” በዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ ዘመን፣ የሃገራችን ደረጃ የት ነው ” ( ሚሊዮን ዘአማኑኤል )

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMy

በቻይናና መንግሥት ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ የኢንዱስትሪ ሸቀጣ ሸቀጦችና የግብርና ምርቶች የዲጂታል ቴክኖሎጅ በኤሌክትሮኒክስ እየተላለፈና እየተሰራጨ የሚካሄድ ዘመናዊ ሽያጭ ለኢትዮጵያ መንግሥት ለማከናወን የሁለትዬሽ ስምምነት አድረገዋል፡፡ የቻይና መንግሥት የኢትዮጵያን የኮሜርሻል ገበያ ተኮር የሆኑ የግብርና ምርቶች (ቡና፣ ሠሊጥ፣ የቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ቅመማ ቅመም ወዘተ) በዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ አገልግሎት ያዘመኑ አገራቶች የደሃ አገራቶችን የግብርና ምርቶች በዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ የደሃ አገራት ገበሬዎችን በመፈንገል ምርታቸውን በዓለም አቀፍ ገበያ በመቆጣጠር ሽሚያ ላይ ይገኛሉ፡፡ የደሃ ሃገራት ምሁራኖች ለፖለቲካ ስልጣን ሲሉ ለዳግማዊ ዘመናዊ ባርነት መዳረጋቸው አይቀሬ ነው፣ በዚህ የዲጂታል ቴክኖሎጅ የኤሌክትሮኒክስ ግብይይት ዘመን፣ ሃገራችን የውጭ ንግድ ገቢ ከ2 እስ 3 ቢሊዮን ዶላር ሲሰላ ዓመታት ተቆጥሮል፡፡ ብሄራዊ ኢኮኖሚ ያልገነባች ሃገር በየክልል መንግሥት ህገወጥ የድንበር ንግድ ወርቅ፣ ሠሊጥ፣ የቀንድ ከብቶች፣ ጫት፣ ማዕድናት፣ ጎረቤት አገራት በዶላር የሚሸጥባት ሀገር የውጭ ንግድ ገቢዎ ሊያድግ አይችልም፡፡ የትግራይ ክልል መንግሥት ህገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር፣ የገንዘብና የመድኃኒት ዝውውር፣ የኮንትሮባንድ ንግድ ሥርጭት እያለ የሃገራችን በውጭ ንግድ ገቢ የውጭ ምንዛሪ አግኝታ ያለባትን ብድር መክፈል አትችልም፣ ከዕዳ ጫናዋም አትገላገልም እንላለን፡፡ በሃገሪቱ የጸረ-ዴሞክራሲ ኃይሎችን በማጠናከር የትግራይ ክልል ህወሓት የማይታይ ስውር እጅ በመዛመት፣ በኦሮሚያ ክልል የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ)፣ በአማራ ክልል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ በደቡብ ክልል ኤጄቶ የጸረ-ዴሞክራሲ ኃይሎችን ጎራ በመቀላቀል ከእኛ ውጪ መደራጀት አትችሉም በማለት አንባገነናዊ ሥርዓትን ለመገንባት ታች ላይ እያሉ ይገኛሉ፡፡ እኛ በዘር ስንናቆር ዓለም በሥልጣኔ ጥሎን ሄደ፣ ሦስት ሚሊዮን ህዝብ ተፈናቀለብን እርዱን፣ ርሃብ ገባ እርዱን ስንል ዘመን አለፈ፡፡ 

በተባበሩት መንግሥታት ኮንፍረንስ በንግድና ልማት ኮንፍረንስ  በማርች 31 ቀን 2019 መሠረት የዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ 13 በመቶ በ2017 ዓ/ም ጨምሮል፣ አጠቃላይ ሽያጩም  29 ትሪሊዮን ዶላር ይገመታል፡፡ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ 12 በመቶ በመጨመር 1.3 ቢሊየን ህዝብ ወይም የዓለም አንድ አራተኛ ህዝብ ቁጥር ይዞል፡፡ ( Global e-commerce sales grew 13% in 2017, hitting on estimated $ 29 trillion, according to the latest numbers released today by the UN Conference on Trade and Development (UNCTAD) march 31, 2019. Online shoppers, which jumped by 12% and stood at 1.3 billion people, or one quarter of the world’s population.)

በዚህም ምክንያት ድንበር ዘለል የኤሌክትሮኒክስ ለሸማቾች ንግድ  ሽያጭ Business-to-Consumer (B2C) 412 ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ ሲገመት፣ የግለሰብ ሸማቾች የኤሌክትሮኒክስ ንግድ ድርሻ 11 በመቶ ሽያጭ በመያዝ 9 ትሪሊዮን ዶላር ደርሶል፡፡ የአሜሪካ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ  ከጃፓን ሦስት እጥፍ ሲበልጥ፣ ከቻይና አራት እጥፍ እንደሚበልጥ ታውቆል፡፡ በተመሳሳይ የእንግሊዝ የኤሌክትሮኒክስ የሸማቾች ንግድ  ሽያጭ 82 በመቶ ህዝብ ሽያጩን በኤሌክትሮኒክስ በ2017 እኤአ ማከናወናቸው ታውቆል፡፡ ሀገረ ጀርመን በአራተኛ ደረጃ እንዲሁም የኮርያ ሪፓብሊክ አምስተኛ ደረጃ ይዘዋል፡፡ የእኛ ሀገር ደረጃስ!!!  (As a result, cross-border Business-to-Consumer (B2C) sales reached an estimated $412 billion, accounting for almost 11 % of total B2C e-commerce. At almost $9 trillion, online sales there were three times higher than in Japan and more than four times higher than in China. (Germany fourth largest online market and republic of Korea fifth)

በተጨማሪም የቢዝነስ-ለ-ቢዝነስ (Business-to-Business (B2B) የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ 3.9 ትሪሊን ዶላር እንደደረሰ ሲገመት፣ የቢዝነስ -ለ-ቢዝነስ ንግድ ድርሻ 88 በመቶ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ   በመያዝ 9 ትሪሊዮን ዶላር ደርሶል፡፡ ቻይና በቢዝነስ-ለ-ቢዝነስ ንግድ የኤሌክትሮኒክስ ሽያጭ አንደኛ ስትሆን አሜሪካ ሁለተኛ፣ እንግሊዝ ሦተኛ ደረጃ ይዘዋል፡፡   በአጠቃላይ ቻይና 440 ሚሊዮን ህዝብ በኢንተርኔት የኤሌክትሮኒክስ   ሽያጭ በማከናወን ከፍተኛውን ደረጃ ይዛለች፡፡ (Business-to-Business (B2B) e-commerce continued to dominate- accounting for 88 % of all online sales- B2C increasing by 22% to reach $3.9 trillion in 2017. In the B2C realm, China increased its lead on the United States, while the United Kingdom healed on to third place. UK B2C 82 % of people making purchases online in 2017. Overall, however, China had the largest number of internet buyers at 440 million.)

የኢትዮጵያ የስሊጥ ምርት፣ ኢትዬጵያ ቻይና የሠራችላትን የመሠረተ ልማት ዕዳ ለመክፈል አጠቃላይ የስሊጥ ምርቷን ወደ ቻይና ተጭኖ እንደሚላክ  ዓለም ያወቀው፣ ፀሓይ የሞቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ በ2002 እኤአ ኢትዬጵያ 38000 ሜትሪክ ቶን ሰሊጥ በማምረት ትታወቅ ነበር፡፡ በተባበሩት መንግስተሰት የምግብና የእርሻ ድርጅት ጥናት መሰረት በ2011 እኤአ 320000  ሜትሪክ ቶን ሰሊጥ በማምረት ከአፍሪካ በምርት ትልቁን ድርሻ ስትይዝ ከዓለም ደግሞ አራተኛ ሰሊጥ አምራች አገር ለመሆን በቅታለች፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ቻይና ደግሞ ከሰሊጥ ላኪ አገርነት  ኢትዬጵያ ሰሊጥ ወደ ቻይና በማስገባት ትታወቅ ጀመር፡፡ የሰሊጥ ምርት ለዳቦ፣ ለቅመማ ቅመም ማጣፈጫነት፣  ተጨምቆ ወደ ዘይት ምርትነት እንዲሁም ለዶሮ እርባታ ከፍተኛ የፕሮቲን ገንቢ ግብአትነት በማገልገል ይታወቃል፡፡ ለኢትዬጵያ ቻይና የፍብሪካዎች ምርቶች ወደ ሃገር ውስጥ መግባት፣የብድር አገልግሎት መመቻቸትና አዳዲስ የመሠረተ ልማት ግንባታ ስራ አወዳጅቷቸዋል፡፡ የቻይና ልማት ባንክ 25 ሚሊዩን ዶለር ብድር ለእርሻው ዘርፍ ኢንተርፕራይዝ ሰጥተዋል፡፡እንዲሁም የቻይና አስመጭና ላኪ ባንክ 3.3 ቢሊዩን ዶለር ብድር ከኢትዬጵያ ወደ ጅቡቲ ነጋድ ወደብ ለሚዘረጋ የባቡር ሐዲድ መስመር ዝርጋታ ሰጥታለች፡፡ በ 2011 እኤአ ኦክስፋም ጥናት መሠረት ከሆነ በኢትዬጵያ 600 000 አነስተኛ መሬት ያላቸው ገበሬዎች ሰሊጥ በማምረት ይተዳደራሉ፣ትንሽ መሬት፣የዘር ችግር፣ጥራት አልባ ምርትና በብድር አቅርቦት  እጦት እንደሚቸገሩ ይታወቃል፡፡ ታዲያ በኢትዬጵያ ንግድ ባንክ የሰሊጥ ምርት ተሰብስቦ ወደ ቻይና መላክ የአነስተኛ ገበሬዎችን የገቢ ምንጭ በመቀነስና ገበሬዎች ለማምረት ይበረታታሉ ለማለት አያስደፍርም፡፡ እንደ ደርግ ወታደራዊ አገዛዝ ዘመን  ገበሬዎች ለእርሻ ሰብል ገበያ ድርጅት (እሰገድ) ምርታቸውን ማስረከብ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ የቻይና መንግሥት ለሃገራችን ያበደረውን ብድር ለማስመለስ የግብርና ምርቶቻችንን እንደ ሠሊጥ፣ ቡና፣ የቀንድ ከብት፣ ወርቅ፣ ወዘተ በኢንተርኔት የኤሌክትሮኒክስ   ሽያጭ ማዝመን ስበብ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሁሉን ንግድ ይቆጣጠሩታል፡፡ ሃገር በቀል ባለኃብቶችና የንግዱ ህብረተሰብ ለሃገርህና ለወገኖችህ በማሰብ ተግተህ መስራት የህልውና ጥያቄ ነው እንላለን፡፡

In return, Ethiopia has effectively been using sesame seeds to repay Chinese loans. Foreign currency earned by selling sesame is passed over to the state-owned Commercial Bank of Ethiopia and used to secure and repay loans provided by China, according to Deborah Bräutigam, senior research fellow at the International Food Policy Research Institute. The relationship is likely to have started in 2005-06 as a shortage of sesame seeds in China and a favourable tariff policy (set by China) kickstarted the rise in Ethiopian exports, which are regulated largely by the state-owned Ethiopian commodities exchange. Bräutigam says China is unlikely to have stipulated that Ethiopia export its sesame, which is now its second most valuable export after coffee. “The ‘guaranteed supply’ of whatever export is already going to China is simply the mechanism for ensuring repayment of the loan,” she says. The Government of Ethiopia is planning Potase mining as acollatoral for repayment of the Chinese loans.

የቤልት ኤንድ ሮድ ኢንሼቲቭ ፎረም ስብሰባ ዶክተር አብይ አህመድ መንግስት ከቻይው ስቴት ግሪድ ከተሰኘው ኩባንያ ጋር  የ1.8 ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በኤሌክትሪክ ኃይል ማሰራጫና ማከፋፈያ ስርጭት መዋለ ንዋይ ለማፍሰስ ስምምነት አድርገዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ለ16 የኢንዱስትሪ ፓርኮች የኤሌትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ ለሁለተኛው የአዲስ ጅቡቲ የባቡር መሥመርና ለከተሞች የኤሌትሪክ ኃይል ለማዳረስ የሚያስችል ነው፡፡ በተመሳሳይ የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለማሳደግ በዲጂታል ቴክኖሎጅ የኤሎክትሮኒክስ ግብይይት፣ ከአሊባባ የኢንተርኔት ንግድ ኩባንያ ጋር ንግድን ለማዘመን የቻይና መንግሥት የሃገሪቱ የውጭ ንግድ ምርቶች ቡና ፣ሠሊጥ፣ ቆዳ፣ ወርቅ ወዘተ ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር ሥራ ላይ ለመሠማራትና የውጭ ምንዛሪ ገቢ በመጨመር የሃገሪቱን ብድርና የእዳ ጫና ለማቃለል የጋራ ስምምነት አድርገዋል፡፡ 

የኢንተርኔት ኢኮኖሚ (Internet economy) በኮምፒውተር ኢንተርኔት ግንኙነት በዓለም አቀፍ  መረጃ መረብ የኤሌክትሮኒክስ ግብይይት በማድረግ ሁሉንም የኢኮኖሚ ዘርፎች በማዘመን ቀድመው የዲጂታል  ቴክኖሎጂውን ያስፋፉ ተጠቃሚ የሚሆንበት የዓለም አቀፍ የገበያ ሥርዓት ነው፡፡ በኢንተርኔት ኢኮኖሚ  ኢንተርኔተ-ቁስ (Internet of Things(IoT) አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence(AI) እና ብሎክ ቼን (blockchain) የኢንዱስትሪና የቴክኖሎጂ አብዬት ህዳሴ አስገኝተዋል፡፡ በዚህ የኢንተርኔት ኢኮኖሚ የዲጂታልና የቁሳዊ ዓለም ውህደት እድገትና ትስስር ይፋጠናል፡፡ መንግሥትና የፖሊሲ አውጪዎች  ለዘብተኛ አቆም ለህብረተሰቡ የኢኮኖሚና ማህበራዊ የለውጥ ፍላጎት የኢንተርኔት ኢኮኖሚ እውቀትና ክህሎት በማስፋፋት አራኛው የዲጅታል ኢንዱስትሪ አብዮት ሥልጣኔ ወጣቱ ትውልድ እንዲቀስም የኢንተርኔት ስርፀትና ስርጭት መሠረተልማት በመዘርጋት የኢንተርኔተ-ቁስና  አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እውቀትን በጊዜው መገብየት ያስፈልጋል፡፡  መንግስታት የመረጃ ቆት አያያዝና መረጃን የሚመራ ብሄራዊ የዲጂታለል ፖሊሲ መቅረፅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በኢንተርኔት ኢኮኖሚ  ኢንተርኔተ-ቁስ (Internet of Things(IoT) ሸቀጣ ሸቀጦች የእቃዎች መረጃ መረብ ቆት ሲሆን ለምሳሌ የመኪኖች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክ ቁሶች፣ ሶፍት ዌር፣ ሴንሰር፣ አክቹወተር እና በኢንተርኔት መረጃ ቁሶችን ማገበያትና ማለዋወጥ የንግድ ሥራ ያከናውናሉ፡፡ በኢንተርኔት የእቃዎች መረጃን የማግኘትና የመቀበል ተግባርን በየቀኑ ያሰራጫል፡፡

በኢንተርኔተ-ቁስ ዓለም አቀፍ የንግድ ሽያጭ 19 ትሪሊየን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ኢንተርኔተ-ቁስ መረጃ መረብ ቆት እድገት ከዓመት አመት እያደገ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት በ1992እኤአ መቶ ሽህ ሰዎች ኢንተርኔተ-ቁስ የንግድ ግብይይት አድርገው ነበር፡፡ በ2003 እኤአ 500 ሚሊዮን ፣በ2012 እኤአ 8.7 ቢሊየን፣ በ2017 እኤአ 28.4 ቢሊየን እድገት ሲያሳይ በ2020 እኤአ 50.1 ቢሊየን የንግድ ግብይይት በኤሌክትሮ ኮሜርስ/ ንግድ ይከናወናል ተብሎ ይገመታል፡፡  የዲጅታል አብዬት ዘመን ዝቅተኛ የኢንተርኔት ስርፀትና ስርጭት ያላቸው አገረት የኤሌክትሮ ኮሜርስ/ ንግድ ውጭ በሚላኩ ምርቶች እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ መረጃዎች የሚከማቹባቸው ትልልቅ ስርቨሮችና ፋይበር ኬብሎች እና ብሮድባንድ፣ ዋይ ፋይ፣ ጂፒኤስ የቴሌኮም መሰረተልማቶች በማሳደግ የኢንተርኔት ግንኙነት ፍጥነትን በማፋጠን መረጃ ቆት አያያዝና መረጃን መለዋወጥ እድገትን ማፋጠን ይቻላል፡፡ በዚህም የኣለም አቀፍ የንግድ የገበያ ድርሻን በትምህርት ዘርፍ፣ በጤና ጥበቃ፣ ትራንስፖርትና አውቶሞቲቨ፣ የኢንዱስትሪና ማኑፋክቸሪንግ፣ ኤሌክትሮኒክስና የችርቻሮ የፍጆታ እቃዎች፣ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ እድገት ያሳያል፡፡ 

አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ artificial intelligence ከፍተኛ የዲጂታለል ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀሙት ተወዳዳሪ አገሮች በማምረት ወቅት አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ  ትልልቅ ዳታዎችን የሚያጠናቅሩበትና የሚተነትኑበት አቅም ስላላቸው ብሎም የኢኮሜርስ አገልግሎት/የኤሌክትሮኒክስ ንግድ በስፋት ስለዘረጉ ተወዳዳሪ መሆን አይቻለንም፡፡ የውጭ ንግዳችን ካልዘመነ የውጭ ምንዛሪ የማግነት አቅማችን ወደፊት የመነመነ ይሆናል፡፡ የባህር ማዶ የውጭ ንግድ ዘርፍ የምርት ገዥዎች ፍላጎት ላይ የተወሰነ ነው፣ ገዥዎቹ ዋጋ ተማኞችም ናቸው፡፡  የባንክና የፋይናንሻል ዘርፍ ኤቲሜ ማሽኖች የኤሌትሪክ ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት በመጠቀም  የባንክ ደንበኞች ከማሸኑ ገንዘብ የማውጣት፣የማስቀመጥ፣ የማስተላለፍ እንዲሁም የባንክ አካውንታቸውን መረጃ የማግኘት አገልግሎት በየትኛውም ጊዜ የማግኘት መብት ሲኖራቸው ያለ ባንክ ሙያተኞች አገልግሎት የሚያገኙበት ዘመናዊ ማሽን ነው፡፡  በዓለማችን 3.5 ሚሊየን ኤቲኤም ማሽኖች በላይ ይገኛሉ፡፡ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ያላቸው ሰው ሰራሽ ሮቦቶች በባንከርነት፣ በወታደርነት፣ በሃኪምነት ወዘተ በሁሉ መስክ አስደማሚ ሥራዎች በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በኤሌክትሮኒክስ ንግድ ከአሁኑ ተወዳዳሪ መሆን ካልቻልን በዓለም አቀፍ የንግድ ዘርፍ የመሳተፍ ብቃትና ችሎታችን ብዙ ያስከፍለናል እንላለን፡፡ በዚህ የዲጂታለል ቴክኖሎጂ የውድድር ዘመን ተግቶ ከመስራት በስተቀር ወሬ ምን ሊረባ፡፡ እንጀራ የሚበላው በእውቀትና ስራ እንጂ በዘር ፖለቲካ ማብካት አይደለም፡፡