መስከረም 25፣ 2012 (አባይ ሚዲያ) በነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ተጭኖ የነበረ ከ2 ሺህ 200 በላይ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች እና አሽከርካሪው ጎንደር ከተማ ላይ ዛሬ ማምሻውን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

አሽከርካሪው የጦር መሳሪያዎቹን በመጫን መነሻውን ከሱዳን አድርጎ ወደ ጎንደር ሲገባ እንደተያዘ ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በተደረገ ቆጠራ 2 ሺህ 221 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ፣ 34 ባለ ሁለት እግር ታጣፊ ክላሸንኮቭ፣ አንድ ባለ አንድ እግር ታጣፊ ክላሸንኮቭ፣ 35 ባለሰደፍ ክላሸንኮቭ እና አንድ ጄ ኤም-3 እንደተያዘ ታውቋል።

አሽከርካሪውም በቁጥጥር ስር መዋሉም የታወቀ ሲሆን የጦር መሳሪያዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ሰራተኞች እና በአማራ ክልል የሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ በጥምረት እንደሆነ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here