መስከረም 23፣ 2012 (አባይ ሚዲያ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በውጭ ሃገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ልዩ አገልግሎት የሚሰጥ የመጀመሪያ ቅርንጫፉን በአዲስ አበባ ከፍቷል፡፡ በቅርንጫፉ ዲያስፖራዎቹ ወደ ትውልድ ሃገራቸው በመጡ ጊዜ የቁጠባ ሂሳቡን በመክፈት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ቅድሚያ ሰጥቶ የሚያስተናግድበት ነው።

በአካል መቅረብ ለማይችሉትም በሚኖሩበት ሃገር አቅራቢያ በሚገኝ የኢትዮጵያ ኢምባሲ እና ቆንፅላ ፅህፈት ቤት አማካኝነት የባንክ ሂሳቡን መክፈት ይችላሉ ተብሏል። የቅርንጫፉ መከፈት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሃገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደርጋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ሃገራዊ የውጭ ምንዛሪ ግኝትንም እንደሚያሳድግ ተጠቁሟል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here