አባይ ሚዲያ (ጥቅምት 2 ፣ 21012 ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ በአለም ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተብለው ከተመረጡ አንድ መቶ ሰዎች ውስጥ ተካተዋል ፡፡ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በዲጂታይዜሽን፣ በመረጃ ደህንነት፣ በዲጂታል መታወቂያ እና በመሳሰሉት የዲጂታል አሰራር ስርዓት ውስጥ አስቻይ ሁኔታዎችን መፍጠር የመመልመያ መስፈርቶቹ ናቸው፡፡ በውድድሩ 500 እጩዎች ቀርበው 100 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የተመረጡ ሲሆን በዚህ ውድድር በመንግስት ሃላፊዎች ዘርፍ የኢትዮጵያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል፡፡

ሚኒስትሩ የግብርናውና የጤናው ዘርፍ በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ በማድረግ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተተከለው 350ሚሊየን ችግኝ በቴክኖሎጂ ተደግፎ እንዲቆጠር በማድረግ እና ኢትዮጵያ በ10 አመታት ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ የራሳቸውን አስተዋፅኦ ያበረከቱ መሆናቸው የተመረጡበት ምክንያት መሆኑም ታውቋል፡፡