አባይ ሚዲያ (ጥቅምት 2 ፤ 2012) በትላንትናው እለት ካልተነኩት ማዕዶች የተሰኘ የውይይት መርሃ ግብር በከዚፋ ሕንፃ አዳራሽ ውስጥ ተደርጓል፡፡ በርከት ያሉ ታዳሚያንን ባስተናገደው በዚህ የውይይት መድረክ ፕ/ር አደም ካሚል እና የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ መምህር የሆኑት ፕ/ር አህመድ ዘካሪያ የተገኙ ሲሆን መድረኩን ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በንግግር ከፍተውታል፡፡

አጀንዳውን ስለ ኢማም አህመድ ባደረገው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ጥግና ጥግ ላይ ቆሞ ከመጓተት ይልቅ ወደ መሀል መተን እንነጋገር የሚል ዓላማ ያነገበ ሲሆን የኢማም አህመድን ትክክለኛ ታሪክ ማወቅ እና እሱን መውሰድ እንዳለብን ተነስቷል፡፡ በስፍራው ከነበሩ ታዳሚያንም ስለ የኢማም አህመድን ጥያቄዎች ተነስተው በምሁራኑ መልስ ተሰቶባቸዋል፡፡