አባይ ሚድያ (መስከረም 23፣2012) “ለመላው ኢትዮጵያውያን የመጣው ለውጥ ትግራይ እንዳይገባ ለማድረግ ህወሀቶች አፍነው እየሰሩ ናቸው” ሲሉ የቀድሞ የህወሀት መስራችና የአሁኑ የትዴት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ተናገሩ። ዶክተር አረጋዊ በርሄ እንደተናገሩት “አሁን በአገሪቱ የተከሰተው ለውጥ ጥሩና ተስፋ የሚጣልበትም ሲሆን በአሁኑ ወቅት ያለው አስተዳደር ስሙ ኢህአዴግ ቢሆንም በርእዮተ አለሙና በአሰራሩ ድሮ ከነበረው የተሻለ እንደሆነ አብራርተዋል።
ዶ/ር አረጋዊ እንደገለጹት አሁን ኢትዮጵያ የምትከተለው ፌዴራላዊ ስርአት ሲመሰረት ዲሞክራሲያዊ ምህዳር እንዳልነበረው አስታውሰው ህወሀት ኢህአዲግ በፈለገው መንገድ ድርጅቶችን አቋቁሞ ፋይናንስ አድርጎ አምጥቶ ነው የፈደራል ስርአት መሰረትኩ ያለው ሲሉ አስረድተዋል። የተዛባ፤ የተቃወሰ አካሄድ ስለ ነበር የፌደራል ሰርአት አለ ማለት አይቻልም ያሉት የትዴት ፓርቲ ሊቀመንበሩ በመጀመሪያ ደረጃ ፌደራል ስርአቱ ዲሞክራሲን መሰረት አድርጎ እንደ አዲስ መዋቀር አለበት ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
ዶክተር አራጋዊ አክለውም ያለፈው ፌዴራላዊ ስርአት በዲሞክራሲያዊ ምህዳርና መሰረት የተዋቀረ አይደለም ብለዋል። አሁን ያሉ ድርጅቶች ፌደራላዊ ስርአቱን እንዴት ማዋቀር እንዳለባቸው ተወያይተው ያንን ደግሞ ወደ ህዝብ ይዘው ወርደውና ህዘብን አሳምነው በህዝቦች ሙሉ ፍላጎት፤ ፈቃድና ተሳትፎን መሰረት ያደረገ የፌዴራል ስርዓት እንደ አዲስ መዋቀር እንዳለበት ነው ዶ/ር አረጋዊ በርሄ የተናገሩት።
በተጨማሪም ለውጡ ጥሩና ተስፋ የሚጣልበትም እንደሆነ የተቆሙት ፖለቲከኛው ይህን አመለካከት ይዞ የመጣው የለውጥ ሀይል በሩን ለብዙ ነገሮች ክፍት ክፍት አድርጎታል ብለዋል።
ከዚህ ቀደም ህወሀት ኢህአዴግ ነፍጎት የነበረውን ሀሳብን የመግለጽ፤ የመደራጀትና የመንቀሳቀስ ነጻነትን ለውጡ አጎናጽፎናል ሲሉ የትዴት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ አክለዋል፡፡

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here