አባይ ሚዲያ (መስከረም 21፣2012) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን መኖርያ ግቢ ውስጥ ያለፈው ሳምንት ማክሰኞ መስከረም 13/2012 ዓ.ም ከለሊቱ 10:30 ላይ ግርግር የተፈጠረ መሆኑንና መኪናቸው ተሰብሮ ላፕቶፕ እንደተወሰደ ተነግሮኛል ሲል የአሶሼትድ ፕረስ ዘጋቢው ኤልያስ መሰረት በፌስ ቡክ ገፁ ፅፏል።
ግቢው ውስጥ አራት መንግስት የመደባቸው ጥበቃዎች ቢኖሩም ድርጊቱ መፈፀሙንና ነገር ግን ሁኔታው ዘረፋ ብቻ ይሁን ወይስ ሌላ በሀላፊዋ ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ገና እየተጣራ ነው ተብሏል።
አራቱ ጠባቂዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ሲሆን ይህ ሁኔታ ሲከሰት በግቢው ውስጥ አራት ሌሎች መኪናዎች እንደነበሩ እና ሰበራ እና ዘረፋ የተደረገበት ሀላፊዋ የሚጠቀሙበት መኪና ብቻ መሆኑንና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችም ከመኪናው ስር እንደተገኙ ተነግሮኛ ሲል ኤልያስ በፅሁፉ አስፍሯል ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here