አባይ ሚዲያ ( መስከረም 27 ፣ 2012 ) ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ሰብሳቢ እንደተናገሩት “ይህንን ምርጫ ማሳካት ለኛ ለኢትዮጵያውያን እንደ አማራጭ ሊቀርብ የሚችል ጉዳይ ሳይሆን በግዴታ ልናሳካው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡” ምንም እንኳን አሁን ላይ አገሪቱ አሳሳቢ ሁኔታዎች ውስጥ ብትገኝም ስልጣን እና ሀላፊነታችንን ለይተን በማወቅ ምርጫውን ነጻ ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ ማድረግ ሃገራዊ ግዴታችን በመሆኑ ምርጫውን በአግባቡ እናስፈጽማለን ስትል ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ተደምጣለች፡፡

አሁን ላይ በርካታ የፖለቲካ ድርጅቶች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባፀደቀው የምርጫ ህግ ላይ ተቃውሞ ያላቸው ሲሆን  ምርጫው ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ ይሆናል መባሉ መራጭ እና ተመራጩ ሳይታወቅ የሚወራ በመሆኑ ህዝቡን እና የፖለቲካ ድርጅቶችን ማስተዋወቅ የምርጫ ቦርድ ቀዳሚ የቤት ስራ ሊሆን እንደሚገባ በርካቶች አስተያየታቸውን እየሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡ ሰባ የሚደርሱ የፖለቲካ ድርጅቶችም አዲስ የጸደቀውን የምርጫ ህግ በመቃወም የርሃብ አድማ ለማድረግ ቀን መቁረጣቸው ይታወሳል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here