አባይ ሚዲያ (መስከረም 28፣2012) ትላንት መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የፓለቲካ ፓርቲዎች ሊያደርጉት የነበረው ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ” በሚል ርእስ በኢትዮጵያ ብርድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ፌስቡክ ገጽ የተዘገበው ዜና የተሳሳተ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል::
ቦርዱ በትላንትናው እለት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምንም አይነት ውይይትም ሆነ ድርድር ያላደረገ ሲሆን የኢቢሲም ሆነ የኢቢሲን ዜና መሰረት በማድረግ የዘገቡ ሌሎች ሚዲያዎች ዜናዎችን ከማሰራጨታቸው በፊት ማጣራት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here