አባይ ሚዲያ (መስከረም 28፣2012) በአሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቁር አሜሪካዊው የፊልም ፕሮዲዩሰር እና ተዋናይ ታይለር ፔሪ ባለቤትነት የሚተዳደር የፊልም ስቱዲዮ ተመረቀ፡፡
ጥቁር አሜሪካዊው የፊልም ፕሮዲዩሰር እና ተዋናይ ታይለር ፔሪ ከአሁን በፊት በርካታ ፊልሞችን በተዋናይነት እና ፕሮዲዩሰርነት ያበረከተ ሲሆን የሴት ገጸ ባህሪ ወክሎ የተጫወተው ማዲያ የተሰኘው ተከታታይ ፊልም ዝነኛ አድርጎታል፡፡
በዚህ ስቱዲዮ ምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ሳሙኤል ጃክሰን ፣ሴስሊ ታይሰን፣ኦፍራህ ዊንፍሪ እና ኤርትራዊቷ ቲፋኒ ሃዲሽ እንዲሁም ኢትዮጵያዊቷ አርቲስት አምለሰት ሙጨ የተገኙ ሲሆን እውቅ ባልና ሚስት ሙዚቀኞች ቢዮንሲ ና ጀዚ በሰርፕራይዝ እንግድነት ተገኝተዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here