መስከረም 23/2012 (አባይ ሚዲያ) የኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ 2011 የውድድር ዘመን ከፕሪሚየር ሊጉ የወረዱት መከላከያ፣ደቡብ ፖሊስ እና ደደቢት ፌዴሬሽኑ በነሃሴ ወር ይፋ ባደረገው የፎርማት ለውጥ ምክንያት በሊጉ እንደሚቆዩ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም ለውጥ ተደርጎ ሊጉ በ 16 ክለቦች እንዲቀጥል መወሰኑ አግባብ አይደለም ሲል የደቡብ ፖሊስ ቅሬታውን አቅርቧል ፡፡

ፌዴሬሽኑ እየበጠበጠን ነው እኛ በ2012 በሊጉ ተሳታፊ ስለሆናችሁ ዝግጅት አድርጉ ተብለን በደብዳቤ ተጽፎልን እኛም ያን ተከትለን ለፕሪሚየር ሊጉ እንዘጋጅ በሚል በጀት የመደብነው፣ተጫዋቾችንም ሆነ አሰልጣኝ ያስፈረምነው ብለዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ እየተከተለው ያለው የሃሳብ መለዋወጥ በእጅጉ አሳዝኖናል ያሉ ሲሆንክለቡ በጉዳዩ ዙሪያ ለፌዴሬሽኑ ደብዳቤ እንደሚያስገባ የህ/ግንኙነት ሀላፊዋ ገልጸዋል፡፡