አባይ ሚዲያ (መስከረም 28፣2012) ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ የኤታስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲከተሉት ባወጣው መመሪያ ዙሪያ እና የትራንስፖርት ሴክተሩን በዘላቂነት ዘመናዊ ለማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከ13 ተቋማት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
የኤታስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማቱ በከተማ አስተዳደሩ ረቅቆ በቅርቡ ይፋ የሆነው መመሪያ ቴክኖሎጂው ላይ ምንም ተፅዕኖ እንደሌለው ተናግረው ህጉን እንደማይቃወሙ እና ለተፈፃሚነቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የትራንስፖርት አሰጣጥ በከተማዋ ውስጥ እንዲስፋፋ ፍላጎቱ ነው ያሉት ኢ/ር ታከለ ኡማ
ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ተጨማሪ ቴክኖሎጂዎችን ለሚያመጡ በራቸው ክፍት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ተቋሞቹ በከተማዋ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ተሽከርካሪዎች ያረጁ በመሆናቸው የከተማ አስተዳደሩ ተሽከርካሪዎቹን በአዲስ በመተካቱ ሂደት ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here