አባይ ሚዲያ (መስከረም 27፣2012) አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በማኅበራት ተደራጅተው ከቀረጥ ነፃ የገቡ በሥራ ላይ የሚገኙ ባለ ሜትር ክፍያ ታክሲዎችን የክፍያ ተመን ወጥነት ያለው ለማድረግ የሚያስችል ጥናት እየተጠናቀቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለሥልጣን አስታወቀ።
የቢሮው ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ በድሉ ሌሊሳ በተለይ እንደገለጹት ቀደም ሲል የተቀመጠው ክፍያ ተመን ወጥነት ባለው መልኩ እየተተገበረ ባለመሆኑ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥናት መደረጉን ተናግረዋል።
አያይዘውም ተመኑ ዝቅተኛ ነው በሚል የተወሰኑ ማኅበራት በድርድር ወደ መስራት መግባታቸውን እና ይህንን ለማስተካከል የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመልክተዋል።
በመሠረታዊነት ጥናቱ ያስፈለገው ቢሮው ባስቀመጠው አቅጣጫ የማይመሩ እንዲሁም የራሳቸውን የክፍያ ተመን አውጥተው የሚሠሩ በመኖራቸው መሆኑንም ጠቁመዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here