አባይ ሚዲያ (መስከረም 28፣2012) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ 40 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ፡፡
የግድቡ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ እንደገለጹት ግንባታው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን 99 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል፤ ቀሪ ሥራውን ለማጠናቀቅም 40 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡
“መንግሥት በወሰዳቸው እርምጃዎች በርካታ ህፀፆች ተስተካክለዋል፤ በተለይም ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው ተቋራጮች ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉ ትልቅ ውሳኔ ነው፤ በዚህ ወቅት የግድቡ ግንባታ ከ68 ከመቶ በላይ ደርሷል’’ ብለዋል ሥራ አስኪያጁ፡፡
በ2013 ዓ.ም ሁለት ተርባይኖች የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደሚችሉም ነው የገለጹት፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here