በአህጉራዊ ውድድሮች ላይ የሚሳተፉ ክለቦች ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ የሜዳ ላይ ጨዋታቸውን ከሃገር ውጪ እንዲያከናውኑ ሊገደዱ እንደሚችሉም ተነግሯል ፡፡
በግብጽ እየተካሄደ ባለው የካፍ የክለብ ላይሰንሲንግ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ አብነት ገብረመስቀል ለፌደሬሽኑ መቀጣት ምክንያቱ ከክለብ ላይሰንሲንግ ጋር የተገናኘ መሟላት የሚኖርባቸውን ቅጾች በሚገባ ባለመሙላቱ እና መመዘኛዎችን ለማሟላት መቸገሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሚሳተፉ ክለቦች የሚጫወቱባቸው ስታዲየሞች ደረጃውን የጠበቀ የመጫወቺያ ሜዳ ፣ በቂ ፓውዛ ያላቸው ፣ ወንበር የተገጠመላቸው እንደዚሁም ንጹ እና በቂ መጸዳጃ ቤቶች ያላቸው ሊሆን እንደሚገባ ተገልጿል ፡፡
ሶስት የተለያዩ ስታዲየሞችን በአማራጭነት ማስመዝገብ እንደሚችሉም የተነገረ ሲሆን በኮንፌደሬሽን ዋንጫ ላይ የሚሳተፉትም ቢሆኑ ተቀራራቢ መስፈርት እንደተጠየቀባቸው ተሰምቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here