አባይ ሚዲያ (መስከረም 28፣2012) ከሴኔጋል ወደ አዲስ አበባ ይበር የነበረው ንብረትነቱም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው የበረራ ቁጥር ET-908 የሆነው ቦይንግ 767-300 አውሮፕላን ከተነሳ በኋላ በቀኝ በኩል ባለው ሞተሩ እሳት በማሳየቱ ወደተነሳበት ብሌዝ ዳያግኒ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተመልሶ ለማረፍ መገደዱን የሴኔጋል አየር መንገድ ቃል አቀባይ ታይዳኔ ታንባ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ አውሮፕላኑ በመደበኛ በረራ ከሴኔጋል ዲአስ በማሊ ባማኮ አድርጎ አዲስ አበባ ለመብረር ጉዞ ጀምሮ እንደነበርና የቴክኒክ ችግር እንደገጠመው እንጂ ሌላ ያለው ነገር የለም፡፡
በአውሮፕላኑ የቀኝ ሞተር የተነሳውን እሳትም የሴኔጋል የእሳት አደጋ ሰራተኞች ለማጥፋት ችለዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኞቹ በመጉላላታቸው ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን ሁሉም ተሳፋሪዎች በተለዋጭ በረራዎች ጉዟቸውን መቀጠላቸውን አስታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here