አባይ ሚዲያ (መስከረም 22፣2010) የጎንደር ከተማ ንፁሕ የመጠጥ ውኃ ተበክሏል እየተባለ በማኅበራዊ ገጾች የተለቀቀው መረጃ የተሳሳተ መሆኑ ተገለፀ።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነትና የደንበኛች አገልግሎት ቡድን መሪ አቶ አወቀ አሰፈሬ እንደገለፁት በሁሉም የውኃ ታንከሮች የጥበቃ አገልግሎት ስላለ ውኃው የሚበከልበት አጋጣሚ የለም ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ውኃው በላብራቶሪ እየተመረመረ ወደ ኅብረተሰቡ የሚሰራጭ ስለሆነ የጎንደር ከተማ ሕዝብ በአሉባልታው ሳይደናገጥ የውኃ አቅርቦቱን መጠቀም እንደሚችል ነው የተናገሩት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here