አባይ ሚዲያ (ጥቅምት 2 ፤ 2012) ዛሬ ማለዳ የካቢኔ አባላት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ተገኝተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት በማግኘታቸው ደስታቸውን ገልጸዋል።

ለአመራሩ እንዲሁም ለተገኘው ስኬት ያላቸውን አድናቆት ለመግለጽም “እውነት ፍቅር ያሸንፋል” የሚል ጽሑፍ የተቀረፀበት የወርቅ ሀብል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አበርክተዋል፡፡