አባይ ሚዲያ (ጥቅምት 2 ፤ 2012) በስዊድን ስቶክሆልም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና በዚያ የሚገኘው የባላደራው ምክር ቤት ቅርንጫፍ በዛሬው እለት የተከለከለውን የባለአደራ ምክር ቤት ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በሀገሪቷ ፓርላማ ፊትለፊት በአዲስ አበባ የታፈነውን ድምጽ እንቃወማለን፣ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የሚሉና የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ   ድምፃቸውን አስምተዋል ።

በተያያዘ መረጃ ይህንኑ በማስመልከትም በዛሬው እለት ከምሽቱ 4 ሰአት ላይ በካናዳ ቶሮንቶ በ 217 ዳንፎርዝ መንገድ በሰብአዊ መብትና ዲሞክራሲ አንድነት ፅህፈት ቤት በቶሮንቶ እና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውንና ትውልደ  ኢትዮጵያውን የአጋርነት መግለጫ ህዝባዊ ውይይት እንደሚያደርጉ ለማወቅ ችለናል፡፡