዊ የማንነት የሰው ቆንቆና የመሬት የመሸጥ የመለወጥ ጥያቄ፣ መቐለ የመሸጉ ወንጀለኛችና ሙሰኞች ለህግ ተጠያቂ ማድረግ፣  አይነኬ ሕግጋት ናቸው፡፡
 • የኢህአዴግ ይነኬ ህግጋት በኢትዮጵያ ፡- የፍትህ ሥርዓት፣ የምርጫ ቦርድ፣ የሰላምና ብሄራዊ እርቅ ጉባዔ፣ የድንበር አከላለል አጥኝ ኮሚቴ፣ የሲቪል ማህበራት ማደራጀት ህግ፣ የሚዲያና ብሮድካስቲንግ ህግ፣ ወዘተ
 • የህወሓት አዲስ አውቶማቲክ የፖለቲካ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶል፣ የህወሓት የ100 ዓመት የፖለቲካ ማራቶት የሰጠን የቤት ሥራ ፣ ህወሓት ከወርቅ ሜዳልያ ወደ ነሓስ ሜዳልያ አዘቀዘቀ!!! በህወሓት ትግራይ የሠላም ደሴትና በኦነግ ኦህዴድ ኢትዮጵያ የጦርነት ቀጠና ማድረግ፣ የህወሓት ጠቅላይ ጦር ሠፈር በመቐለና የኦነግ ሽምቅ ውጊያ በወለጋ!!!  ህወሓት  ትግራይን ከኢትዮጵያ ገንጥሎል፡፡ ኦነግ ኦሮሚያን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ቀጣይ የኩረጃ ትግል ያደርግ ይሆናል!!!
 • ህወሓት ከግልፅነት ወደ ህቡዕነት ሥራ፣ ህወሓት ከፌዴራል ወደ ክልል መንግስትነት፣ ከአደባባይ ሥራ ወደ ማጀት ሥራ፣ ህወሓት/ኢህአዴግ ከግምባታ ወደ አፍራሽነት ሚና፣ ታከረቲክና ስትራቴጅ መንደፍ

   የህወሓት አዲስ አውቶማቲክ የኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ

 • የህወሓት አዲስ አውቶማቲክ የኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶል፣ የኦሮሚያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ዲንሾ የፓርቲ የንግድ ድርጅት ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት›› በዶክተር አብይ አስተዳደር ዘመን የወያኔ በክልል መንግሥታትና ተቆማት ላይ የፖለቲካ ተፅዕኖ ማሳደር ብቃቱ በመሸርሸር ላይ ይገኛል፡፡ የአዲሱ የኦሮሚያ ካቢኔ ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት››በሚል መርህ በኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዩት በፍጥነት ወደ ተግባር ለማስገባት፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና የኦሮሞ ባለሃብቶች ጥምረት ምክር ቤት መሥርቶል፡፡ ይህ ተግባራቸው ከወያኔ ፊዴራል መንግሥት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጋር ይጋጫል፡፡ ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት›› በአንድ በኩል ክልላዊ መንግሥት መር በሌላ በኩል የአንዱ ዘር ተኮር መሆኑ የህወሓት የፖለቲካ ቅጅና ኩረጃ ላይ የተመሠረተ ነው እንላለን፡፡
 • የኦሮሚያ ኢኮኖሚ አብዬት መሠረት ኦዳ ኢንቲግሬትድ ትራንስፖርት አክሲዩን ማህበር/ኩባንያ አጠቃላይ ካፒታሉ በ1.6 ቢሊዩን ብር ሲሆን የክልሉ መንግሥት ለዚህ አክሲዩን ማህበር መመሥረቻ 500 ሚሊዩን ብር የመደበ ሲሆን ቀሪው ከአክሲዩን ሽያጭና ከባንክ ብድር መሆኑ ታውቆል፡፡አክሲዮኑ በመላ ኢትዮጵያ ዜጎች አልተሸጠም፣ ለኦሮሚያ ኢንቨስተሮች ብቻ መሆኑ ዘር ተኮር ያደርገዋል፡፡
 • ኬኛ ቤቬሬጅ (ኬኛ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ) አክሲዩን ተመስርቶል፣እንዲሁም የኦሮሞ ኮንስትራክሽን አክሲዩን ማህበርና አምቦ ፕመር የተባለ የማዕድንና የግብርና ማኑፋክቸሪንግ አክሲዩን ማህበር እንደሚመሠረት ተገልፆል፡፡ የኦሮሚያ ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት››የኦዳ ትራንስፖርት ኩባንያ በግማሽ ቀን በተካሄደ የአክሲዩን ሽያጭ 617 ሚሊዩን ብር የሚያወጡ አክሲዩኖች መሸጣቸው ይታወሳል፡፡ የኦዳ ትራንስፖርት የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት የተሸከርካሪዎች ግዥ በመፈፀም እንደሚጀምርና ከወጣቶች ጋር በጋራ የሚያስተዳድራቸው የነዳጅ ማደያዎችና የነዳጅ ዲፖዎች እንደሚኖሩት ተገልፆል፡፡ እንዲሁም ‹‹የኦሮሞ የኢኮኖሚ አብዩት›› የኦህዴድ ዲንሾ የፓርቲ የንግድ ድርጅት የአሰላ የብቅል ፋብሪካ በመግዛት ሥራውን ጀምሮል፡፡
 • በኦሮሚያ ክልል ፍህታዊ የኢኮኖሚ ስርጭት የለም፣ አድሎዊ የኢንዱስትሪ ግንባታ፣ አድሎዊ የወንዜ ልጅነት የሥልጣን ክፍፍል፣ ኢፍህታዊ የባጀት ክፍፍል ለአለፉት 27 አመታት ተንሰራፍቶ መቆየቱን በማስረጃ መሞገት እንችላለን፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ ባንዳ የኦህዴድ የፖለቲካ ሰዎች ህዝብ የማያውቅ መስሎቸው በዚህ ኢዴሞክራሲያዊ አሠራራቸው በስመ ኦሮሞነት በመደለል ለመቀጠል እንደማይችሉና ወለጋ፣ ጂማ፣ ቦረና፣ ሃረር፣ ባሌ፣ አርሲ የእራሱን ልማት በማህበር ተደራጅቶ መቀጠሉ አይቀርም እንላለን፡፡ በተዛባ የኦዴፓ ወያኔዊ የሹንባሾች አሥተዳደር የኦሮሞ ህዝብ ወለጋ፣ ጂማ፣ ቦረና፣ ሃረር፣ ባሌ፣ አርሲ እስከ አዳማ ድረስ እየሄደ መገበር የለበትም እንላለን፡፡ ኦዴፓ በህዝብ ተመርጦ የኦሮሞን ርዕሰ መስተዳደር መወሰን፣ መሪውን መምረጥ፣ በክልሉ ኃብትና ንብረት መወሰን፣ የክልሉን በጀት ድልድል የመወሰን፣ የመብራት ፣ ውኃ፣ ትምህርት ቤት፣ ሆስቲታል አገልግሎት ወዘተ ፍህታዊ ድርሻና ሥርጭት መረጃ በግልፅነትና በተጠያቂነት ኦዴፓ በይፋ ለህዝብ አሳውቆና ለውይይት ቀርቦ ልማቱ እንዴት እንደሚዳረስ በእቅድ ተነድፎ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መቀጠል አለበት እንላለን፡፡ የኦህዴድ /ኢህአዴግ መንግሥት ልክ እንደ ህወሓት መንግሥት በዘር ተኮር የሥልጣን ፈረቃ ለናሙናነት ለመጥቀስ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ካሉት 58 የቢሮ ሃላፊዎች ውስጥ 31 ኦሮሞ፣ 11 ደቡብ፣ 9 ትግራዋይ 7 አማራ ናቸው፡፡ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ50 የባንክ ሹማምንቶች ውስጥ 31 የኦህዴድ አባላት መሆናቸው ታውቆ፡፡
 • ኦህዴድ/ ኦዴፓ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ‹‹የኦሮሚያ ኢኮኖሚ አብዬት›› የኢትዮጵያን መዓድን ኃብት በተለይ የለገደንቢ ወርቅ መዐድን ኃብት ስምምነት በኦሮሞ ክልል ንብረትነት ድርሻ በማድረግ ከሜድሮክ ጎልድ ጋር በሼር ኃብቱን ይካፈሉ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ የጫረብን የለገደንቢ ወርቅ ማዕድን ሥራውን እስካሁን ባለመጀመሩ የሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ እየተመናመነ በመጣበት ሁኔታ ውሉን ለማደስ ያልተሞከረበት ሚስጢር ኃብቱን የአላሙዲንና (51 በመቶ) የኦህዴድ/ ኦዴፓ (49 በመቶ) ድርሻ በሚስጢር ያለ አዲስ ስምምነት እየተወጠነ መሆኑ የሚናገሩ ‹የሰይጣን ጆሮ አይስማው› ይላሉ፡፡ ህወኃት/ኢፈርት የኢዛና የወርቅ ማዕድንን ለትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ኃብት ማድረጉ ለኦህዴድ/ ኦዴፓ የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን ኃብት የግሉ የማድረግ ትምህርት ይቀስማል ይባላል፡፡ ሌሎቹንም የሃገሪቱን የማዕድን ኃብት በዚሁ ዓይነት መንገድ በመቆጣጠር (የኦሮሚያ ኢኮኖሚ አብዬት) የሚመሩትን አቶ ለማ መገርሳ ኢሳት፣ ቪኦኤ፣ ኦኤምኤን፣ የአገር ውስጥ ሚዲያዎች ሊጠይቁ ይገባል እንላለን፡፡
 • ኦህዴድ/ ኦዴፓ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ‹‹የኦሮሚያ ኢኮኖሚ አብዬት›› ለማጠናከር አዲስ አበባ ኮንዶሚንየም 51 ሽህ ቤቶች መውረሱን ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ ኢኮኖሚውን የተቆጣጠረ ፖለቲኮውንም ይቆጣጠራል የምንለው ለዚህ ነው፡፡
 • የኢሳት ‹‹አውደ ኢኮኖሚ››ፕሮግራም የትግራይ፣የአማራና የኦሮሞ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥቶች፣ መንግሥት መር ኃብቶችን በመንግሥትና በአክሲዬን የህዝብ ኃብትነት የማዘዋወር እቅድን በማድነቅ ገልጸውታል፡፡ ሆኖም የክልል ዘር ተኮር መንግሥቶች  አክሲኖቹ ለአንድ ዘር ወይ ለትግራይ፣ ለአማራና ለኦሮሞ የተመረጠ ዘር ብቻ መሽጡን የተረዱ አይመስለንም፡፡ በኢትዮጵያ ህግ መሠረት የአንድ አክሲዬን ሽያጭ ከዘር፣ ከኃይማኖት፣ ከፖለቲካ ወዘተ ልዩነቶች ውጪ የመላው ህዝብ ኃብትና ንብረት ሊሆኑ ይገባል እንጂ በአንድ ዘርና ፖለቲካ ላይ የተመሠረተ መሆን የለበትም ይላል ፡፡ የወጋጋን አክሲዬን የተሸጠው ለትግራዎይ ነው፣ የአዋሽና ኦሮሚያ ባንኮች አክሲዬን ለኦሮሞዎች፣ የአባይ ባንክ አክሲዮኖች ለአማራዎች ብቻ መሆኑ የፋይናንስ ባንክ ዘርፉን መቀመቅ ከቶታል፡፡ ስለዚህ በ‹‹የኦሮሚያ ኢኮኖሚ አብዬት›› ስም የተሸጠው አክሲዬን የክልሉና የህዝቡ የአንድ ዘርና ፖለቲካ ፓርቲ መሆኑ የመላ ኢትዮጵያዊ ባለኃብትን ያላሳተፈ ዘር ተኮር፣ ፖለቲካ ተኮር በመሆኑ በፕሮግራማችሁ እርምት ያሻዋል እንላለን፡፡
 • የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) ትጥቅ ሳይፈታ ወደ ሃገር ቤት ያሰገባው ኦህዴድ/ ኦዴፓ ሲሆን ሌሎቹ አማፂን ድርጅቶች ትጥቅ ፈተው በሰላማዊ መንገድ መግባታቸው ይታወቃል፡፡ ኦነግ በወለጋ ውስጥ 18 ባንኮች ዘርፎ እንዲጠናከር አድርገዋል፡፡
 • ኦህዴድ/ ኦዴፓ መንግሥት ደግሞ ከስምንቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኤክስኪውቲቭ ኃላፊዎች 5ቱ ኦህዴድ ፖለቲካ ካድሬዎች ተሸመዋል፣አቶ ባጫ ጊና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና ፕሬዜዳንት፣ አቶ ኑሪ ሁሴን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ዋና ፕሬዜዳንት፣ አቶ አሊ አህመድ የኢንብ የሰው ኃይል ኃላፊ፣ መሊካ በድሪ የኢንብ የፋይናንስ ኃላፊ፣ ሱራ ሰቀታ የኢንባ የህግ ኃላፊ፣ ፍቅረሥላሴ ዘውዱ የኢንባ የቢዝነስ ኃላፊ፣ ጥሩ ብርሃን ኃይሉ የኢንባ ሪስክ ማኔጅመንት ኃላፊ፣ ኪዳኔ መንገሻ የኢንባ የውስጥ ኢዲት ኃላፊ ናቸው፡፡ አቶ ወዮ ሮባ አካኮ የስኮር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሸሙ፣የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አወቃቀርም በአመዛኙ ከህወኃት ሰዎች ወደ ኦህዴድ የፖለቲካ ሹሞች መሸጋገሩ ፈረቃ አስኝቶታል፡፡ ሜጀር ጀነራል ከማል ገልቹ ከስልጣን መነሳት በኦነግ ጥያቄ መሰረት ተነስተዋል፡፡ ኦህዴድ ከህወሓት የቀሰመው ትምህርት በዘር ተኮር ሹም ሽረት ላይ ያተኮረ ትውልድ ገዳይ ሃገር የማያዘምን የዘር፣ የዝምድና አድሎዊ አሰራር በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ስታዲም ተመርቆል አንቦ ስታዲም ይቀጥላል፡፡

ከመጋቢት 24 ቀን 2010 እስከ መጋቢት 24 ቀን 2011ዓ/ም) ዶክተር አብይ አህመድ   

{I} የትግራይ ብሄራዊ ክልል ክኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት ከተገነጠለ አንድ ዓመት ሞልቶታል፡፡ መቐለ የመሸገው ፀረ ዴሞክራሲ ኃይል በስብዓዊ መብቶች ጥሰት፣ ግድያ፣ ግርፋት፣ ስነልቦናዊ ቀውስ፣ ለፍርድ ሳይቀርቡና ተጠያቂ ሳይሆኑ ፌዴራል መንግሥቱ በክልሉ መንግሥት እጅ ሰጥቶል፡፡ በሙስናና ሌብነት የተዘረፈ የህዝብ ኃብት ተዘርፎ ቀርቶል፣ የአንዳቸውም ዘራፊዎች ኃብትና ንብረት ተሸጦ ሲመለስ አላየንም አልሰማንም፣ በአዲስ አበባ ከተገነቡት 400 ፎቆች 300 ፎቆች የህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲ የንግድ ድርጅቶችና ሹማምንት ሃብት መሆናቸው ቢታወቅም ምንም እርምጃ አልተወሰደባቸውም፡፡ የህወሓት/ኦህዴድ ኢህአዴግ፣ የፋይናንስ ባንኮችና ማይክሮ ፋይናንስ የፓርቲ ድርጅቶች  መለመላቸውን ገብተው ሃገር በተቆጣጠሩ  ባለፈው 27 ዓመታት ውስጥ ባንኮቹን ፣ ኢንሹራንሱን፣ ፋብሪካዎቹን፣ መሬቱን፣ ፎቆቹን፣ መኪኖቹን፣ ሁላ በአስማት በነቀላና ተከላ ወረሱት፡፡

{2} የህወሓት፣  በመንግሥት ውስጥ መንግሥት (A state within a state) ) የህወሃት/ኦህዴድ ኢህአዴግ የጦር አበጋዞች መንግስት  በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሱማሊያ በደቡብ ክልሎች በኩል ከኢትዩጵያ ድንበር ዘለል የወርቅ መዕድን ንግድ፣ የቁም እንስሳት ንግድ፣ የጫት ንግድ፣ የሠሊጥ ንግድ ወዘተ ወደ ሱዳን፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያና ኤርትራ በመላክና በመሸጥ ዳጎስ ያለ የውጭ ምንዛሪ ዶላር፣ የብሄራዊ ክልላዊ መንግሥቶች በተለይ የትግራይ ኢፈርት፣ የአማራው ጥረት፣ የኦሮሞው ዲንሾ፣ የደቡቡ ወንዶ እንዲሁም፣ የፖለቲካ የንግድ ድርጅቶች (የቢዝነስ ሞኖፖሊ) በውጭ ሃገራት ባንኮች የዘረፈውን በማስቀመጥ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ዋነኛ ተግዳሮት በመሆን በዶክተር አብይ ዘመነ መንግሥት የውጭ ገንዘብ ዝውውር፣ የጦር መሣሪያ ዝውውር፣ ህገ ውጥ የመድኃኒት ሽያጭ ዝውውር የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ባዶ ካዝና እንዲሆን አድርጎታል፡፡

{3} የህወሓት የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤትና የክልል ምክር ቤቶች ተጠሪ የፖለቲካ ሹማምንቶች ከፓርላማ ስብሰባ ከኮበለሉ ዓመት ሞልቶቸዋል፡፡ መቐለ የመሸገው ሹማምንት የፌዴራል መንግሥት የሚያወጣውን መግለጫዎች ሁሉ በመቃወም የመልስ ምት በአፋጣኝ ይሰጣሉ፡፡  

{4} የኦህዴድ /ኢህአዴግ መንግሥት ፓርላማ ለትግራይ መንግት የ 200 ሚሊዮን ዶላር (5.4 ቢሊዮን ብር) ብድር ለመቐለ ህዝብ የንፁህ ውኃ ስርጭት ብድሩን አፅድቆል፡፡

{5}  ኦህዴድ/ ኦዴፓ፣ ከህወሓት ተላላኪ የኦነግ የጦር አበጋዞች ዳውድ ኢብሳ በወለጋ፣ ጉጂና ቦረና አካባቢውን የጦርነትና ሽብር ቀጠና አድርገውታ፡፡ 18 ቦንኮች ዘርፈዋል፣ መሰረተ ልማቶች አፍርሰዋል፣ በሰሜን ሸዋ አጣየ፣ ካራቆሬ፣ ከሚሴ፣ ማጀቴ፣ ጨረርቶ፣ ኤፍራታ እና አካባቢው በግፍ ሰዎች ገለዋል፣ አቁስለዋል፣ ንብረት ዘርፈዋል ፣ በመተማ፣ በደቡብ ወሎ  ከሚሴ ወዘተ ህዝቡ መከላከያ ሠራዊት ለኦነግ እያገዘ ነው ይላል፡፡ በተመሳሳይ የቡራዮ ግድያና መፈናቀ እንዲሁም የለገጣፎ ግድያና መፈናቀ የህግ ተጠያቂነትና ፍትህ የውኃ ሽታ ሆኖል፡፡ ዛሬ ደግሞ ኦነግ በይፋ ከዋናው ድርጅቱ ከእነ ዳውድ ኢብሳ መለየቱ እና በ7 በላይ በሆነ የእዝ አደረጃጀት ተደራጂቶ እየተንሳቀሰ መሆኑ ተገልፆልናል፡፡ ባለፈው ጊዜ ኦነግ ሠራዊቱን ለአባ ገዳዎች አስረከበ ያሉን ትያትርን አይተን ሳንጠግበው አነሱብን፡፡ በኢትዮጵያ ሚዲያዎች ‹‹ የኢትዮጳያ የደኅንነት ሥጋት የብሄር ፖለቲካ ነው ›› የኢትዮጵያ መንግሥት  ይፋ አድርጎል፡፡ በአጠቃላይ የኦሮመን ህዝብ ከአማራ ህዝብ ጋር የማጋጨት የቆየ የህወሓት ሴራ ነው፡፡

{6} ‹‹በየካቲት ወር የተመዘገበው የ12 ወራት ተንከባላይ አማካይ አገራዊ የዋጋ ግሽበት በ13 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን፣ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ይፋ አደረገ፡፡ ኤጀንሲው ዓርብ የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ይፋ እንዳደረገው፣ ረዘም ያለ ጊዜ የዋጋ ግሽበት ሁኔታን  በሚያሳይ የ12 ወራት ተንከባላይ አማካይ የዋጋ ግሽበት አማካይነት በተደረገው ምዘና፣ በዚህ ዓመት የካቲት ወር  የ12 ወራት ተንከባላይ አማካይ አገራዊ የምግብ የዋጋ ግሽበት በ11.7 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ የ12 ወራት ተንከባላይ አማካይ አገራዊ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበትም በ14.4 በመቶ ጭማሪ አሳይተዋል ብሏል፡፡››

የክልል ዘር ተኮር መንግስቶች ህወኃት/ ብአዴን/ ኦህዴድ/ ደኢህዴን  የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ በክልላቸው ውስጥ ስውር ሥራዎች በማደራጀትና አንዱ አንዱን በመክሰስ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻውን አጦጡፈውታል፡፡

{I} የየክልሎቹ መገናኛ ብዙኃን የቴሌቪዝንና ሬዲዬ ሥርጭት የጦርነት ነጋሪ በመጎሰምና መግለጫዎች በማንጋጋት ያለ አንዳች የህዝብ ውክልና ፣ ህዝብን ከህዝብ የሚያጣሉ፣ የህዝብ አውንታ የሌላቸው ኢህአዴግ ዘር ለዘር እያጋጩ በሥልጣን የመቆየት ቀጣይ የቤት ሥራ ለህዝብ ሰጥተዋል፡፡

{II} ክልሎች የራሳቸው መከላከያ ኃይል  በማደራጀት ካራ እያሳሉ ይገኛሉ፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ በመቐለ ከመሽገ አመት አስቆጠረ፣ በስብአዊ መብት ጥሰት የተከሰሱና በሙስና ሌብነት ወንጀል የህዝብ ኃብት የዘረፉ ሹማምንቶችን አሳልፈን አንሰጥም በማለት የፌዴራል መንግስቱን ሥልጣን ተጋፋ፡፡

{III} የየትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ክልል ባንኮችና የማክሮ ፋይናንስ ተቆማቶች፣የኢትዩጵያ ባንኮችና ኢንሹራንሶች የማን ኃብት ናቸው??? የክልል ዮኒቨርሲቲዎችና የእግር ኮስ ክለቦች፣ የመኪና ታርጋ ወዘተ ዘርን ያማከለ ሥራ ቀጥሎል፡፡

{IV} ክልሎች የራሳቸው የደህንነትና የስለላ ሥራ በማደራጀት የትግራይና የአማራ ህዝብ በሠላም እንዳይኖርና አርሻውን እንዳያርስ አድርገውታል፡፡

{V} የፌዴራል መንግሥት የበጀት ድልድል ቀጥሎል፡- የኢሕአዴግ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወኃት)፣ ሹማምንትና ካድሬዎች መደበኛው በጀት ለብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት ለመንግስት ሠራተኛ ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ፣ ዳጎስ ያለ ጥቅም ያገኛሉ፡፡

ግሎባል አልያንስ ‹‹የኢትዮጵያን የዘር ፍጅትና መፈናቀል፣ በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንዲጣራና ኤችአር 128 ጥያቄ ይቀጥል እንላለን!!!›› በህወሓት/ ኦህዴድ ኢህአዴግ መንግሥት ላይ ዲያስፖራው ወገናችን ለዓለም ህብረተሰብ ማሳወቅና በሃገሪቱ የህግ ሉዓላዊነት ሊከበር ያልቻለው መቐለ በመሸገው ወንበዴና ወንጀለኛ ያሰማሩት የኦሮማ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ)  የውክልና ጦርነት መላ ሃገሪቱ ውስጥ  3 ሚሊዮን ህዝብ መፈናቀሉን በጊዜው ልታሳውቁለትና ወደ እርስ በእርስ ጦርነትና የዘር ፍጅት እንዳይሸጋገር ማድረግ ኃላፊነት አለብን እንላለን፡፡‹‹ሳይቃጠል በቅጠል›› ብለን ከልብ እናሳስባለን፡፡ ግሎባል አልያንስ ለኢትዮጵያ ተፈናቃይ ደሃ ህዝብ ላደረጋችሁት ህዝባዊ ድጋፍ ታሪክ ያስታውሳችሆል፡፡

በዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የኢትዮጵያን የዘር ፍጅትና መፈናቀል በገለልተኛ አካል ይጣራ!!! ኤችአር 128 እንዲቀጥል ዲያስፖራ ይታገል!

ኦህዴድ‹‹የውጭ አንበሳ፣ የውስጥ ሬሳ!!! ‹‹ኦነግ  አባ ቶርቤ!!!››

ኤችአር 128 ይጠናከር