አባይ ሚዲያ (መስከረም 28፣2012) ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የውጭ ምንዛሬ በአስቸኳይ ካልለቀቀለት ጋዜጦችን፣ፈተናዎችንና ሌሎች ህትመቶችን ከሁለት ወራት በኋላ ማተም ሊያቆም እንደሚችል ገለጸ።
የድርጅቱ የኮርፖሬት ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታሁን ነጋሽ ‹‹ለህትመት መሰረታዊ የሆኑት ወረቀት፣ ቀለም፣ ፕሌት፣ ኬሚካልና ሌሎች 90 በመቶ የሚሆኑት ግብዓቶች ከውጭ አገር ስለሚገቡ የውጭ ምንዛሬ ያስፈልጋል።
ከግብዓት በተጨማሪም መለዋ ወጫና አዳዲስ ማሽኖችን ለመግዣ የውጭ ምንዛሬ ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን ለድርጅቱ ከአንድ ዓመት በላይ የውጭ ምንዛሬ እንዲፈቀድልን ጥያቄ ብናቀርብም እስከዛሬዋ ዕለት ድረስ አልተፈቀደልንም።
በተለይም ባለፉት ስድስት ወራት ለብሄራዊ ባንክ ሊያጋጥመን የሚችለውን ችግር በስፋት አስረድተናል፤ ነገር ግን መፍትሄ አልተሰጠንም›› ብለዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here