ዛሬ ለምርጫ የምንሯሯጥበት ሰአት እይደለም (ተካልኝ ጎዳና (ከስዊድን) )

ወደ ዋናው የዚህ ጽሁፍ አላማ ከመግባቴ በፊት መነሻ ይሆናሉ የምላቸውን ነጥቦች ልጠቅስ እወዳለሁ። ብዙ የተነገረባቸውና የተጻፈባቸው ስለሆነ ዝርዝሩ ውስጥ መግባት ጊዜ ማጥፋት እንዳይሆን ከየት ተነስተን የት ደርሰናል የሚለውን እንደሚከተለው ማጠቃለል ይቻላል።

አንደኛ፣ ዛሬ ያለንበት አንጻራዊ ነጻነት ሊመጣ የቻለው በብዙ ዘመናት የህዝብ ትግል ነው። በተለይም ለሶስት አመታት በዘለቀ የወጣቶች ትግል መሆኑ በገሀድ የታየ ነው። ከዚያ ቀደም ብሎም የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ለመብታቸው ያደረጉት ትግል አስትዋጻኦ ከፍተኛ ነው። በትግል ሂደቱም ብዙዎች ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈሉበት ነው። የኔ ይበልጥ የኔ ይበልጥ ፉክክር የትግልን ውስብስብነትና እድገት (dynamics) ያለመገንዘብ ይሆናል። ጠቃሚነትም የለውም።

ሁለተኛ፣ በኢሃዴግ ውስጥ ለውጥን ለሚሹ በር የከፈተው የህዝብ ትግል አመራርና ቅንብር የጎደለው እንደነበር በዚያም ምክንያት ግልጽ አላማና አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያልቻለ እንደነበር የሚያጠያይቅ አይደለም። በዚህም ምክንያት ብዙዎችን በከፍተኛ ፍርሀትና ጥርጣሬ ውስጥ የከተተ ሁነታ ተፈጥሮ ነበር። የአዲስ አበባ የዳር ተመልካች ሆና መቆየት ከዚህ አክዋያ ሊታይ ይችላል፡ ይህም በመሆኑ ኢሃአዴግ ጥቂት አመራሮችን ብቻ ቀይሮ እንደ ድርጅት ለመቀጠል አስችሎታል። ከዚያም አልፎ ለውጡን ያመጣሁላችሁ እኔ ነኝ እስከ ማለት ደርሶአል። እመራር የሌለው ትግል መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ስለማይችል ህዝቡ በአዲሱ የአኢሃእዴግ አመራር ቃል የተገባውን  የጥገና ለውጥ ከመቀበል የተሻለ ምርጫ አልነበረውም። የአዲስ አበባና የሌሎች ትላልቅ ከተሞች ህዝብ የ ዶ/ር አቢይን አመራር ሆይ ብሎ የተቀበለውም የወያኔ አምባገነንነት ከጫንቃው ስለተነሳለት ብቻ ሳይሆን ከገባበት ስጋትና ጭንቀትም ስላላቀቀው ጭምር ነው።

ሶስተኛ፣ የዶ/ር አቢይ መንግስት በገባው ቃል መሰረት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ተስፋ የሚሰጡ እርምጃዎችን ወስዶአል እየወሰደም ይገኛል። ከነዚህም ውስጥ አፋኝ አዋጆችን ማሻሻል፣ለዲሞክራሲ አስፈላጊ የሆኑ ድርጅቶችን እንደገና የማዋቀር ጥረት በተቀዳሚንትየሚጠቀሱ ናቸው። በጠላትንት የተፈረጁ ድርጅቶችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአገሪቱ ፖለቲካ እንዲሳተፉና እንዲንቀሳቅሱ መጋበዝም ትልቅ አስተዋይነትና የፖለቲካ ወኔም የሚጠይቅ ነው። ያሉት አዎንታዊ እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው የተደረጉት ለውጦች ኅዝብን ባሳተፈ መልኩ ባለመሆኑ ዘለቄትነታቸውና ጥልቀታቸው አጠያያቂ ቢሆን አያስገርምም። ከእንጊድህ ብሁዋላ ህዝቡ የለውጥ ተመጽዋች ሳይሆን የለውጥ ቀራጭና ባለቤት የሚሆንበትን መንገድ መሻት ይጠይቃል። ለዚህም ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እንዴት ወደፊት መራመድ ያስፈልጋል የሚለው በአንክሮ መታየት ይኖርበታል።

የተቻኮለ ምርጫ የህዝብን ተሳትፎ አያረጋግጥም

ብዙው እንደሚስማማው ዛሬ ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች:: ወደ ብሩህ አቅጣጫ የማምራት መንገዱ የመከፈቱን ያህል ወደ አስከፊ አቅጣጫ የመገፋቱ አደጋም የሚናቅ አይደለም:: የለውጥ ሀይል ተብሎ የሚጠራው ቡድንም በተለያዩ ጽንፈኛ ቡድኖች አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ እየገባ ያለበት ሁኔታ ነው የሚታየው። በዚህ ተስፋና ቀውጥ ተቀላቅለው በሚታዩበት ወቅት ለምርጫ መሯሯጥ ሊያስከትል የሚችለውን ቀውስ ከግንዛቤ በማስገባት አማራጭ ጎዳናዎችን መቃኘት ያስፈልጋል:: የሚቀጥሉት ሁለት አመታት ለአገራችን ወሳኝ እንደመሆናቸው መጠን በተለያዩ አማራጭ መንገዶች ላይ ተወያይቶ ስምምነት ላይ መድረስ ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም። የዚህ ፅሁፍ አላማም አንድ የመፍትሄ ሃሳብ ለመሰንዘርና ሌሎችንም  አማራጭ የመፍትሄ ሀሳቦችንም ለመጋበዝ ነው:: መሰረታዊ የመፍትሄ ሃሳቡ፣ ለምርጫ አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች ገና ያልተሟሉ በመሆኑ የሚቀጥለው ምርጫ ለሁለት አመት እንዲዘገይ፣ ከፖለቲካ ፓርቲ ማነቆ ነፃ የሆነ የባለሙያዎች መንግስት በገለልተኝነት ለነፃና ፍትሃዊ ምርጫ አስፈላጊውን ሁኔታ እንዲያመቻች፣ የለውጡ ባለቤት የሆነው ህዝቡ የዳር ተመልካች መሆኑ አብቅቶ የቀጥታ ተዋናይነቱ የሚረጋገጥበት ሁኔታ እንዲመቻች የሚያሳስብ ንው::

ዛሬ ለነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ሁኔታዎች ያለመኖራቸው የሚያጠያይቅ አይደለም

የኢትዮዽያ ህዝብ ለምርጫ እንግዳ አይደለም።  ከንጉሳዊ ስርአቱ ጀምሮ በደርግ ተሻግሮ እስከወያኔ የይስሙላ ምርጫዎች ሲፌዝበት የኖረ ህዝብ ነው:: የሚመኘውና የሚናፍቀው ነፃና ፍትሀዊ ሊሆን የሚችል ምርጫ እንጂ የጊዜ ሰሌዳ ለማክበር ብቻ ሲባል የሚደረግ ምርጫን ሊሆን አይችልም:: ነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ለማድረግ ሁኔታው አለ ቢባል ከእውነቱ የራቀ ይሆናል። ይህ እንዲሆን ጉዞው ቢጀመርም ብዙ የሚቀረው አለ::

 1. አስፈላጊ የሆኑት የዲሞክራሲ ምርጫ አካላትና ድንጋጌዎች ገና በጅምር ነው ያሉት:: እነዚህ ስራዎች በአጥጋቢ ሁኔታ በሚቀጥለው እንድ አመት ውስጥ መሬት ወርደው ምርጫውን ተአማኝ ለማድረግ ያለው እድል አነስተኛ ነው
 2. አገር ቤት የነበሩትም ይሁን ከውጭ የገቡት ድርጅቶች ገና ራሳቸውን ለህዝብ ለማስተዋወቅ አላማቸውንና ቅርፃቸውን እየመረመሩ የሚገኙበት ሁኔታ ነው ያለው:: የድርጅቶች ውህደቶች ጥምሮች የመመስረት ጉዞ ገና ዳዴ እያለ ባለበት ሁኔታ ግልጽ የፖለቲካ አማራጮቹ ለህዝቡ ማቅረብ አዳጋች ነው። ግልጽነት የሌለው የምርጫ ውድድር ደግሞ አካሄዱም ሆነ ውጤቱ አደጋ ያዘለ ነው።
 3. ከሁለት እስክ ሶስት ሚልዮን የሚጠጋ ህዝብ ከቄዬው በተፈናቀለብት ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ የእነዚህን ተፈናቃዮች ድምፅ አልባ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የእፈናቃዮችንም እኩይ አላማ ማሳካት ነው የሚሆነው።
 4. አይን ባወጣ መልኩ እኔ ቦታ ድርሽ ብትል የሚለው ዛቻ ማስፈሪርያና የጉልብት እርምጃዎች በነፃ ተንቀሳቅሶ ሃሳብን ለማራመድ በማይቻልበት ሁኔታ ፍትሀዊ ምርጫ የሚታለም አይደለም:: በተለይም ይህ አይነቱ ህገወጥነት በክልል አመራሮች ጭምር በቀጥታም ይሁን በተዘዋራሪ መንገድ በሚበረታታበት ሁኔታ ምርጫ ፌዝ ነው የሚሆነው:: የመንግስት ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ ያለው ቁርጠኝነት የሚመዘነው በተለያየ የስልጣን እርከን ያሉ አስተዳደሮች የሚፈጥሩትን እንቅፋት ያለአመንታት መታገል ሲችል ብቻ ነው:: ይህን ለማድረግ ቁርጠኝነት ብቻ ሳይሆን  ጊዜም የሚጠይቅ ነው።
 5. ሰላም መረጋጋትና የዜጎች የህይወትና የንብረት ዋስትና በሌለበት ዲሞክራሲ ቅንጦት ብቻ ሳይሆን ሊታለምም የሚቻል አይደለም። ምርጫ እንክዋን መረጋጋት በሌለበት ቀርቶ በተረጋጋ ሁኔታ እንኽዋን እጅግ ተፈታታኝ ነው።

በእነዚህ አንኳር ምክንያቶች የሚቀጥለው ብሄራዊ ምርጫ እሁን በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ ቢካሄድ ነፃና ፍትሀዊ ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ እጅግ ይከብዳል::ግርግር ለሌባ ይመች እንደሆን እንጂ ለማንም አይጠቅምም::

ለሁለት አመት የሚያገለግል ገለልተኛ አስተዳደር አስፍላጊነት

 • የኢትዮዽያ ህዝብ ተጨማሪ ሁለት አመት የኢህአዴግን አገዛዝ እንዲሸከም መጠበቅ የህዝቡን ትእግስተኝነት እንደሞኝነት መቁጠር ይሆናል። ስለዚህም የአሁኑ ፓርላማ ዘመን በጊዜው ሰሌዳ መሰረት ከአንድ አመት በህሗላ ማብቃት ይኖርበታል።
 • ኢህአዴግ የመንግስት ፓርቲነቱ አብቅቶ እንደማንኛውም የፓለቲካ ፓርቲ ለሚቀጥለው ምርጫ ተፎካካሪ ይሆናል:: ይህ ኢህአዴግን ከሌሎች ፓርቲዎች በእኩልነት ማሳተፍ የኢትዮዽያ ህዝብን ጪዋነትና ገደብ የለሽ ይቅርባይነትን የሚመሰክር ርርጊት ነው::
 • በጠቅላይ ሚንስቴር ኣቢይ የሚመራ የሙያተኞች ካቢኔ ለሁለት አመት አገሪቱን የማረጋጋትና ለዲሞክራሲ ሽግግር ማዘጋጀት ስራ ያከናውናል:: ይህ አሰራር በተለመደው መንግድ መንግስት ለማዋቀር አስቸጋሪ ሲሆን እንደ አማራጭ የሚተገበር ነው::በብዙ እገሮች ባላደራ መንግስት (care taker government) በመባል ይታወቃል:: እንድዲህ ያለ መንግስት ከፓርቲ ፖለቲካ ተፅእኖ ነፃ ሆኖ በሚዛናዊነት የመንግስትን የቀን ተቀን ተግባራት ያከናውናል:: በኢትዮዽያ ልዩ ሁኔታ ይህ መንግስት ከኢህአዴግ 27 አመት ፈላጭ ቆራጭ መንግስት ወደ በነፄና ፍትሀዊ ምርጫ የሚቓቓም መንግስት መሸጋገሪያ ድልድይ ሆኖ ስለሚያገለግል የሽግግር መንግስትም ተብሎ ሊታይ ይችላል::
 • የሚቋቋመው መንግስት በ ዶክተር እቢይ መመራት አስፊላጊነት ሁለት መሰረታዊ ምክንያቶች አሉት:: አንደኛ ያለምንም የስልጣን ክፍተት የመንግስት ተግባሮች ቀጣይነትን ያረጋግጣል:: አገሪቱ ዛሬ ባለችበት የዋዠቀ ሁኔታ ለአንዲት ቀንም እንኳ ቢሆን የማእከላዊ መንግስት ስልጣን ክፍተት መኖር አደገኛ ነው:: ሁለተኛውና ዋናው ለዶክተር አቢይ አመራር በስልጣን መቀጠል ምክንያት ባለፋት 18 ወሪት በንግግራችውና በወሰድዋቸውም እርምጃዎች አገር እቀፍ ተቀባይነትን እትርፈዋል:: ምንም እንክዋ አንዳንድ ጥያቄዎች እይተነሱባቸውም ቢሆንም የሳቸውን ያህል ተሰሚነት ያለው ሌላ የፖለቲካ መሪ ዛሬ አለ ማለት አይቻልም:: ቃል እንደገቡት አሸጋግሩን ብሎ መማጽን የግድ ሊል ነው። ሆኖም ግን ህዝብን ባሳተፈ መልክ ኢንዲሆን መግፋትን ይጠይቃል።

የህዝብን ንቁ ተሳትፎ ማረጋገጥ::

 • የምርጫውን መራዘም የግድ ያሉት ችግሮች በመንግስት ጥረት ብቻ የሚወገዱ ስላልሆኑ የተለያዪ ህብረተስብ አካላት የሚወከሉበት የብሄራዊ የለውጥ ምክክር ቤት መቋቋምን የግድ ይላል:: እስካሁን የለውጥ ጅማሮዎች የህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያልነበራችው በመሆናቸው የሚቀጥለው የሽግግር ጊዜ ህዝብን አሳታፊ መሆን ይኖርበታል:: እንዱ አሻጋሪ ሌላው ተሻጋሪ መሆኑ አብቅቶ ሁሉም የሽግግሩ ባለቤትና የበክሉን አስተዋፅኦ የሚያደርግበት ሊሆን ይገባል::
 • የምክክር ቤቱ ዋና እላማ እገር ለማረጋጋትና ለዴሞክራሲ ምርጫ የሚደረገውን ዝግጅት ማገዝ ሊሆን ይገባል:: ሆኖም ግልፀኝነትንና ተአማኒነትን ለማረጋገጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዲሞክራሲ ሽግግሩንና አገር ማረጋጋትን ብሚመለክት መንግስታቸው እያካሄደ ያለውን ስራ ቋሚና ተከታታይ በሆነ መልክ ከብሔራዊ የምክክር ቤቱ ጋር ውይይት እንዲያደርጉ ይጠበቃል:: ሆኖም ግን የመንግስትን ስልጣንና ተግባርን ከምክክር ቤቱ ሃላፊነት ጋር እንዳይቃረን ጥንቃቄ ይጠይቃል።
 • የምክክር ቤቱ አባላት እስካሁን እንደተለመደው በጠ/ሚንስትሩ የሚመለመሉ ሳይሆን በቀጥታ በየድርጅቶቻቸው የሚወከሉ መሆን ይኖርባቸዋል:: ይህም በዲሞክራሲ ጎዳና አንድ እርምጃ ተጏዝን ማለት ያስቻላል:: በቀዳሚነት ተወካዮቹ ከፓለቲካ ድርጅቶች ክሙያ ማህበራት ከሲቪክ ማኅበራት የሚውጣጡ ቢሆንም የራቸውን ድርጅት ጥቅምና ፍላጎት የሚያራምዱ ሳይሆን በጋራ የአገሪቱን የለውጥ ሽግግር እንቅፋቶችን ለማስወገድ መስራት መሆን ይኖርበታል:: ምክር ቤቱ የስልጣን ሽኩቻ ሜዳ እንዳይሆን በዚህ ምክር ቤት የሚወከሉ ግለስቦች ከሚቀጥለው የምርጫ ውድድር እራሳቸውን ማግለል ይጠበቅባቸዋል::

መልካም የሽሽግግር ጊዜ ይሁንልን!