መስከረም 22፣2012 (አባይ ሚዲያ) ባለፋት አመታት ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ሠብዓዊና ዴሞክራሲያዊ የሆኑ መብቶቹ ተከብረውለት በነፃነት እንዲኖር የክልሉ መንግስት እና ህዝብ መጠነ ሰፊ የሆነ ትግል እንዳደረጉ ይታወቃል ያለው የፓርቲው መግለጫው በተለይም ላለፋት 27 ዓመታት ዋጋ ሲያስከፋሉ የቆዩ ግፈኞችን ከሌሎች የሀገራችን ብሄሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ጋር በመተባበር፤ በተለይም በአማራ ወጣቶችና ሌሎች የማህበረሰብ አባላት በመስዋዕትነት ጭምር የታገዘ ትግል በማድረግ የለውጥ አየር በኢትዮጵያ ምድር እንዲመጣ ግንባር ቀደም መስዋዕትነት ተከፍሏል ብሏል፡፡

መግለጫው አክሎም ይህ የለውጥ ጅማሮ በሁከትና መለያየት ውስጥ ትርፍን በሚያሰሉ፤ በሴራ ፖለቲካ ተወልደው ባደጉ አካላት እና የህዝቡን የለውጥ ጉዞ ለመቀልበስ በተለያዩ አቅጣጫዎች በተቀናጀ መልኩ በመዝመት፣ ክቡር የሆነውን የሰው ህይወት በማጥፋት፣ ዜጎችን በማፈናቀልና መሠል ሴራዎችን በመጎንጎን በርካታ ጥቃቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል ብሏል፡፡

ከዚህ ሴራ ጀርባም ክልሉን በኢኮኖሚ የማዳከም ፕሮጀክት እንዲሁም ታላቋ አገራችን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያላቸውን ያሮጌው ዘመን ቁማርተኛ መዥገሮችን የክልላችን የፀጥታ መዋቅር አስፈላጊውን ዋጋ ሁሉ እየከፈለ ከህዝባችን ጋር ሆኖ በጠንካራ ክንዱ የሚመክታቸው ይሆናል ብሏል፡፡

መግለጫው የፌደራል መንግስት እነኚህ ወንጀለኞች፣ ካለፈው ስህተት የማይማሩና በዚህ ታሪክ ይቅር በማይለው የጥፋትና የሽብር ሥራ ላይ የተጠመዱ አካላትን እንዲሁም ጉዳዮን ወደ ሌላ በማላከክ የህዝባችንን ደህንነት ላይ ተጨባጭ ችግር በሆኑ ጽንፈኛ የሀገራችን ሚዲያዎች ላይ ህግና ሥርግትን ተከትሎ እርምጃ በመውሠድ ህግ እንዲያስከብር እንጠይቃለን ብሏል፡፡

ለዘመናት በአንድነት ተዋህዳችሁ የኖራችሁ የአማራና የቅማንት ህዝቦችም በእናንተ ህይወት ለሚነግዱ የጥፋት ሃይሎች ሴራ ሳትጋለጡ በጋራ በመቆም በተለመደ አብሮነታችሁ ሴረኞችን በአንድነት በመቆም እንደምታሳፍሩ እንተማመናለን ብሏል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ለተሰው ንጹሀን ዜጎች እና የክልላችን የፀጥታ አካላት በክልላችን ህዝብና መንግስት ስም የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን ለመግለጽ እንወዳለን ሲል መገለጫውን ቋጭቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here