አባይ ሚዲያ (መስከረም 28፣2012) በስራ ላይ ያለው የፌዴራል ጥቅል ዓላማ ያለው ድጎማ ማከፋፈያ ቀመር ተግባር ላይ የሚውልበት ጊዜ እስከ 2014 ዓ.ም እንዲራዘምና ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው አዲሱ የድጎማ ማከፋፈያ ቀመር ዝግጅት ከተያዘው በጀት ዓመት አንስቶ እንዲጀመር የፌዴሬሽን ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ ወሰነ፡፡ ምክር ቤቱ ባካሄደው 5ኛው የፓርላማ ዘመን አምስተኛ ዓመት አንደኛ መደበኛ ስብሰባው ከተመለከታቸው አጀንዳዎች መካከል በስራ ላይ ያለው የድጎማ ማከፋፈያ ቀመር ተግባር ላይ የሚውልበት ጊዜ በሁለት ዓመት እንዲራዘም የሚል ሲሆን፤ የምክር ቤቱን አባላት በስፋት አከራክሯል፡፡
ለመራዘሙ በምክንያትነት የቀረቡት ጉዳዮች አሳማኝና ተጨባጭ ያልሆኑ፣ ተቀባይነት የሌላቸው፣ የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታም ያላገናዘቡ በመሆኑ የውሳኔ ሃሳብ ሊታለፍ ይገባል የሚል አቋም ይዘው ተከራክረዋል፡፡ ዘንድሮ አገራዊ ምርጫ የሚካሄድ በመሆኑም ካለው አገራዊ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር የፌዴራልና የክልል አመራሮችን አግኝቶ ቀመሩን አሳታፊ በሆነ መንገድ ለማዘጋጀት አስቸጋሪ እንደሚሆን ተብራርቷል፡፡ ማሻሻያ ከተደረገበት መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ለማስተላለፍ ያወጣው መመሪያ የህገ መንግስት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በማለት ጉባኤው በአብላጫ ድምጽ አቅርቧል፡፡
በመመሪያው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ የሟች ልጆች እጣውን መውረስ አይችሉም የሚል ሲሆን፤ መመሪያው ከ18 ዓመት በታች እና በላይ የሚል ልዩነት መፈጠሩ ምክንያታዊ አለመሆኑን ጠቅሶ በቤት ምዝገባ ወቅት ያልተመዘገቡ የቤት እጣ መውረስ አይችሉም የሚለው አቋም አግባብነት የለውም ብሏል፡፡በሟች ወራሾች መካከል ልዩነት መፍጠር በህገ መንግስት የተሰጣቸውን በህግ እኩል ጥበቃ የማግኘት መብት የሚሸራርፍ እንደሆነም ተቀምጧል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here